ቀልበን ሰሊም


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


♥ ሰላማዊ ቀልብ ሁሌም በዕርጋታ የተሞላች ነች
ጥሩ ነገር ለማግኘት
ጥሩ ቦታ መገኘት
( @Qelbee )
ቀልበን ሰሊም የዑማው ቻናል
http://t.me/Qelbee

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Meren tube (مرن)
:
# ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያድርሱ
👇👇👇👇
👉👉 @Merennnnn
@merennnnn 👈👈
☝️👆☝️👆












Habib:
ታላቅ ሀገራዊ ተቃውሞ በ አዲስ አበባ አርብ ( ጁምዓ ) ታህሳስ 17 ከጠዋቱ 3 :00 ጀምሮ በአብዮት አደባባይ
መስጂዳችን ህልውናችን ነው በሚል መሪ ቃል !
የጁምዓ ሰላት እዛው ነው የሚሰገደው
ሁላችንም እንዳንቀር
ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ሼር ሼር


Ahmed:
አስተማሪ
ሶስት ጎደኞች ነበሩኝ ስማቸው በምህጻረ ቃል ‹‹ገ›› ‹‹ቤ››
‹‹ስ›› ናቸው፡፡ አንደኛወን ጎደኛዬን ‹‹ገ››ን ጠራሁትና እኔ
ስሞት ምን ይሰማሃል አልኩት ‹‹ገ›› አንተ ከሞትክ
አልቀብርህም በጓሮ በር ሹልክ ብዬ እወጣለሁ አለኝ፡፡
ሌላኛውን ጎደኛዬን ‹‹ቤ››ን ጠራሁትና እኔ ስሞት እንዴት
ትሆናለህ አልኩት፡ እሱም አንተማ ስትሞት አጥቤ ከፍኝ
እቀብርሃለሁኝ አለኝ፡፡ ሶስተኛ ጎደኛዬን ‹‹ስ››ን ጠራሁትና
እኔ ስሞት አንተ እንዴት ትሆናለህ አልኩት፡-አንተማ
ከሞትክ አብሬህ ነው የምቀበረው አልለይህም አለኝ፡፡ የቱ
ጎደኛዬነው ለኔ አሪፍ ትላላቹህ ከ‹ገ› ከ‹ቤ› ከ‹ስ› ቆይ
ግን እነዚህን ጎደኞቼን ለምን አልዘረዝርላችሁም፤
የመጀመሪያው ጎደኛዬ ‹‹ገ›› ያልኳችሁ ገንዘቤ ነው እኔ
ስሞት የሰበሰብኩት ገንዘብ ምንም አይጠቅመኝም ጥሎኝ
በጓሮ በር ነው የሚጠፋው፡፡ ሁለተኛው ጎደኛዬ
‹‹ቤ››ያልኳችሁ ቤተሰቤ ነው አጥቦ ከፍኖ የሚቀብረኝ
ነው፡፡ ሶስተኛው ጎደኛዬ ‹‹ስ›› ያልኳችሁ ስራዬ ነው
አብሮኝ ጉድጓድ የሚገባው አብሮኝ የሚቀበረው፡፡
ዋና ጎደኛችን ስራችን ነው
# ስንሞት አብሮን የሚቀበረውን ስራችንን አላህ
ያሳምርልን!


*ሙሳ እና ሐሩን* (ዓለይሂሙ ሰላም)
ከ *ክፍል አንድ እስከ ሀያ አንድ*
(ለትውስታ ያክል በጨረፍታ)
በነብዩሏህ ዩሱፍ አማካኝነት የያዕቁብ ልጆች የሆኑት እስራኤላዊያን ከ ሀገራቸው እስራኤል ወደ ግብፅ በመምጣት ሂወታቸውን መምራት ጀመሩ።
ከጊዜም በኋላ ዩሱፍ ይችን አለም ሲሰናበቱ የተተካው ንጉስ እስራኤላዊያንን የማይወድ ዝቅ አድርጎ የሚመለከት በመሆኑ የበታችነት ስሜት ተሰማቸው
በዚህ አላበቃም እየቆየ ስልጣኑ ሲረማመድ ወደ አመፀኛው ፊርአውን ዘንድ ደረሰ
ፊርአውንም ከ እስራኤላዊያን መንደር እሳት ተነስቶ ቤተመንግስቱ ሲቃጠል በህልሙ ያያል ህልሙን ሲያስተረጉምም ስልጣኑን ከእስራኤላዊያን ዘንድ የሚነሳ ሰው እንደሚወርሰው ህልም ፈችወች ነገሩት በዚህን ጊዜ ከባድ ውሳኔ ወሰነ ከ እስራኤላዊያን የሚወለዱ ወንድ ህፃናትን መግደል በዚህም ምክናየት ብዙ ሺ ህፃናትን ገደለ። ህዝቦች ሲያልቁ አንድ አመት ሚወለዱትን መግደል አንድ አመት ደግሞ ባለመግደል ተስማሙ ባማይገደልበት አመት የ ሙሳ ወንድም ሀሩን ተወለዱ።
በሚገደልበት አመት ደግሞ ሙሳ ተወለዱ። እናቲቱ ለማሳደግ ፈራች አላህም አሳድጊው ከፈራሺም በሳጥን አድርገሽ ጣይው ለኔም ለሱም ጠላት የሆነ ሰው ያነሳዋል ወዳንችም እንመልሰዋለን መልክተኛም እናደርገዋለን ይሄ ም እኛ የምንፈፅመው ቃላች ነው አላት።
እሷም በሀር ውስጥ ጣለችው *ፊርአውንም* አነሳው ሊገለው ሲል ሚስቱ አትግደለው ለኔም ላንተም የ አይናችን ማረፊያ ይሆናል አለችው እሺ ብሎ ተወላት ጡት ሚያጠባው ሴት ፍለጋ ተጀመረ አላህ ደግሞ ከ እናቱ በፊት የማንንም ጡት እንዲጠባ አልፈቀደም ሁሉንም ሴቶች አልቀርብ አለ በበሀር ውስጥ ሲጣል እህቱ የት እንደሚደርስ እየተከታተለችው ነበርና ስላማያውቋት ጠጋ ብላ እኔ ጡት የምታጠባላችሁ ሴት ልጠቁማችሁ አለች እሺ አሏት የሷም የሱም እናት የሆነችውን ሴት ጠቆመች እናቱ ማጥባት ጀመረች ሙሳ በ ጠላቱ ቤት አደገ ካደገም በኋላ ሰወች ተጣልተው ሲገላግል አንዱን ግብፃዊ በስተት ገደለው በዚህም ምክናየት እንዳይገሉት በመፍራት ሀገር ጥሎ ወጣ መድየን ወደምትባል ሀገር ሄደ እዛም ሁለት ሴቶችን ከብቶቻቸውን ውሀ የሚያጠጡ ሲሆኑ አገኛቸው እርሱም አጠጣላቸው አንዲቱ ልጅ ተመልሳ አባቴ ያጠጣህበትን ሊከፍልህ ይፈልግሀልና ጥሪው ብሎኝ ነው አለችው ሙሳም ተከትሏት ሄደ አባቷም ከሁለቱ አንዷን ሴት ዳረውና ለ 8አመት ቀጥሮት እዛው መስራት ጀመረ 10 አመት ሲሞላው ቅጥሩን ጨርሶ ወደ ግብፅ ተመለሰ በመመለስ ላይ ሳለ ወደ ጡር ተራራ እሳት ለማምጣት በሄደበት አላህ *እኔ አላህ ነኝ ከኔ ውጭ የሚመለክ አምላክ የለም* ሲል ጠራው የያዘውንም ብትር ጣል አለው ሲጥል እባብ ሆነች አንሳት አለው ወደ ብትርም ተመለሰች እጁንም እጉያው እንዲያስገባ አደረገው ሲያወጣው ነጭ ሚያበራ ሆነ *አላህም* እኒህን ምልክቶች ይዘህ ወደ *ፊርአውን* ሂድ አለው። ከነሱ ሰው ገድያለሁ ይገሉኛል ብየ እፈራለሁና አጋዥ አድርግልኝ ወንድሜ ሀሩንን አለ *አላህም* ጥያቄውን ተቀብሎ እሺ ለ ሀሩንም መልክቴን እልካለሁ ሂዱና ወደ እኔ ጥሩት አላቸው
*ሙሳም* ሂደው መልክቱን ነገሩት ሊሰማቸው ፍቃደኛ አይደለም እኔ አሳድጌህ ከኔ ሌላ አምላክ ሊኖርህ ይችላል ሲል ዛተበት *ሙሳም* ተዐምር ባሳይህስ አሉት እስኪ አምጣ አላቸው የያዙትን አሳዩት ደነገጠ ግን ጓደኛው ሀማን ይሄ ድግምት ነው እኛም የዚህ አይነት ድግምት እናመጣለን ብሎ ፊርአውንን አጃገነው በዙሪያው ያሉትንም መማክርት አማከራቸው ሙሳ ና ወንድሙን እዚህ አቆይ ከዛም ሰብሳቢወችን ላክ ድግምተኞችን ያመጡልሀልና አሉት። ፊርአውንም ሀሳባቸውን ተቀበለ። .......


*ይ ቀ ጥ ላ ል*
t.me/konkwyy




.






Репост из: Sunnah is fashion
...ነገ ሙሐረም ዘጠኝ ይደርሳል። ነብያችንን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘጠነኛዋንና አስረኛዋን ከፆምን የአንድ አመት ወንጀል እንደሚማርልን ተናግረዋል። ነገ በተለያየ አጋጣሚ መፆም የማትፈልጉ ወይም መፆም ያልተመቻችሁ የዐስረኛዋንና የዐስራ አንደኛዋን የመፆም መብት እንዳላችሁ መግለፅ እንፈልጋለን።

👉የዚህ ኸይር ተካፋይ ይሁኑ!
👉ለወዳጅ ዘመዶም ያካፍሉ!

#ሼር
t.me/sunnahupside




ወሬ ለማዳረስ ከመፈርጠጥ


ቅድሚያ ማረጋገጥ ማረጋገጥ
ሼር

http://t.me/Qelbee




#የዐሹራ_ፆምን_በተመለከተ

#የዐሹራ_ቀን ማለት የሙሐረም 10ኛውን ቀን ነው። ይህንን ቀን መፆም ተገቢ ነው። ምክንያቱም አላህ ነብዩሏህ ሙሳ - ዐለይሂሰላምን - ከፊርዓውን በደልና ግፍ ያላቀቀበት ቀን በመሆኑ ረሱል - ﷺ - ፁመውታል ሰዎችም እንዲፆሙ አዘዋል። ይህንን የሚገልፅ (ቡኻሪ ፥ 2004 እና ሙስሊም ፥ 1130) ላይ የተዘገበ ሐዲስ አለ። የዐሹራን ቀን መፆም ያለፈውንም አመት ወንጀል(ማለትም ትናንሹን) ያስምራል። የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ የዐሹራን ቀን መፆም አላህ ዘንድ ከዚህ በፊት ያለውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ] (መሰሊም ዘግቦታል). የዐሹራን ቀን መፆም እንጂ እንደዒድ አድርጎ መያዝ ክልክል እና አዲስ መጤ የሆነ ተግባር ነው።
°
ከአስረኛው ቀን አብሮ 9ኛውንም ቀንም መፆም ይወደዳል። ምክንያቱም ረሱል - ﷺ - ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ላይ [ የሚቀጥለው አመት ብደርስ 9ኛውንም ቀን ፆመዋለው። ] ስላሉ ማለት ነው። በዚህም ምክንያት ከአይሁዶች ጋር መቃረን ይገኝበታል።
°
ዘጠነኛውን ቀን መፆም ካልቻሉ 10ኛውን እና 11ኛውንም ቀን መፆም እንደሚቻል ዑለማዎች ተናግረዋል። ማስረጃቸውም ከዐብደሏህ ኢብኑ ዐባስ - ረዲየሏሁ ዐንሁማ - የተወራው ተከታዩ ሐዲስ ነው ፦ |" የዐሹራን ቀን ፁሙ የሁዳዎችንም ተቃረኑ ፤ ከሱ በፊት ያለውን ቀን ፁሙ ወይም ከሱ በኋላ ያለውን ቀን ፁሙ። "| (ሶሒሕ ኢብኑ ኹዘይመህ ፥ 3/290).
____
#የዘንድሮው_የ1441ሂ. ቀናቶችን ለማስታወስ ያክል እሁድ ሙሐረም 9 ፣ ሰኞ ሙሐረም 10 እና ማክሰኞ ሙሐረም 11 ናቸው። አላህ ይወፍቀን.


http://t.me/Qelbee


Watch "ጁማዓ ሙባረክ ማለት ቢድአነው ይዳመጥ?" on YouTube
https://youtu.be/ST0Hv8elkZo

ሼር ሰፕስክራይብ


🍁ሱረቱል ካህፍ በኢድሪስ አብካር🌸
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّاتُ الْفِرْدَوْسِ نُزُلًا

እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ የፊርደውስ ገነቶች ለእነሱ መስፈሪያ ናቸው፡፡

♦️ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች
▪️ገላን መታጠብ
▪️ጥሩ ልብስ መልበስ
▪️ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)
▪️በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ
▪️በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት
▪️ሱረቱል ከህፍን መቅራት
▪️ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ
_
🔻በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ, ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ, ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት እና ሶላት ካለቀ በኋላ ያመለጣቸውን ሰዎች ሶላት ሳይቆርጡ ረጋ ብሎ መውጣት ያስፈልጋል።

Показано 20 последних публикаций.

43

подписчиков
Статистика канала