የሁሉም መልካም ነገር መጀመሪያ እንዳለሁ ሁሉ መጨረሻም አለው። የህይወት መልካም ፍሬዎች ለዘላለሙ አብረውን አይቆዩም ..
ስናጣቸው ፣ ስንፈልጋቸው ፣ ስንናፍቃቸው ፣ ስንመኛቸው ፣ ስናገኛቸው በሚኖረን የተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ ሆነን ጊዜያችንን እንገፋለን።
በነበረበት የሚቆይ ምንም የለም። እምነት ይሸረሽራል ፣ ፍቅር ጥፍጥናውን ይቀንሳል ፣ ግንኙነት ይሻክራል ፣ ደስታ ይጠወልጋል ፣ ናፍቆት ወደ መረሳሳት ይደርሳል ... አብሮነትም በመለያየት ይቋጫል።
በመጨረሻም መልካም ትዝታ በመልካም ምኞት ተወስነን .. የህይወት አድማሳችንን በአእምሯችን ጓዳ ሸክፈን እንከንፋለን።
የህይወት ተለዋዋጭ ክስተቶችን መቋቋም ካልቻልን .. በሞቃቱ ጊዜ ብርድ ፣ በደስታ ጊዜ ሀዘን ፣ በጥፍጥና ወቅት መራራን ካባ ደርበን ጊዜያችን ያልፋል።
የመጣውን መቀበል እስካልቻልን ድረስ የመኖርን ጣዕም ልናውቀው አንችልም። የሚሻለው ግን ..."የሁሉም መልካም ነገር መጀመሪያ እንዳለው ሁሉ መጨረሻውን አምነን መቀበልና .. ለሚመጣው አዲስ ነገር መዘጋጀት ነው" ...
ያጣናቸው ሁሉ በጎ አይደሉም። ያገኘናቸው ነገሮች ደግሞ በመልካም አጋጣሚነት የሚሰፍሩ አይደሉም።
የህይወት ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው ካላስተናገድናቸው በስተቀር .. በትዝታ የተሸበበ ፤ በፀፀት የተሞላ ፣ በእንባ የታጀበ .. አሰልቺ ህይወት ለመምራት እንገደዳለን።
___
⇩⇩⇩ለወዳጅ ዘመድዎ ሸር ይደረግ !
https://t.me/Oumerul_Faruq1https://t.me/Oumerul_Faruq1