📢
በሶ ግቢ ውስጥ 📚 በሶ ሳትይዝ ካንፓስ እንዳትሄድ
📚 በሶ ሲባል ምን ትዝ አለኝ መሰላቹህ ፍሬሽ እያለሁ ጥቂት በሶና ስኳር ይዜ ነበር እናም የሆነ ቀን ውግ ይድረሰኝ ብዬ በሶ መጣት አማረኝ ፤ አምሮኝም አልቀረ ውሃ ቀድቼ በሶና ስኳሬን ማሚ በነገረችኝ መሰረት mix አረኩና በበሶው ላይ ውሃ ጨምሬ shake ማድረግ ጀመርኩ ፤ ትንሽ ወዝ ወዝ እንዳረኩት ግን ድምፅ አልባ ቅጥቀጣ ብቻ ተረፈኝ ምንሼ ብዬ በርገድ ሳደርገው ገራሚ ሁኖልኛል
እንዴዴዴ ይቺም የሴት ስራ መሆኗ ነው ❓ እረ አልሰማሽም ብዬ ውሃ ብጨምርም በሶዋ ገንፎነቴ ይሻለኛል ብላ ግግም አለች ፥ እንገግም ካልንማ ካንቺ አናንስም ብዬ በማንኪያ ጥርግ አድርጌ እንክት.( እና የላቤን ውጤት ልደፋ ሲያምራችሁ...!)
📚 ሁለተኛ በሶ አልበጠብጥም ብዬ ልገዘት ስል አንዱ የዶርም ልጅ ጠኔው ሞርሙሮት መሰለኝ በኔው ውሃ በጥበጥ አርጎ የበሶ ነፍስ አድንነትን አስረዳኝ ። እኔም በዛው የበሶ አበጣበጥን ተማርኩ ማለት ነው ።
በሶ እንዴት ይበጥበጥ .... ❓
Apparatus of በሶ
🍼 የበሶ ዱቄት (beso flavour)
🍼 ውሃ በሃይላንድ
🍼 መበጥበጫ ዕቃ
🍼 ስኳር (ከበሶው ጋር ካልተፈጨ)
🍼 ማንኪያ or piece of paper
🍼 በርሃብ የተመታ አፍ፣ሆድ እና ከርስ
💡 Procedure of shaking በሶ( ለኔ ቢጤ ወንዶች...! )
1⃣ በመጀመሪያ የምንችለውን ያህል ውሃ በመበጥበጫው መጨመር
2⃣ በውሃችን ልክ ስኳር መጨመር ( ለ500ml water 3 የስኳር ማንኪያ sugar )
3⃣ ስኳሩንና ውሃውን ማዋሃድ( Either ማማሰል or መበጥበጥ )
4⃣ ሶስት ማንኪያ የበሶ ዱቄት መጨመርና በመበጥበጥ ማዋሃድ
5⃣ የበሶ ውህዱ ርሃብ የሚጨምር ድምፅ እስኪሰጥ ድረስ የበሶ ዱቄት መጨመር
6⃣ በርሃብ የተመታውን አፍ በግሩም በሶ ነፍስ መዝራት ...አለቀ ..!
Ok ለሴሚስተር ምን ያክል በሶ ይበቃናል ❓
ለnon ካፌ ተማሪዎች ሶስት ኪሎ በሶ በቂ ነው ከተቻለ ስኳሩንም አንድ ላይ ብታስፈጩት ለመያዝና ለመበጥበጥም ምቹ ነው። ለስፖርተኛ ተማሪዎች አስር ኪሎም ብትይዙ ሸክሙ አይጎዳችሁም ( በጠፋ ስኳር አስር ኪሎ ተሸክመህ በኋላ....) እንደኔ በሶ የማይደላቹህ ከሆነ ደግሞ ዳቦ ቆሎ ኩኪስ ምናምን ግድ ነው ።
📚 በሶ ማለት ግቢ ውስጥ ነፍስ አድን ነገር ናት so እንዳትንቋት!
✍️ Author: Unknown
@Qesem_University ✔️