Фильтр публикаций




Репост из: ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus
ሊንደን ጆንሰንን ቃለ መሐላውን ያስፈጸሟቸው ሴት ዳኛ ሲሆኑ እስካሁን በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ፕሬዝደንትን ቃለ መሐላ ያስፈጸሙ ብቸኛዋ ሴት ዳኛ ናቸው፡፡

ጆንሰን ቃለ መሐላ ላይ ሲፈጽሙ ጎናቸው የቆሙትም ባለቤታቸው በጥይት በተገደሉበት ጊዜ ለብሰውት የነበረውን ያንኑ ልብስ እንደለበሱ ነበር፡፡

ምስሉ ፕሬዝደንቱ በሰው እጅ ለተገደሉበት የአሜሪካ ሕዝብ ተተኪ ፕሬዝደንት መሰየሙን በስተቀር ባልተጠበቀ ምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥም ቢሆን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሥራ እንደሚቀጥል እምነት እንዲያድርበት ያደረገም ነበር፡፡

ታዲያ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሥራ ሁልጊዜ ያለ እንከን ይከናወናል ማለት አይደለም፡፡ በታቀደላቸው ስርዐት መሠረት ያልተከናወኑ ብዙ በዓለ ሲመቶች አሉ፡፡

በሥነ ሥርዓት ያልተከናወኑ በዓለ ሲመቶች የወፍ ምስል

ወደ ጥንት ወደ እ አ እ 1829 ዓም መለስ ብለን የአንድሩው ጃክሰንን በዓለ ታሪክን ብንቃኝ ቃለ መሓላቸውን ከፈጸሙ በኋላ በኋይት በነበረው ድግሥ ላይ የታደሙ ደጋፊዎቻቸው እጃቸውን እየጨበጡ ደስታቸውን ለመግለጽ ጓጉተው ሲረባረቡ አዲሱን ፕሬዝደንት ከግድግዳ ጋር አጣብቀው ሊደፈጥጧቸው ምንም አልቀራቸውም ነበር፡፡ ፕሬዝደንቱ በመስኮት ወጥተው እንዳመለጡ ታሪክ ይናገራል፡፡

በ1865 ደግሞ የፕሬዝደንት አብራሃም ሊንከን ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት አንድሩ ጆንሰን በቃለ መሐላ ሥነ ስርዐታቸው ላይ በስካር መንፈስ ንግግር ማድረጋቸው ተመዝግቧል፡፡ አሟቸው ስለነበረ ለህመም ማስታገሻ እንዲሆናቸው የወሰዱት ዊስኪ ነው ያሰከራቸው የሚል ምክንያት እንደተሰጠላቸው ተጽፏል፡፡

በ1873 ዩሊሰስ ኤስ ግራንት በበዓለ ሲመታቸው ድግስ ላይ "በድግሱ ቦታ ሰማያዊ ወፎች ቢበሩልኝ እንዴት ደስ ባለኝ ብለው ነበር" እና ሐሳባቸው ይሙላ ተብሎ ወፎች ለትዕይንት እንዲበሩ ተደረገ፡፡

ክፋቱ ብርዱ ነበር እና ወፎቹን ክንፋቸውን እያደረቀ እንዳረገፋቸው ይነገራል፡፡ የወፍ ነገር ከተነሳ እ አ አ በ1973ም ሪቻርድ ኒክሰን ርግቦች የበዓለ ሲመታቸው የሰልፍ ትዕይንት በሚያልፍበት መንገድ እንዳይገኙ ለማባረር ኬሚካል አስረጭተው ነበር እና የበዐሉ ታዳሚዎች የዋሽንግተኑ ፔንሲልቬኒያ አቨኑ ጎዳና ላይ መደዳውን ኬሚካሉ የገደላቸውን ርግቦች ሬሳ እንዳይረግጡ እየዘለሉ ያልፉ እንደነበር በፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመት ታሪክ ተመዝግቧል፡፡


Репост из: ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus
የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ
-------

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመት ትልቅ ቀን ነው፡፡ የራሱ የኾነ ወግ እና ሥርዐትም አሉት።

አንዳንዶቹ ከመጀመሪያው ፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ጀምሮ የነበሩ የክፍለ ዘመናት ዕድሜ የጠገቡ ወጎች አና ባሕሎች ናቸው፡፡ ታዲያ ሁሉም ፕሬዚደንታዊ በዓላተ ሲመት በሚፈለገው ሥርዓት አና ወግ በታቀደው መሠረት ተከናውነዋል ማለት አይደለም፡፡ እሱም ነው አንዳንዶቹን ከሌሎቹ ይበልጥ አይረሴ የሚያደርጋቸው፡፡

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1789 ዓ.ም የተከናወነው የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ጆርጅ ዋሽንግተን በዓለ ሲመት
የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ጆርጅ ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸውን የፈጸሙት ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡

በወቅቱ ኒውዮርክ የአገሪቱ ጊዜያዊ መዲና ስለነበረች ነው፡፡ አሜሪካዊያን ከዚያ በፊት ፕሬዝዳንት ኖሯቸው ስለማያውቅ የምክር ቤት አባላቱ ሥነ ሥርዐቱ እንዴት ቢከናወን ይሻላል በሚል መክረው እስኪወስኑ ጆርጅ ዋሽንግተን አንድ ሳምንት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡

ከዚያ በኋላ እ አ አ ሚያዚያ 30 ቀን ላይ ፕሬzደንቱ እና ምክትላቸው እንዲሁም የምክር ቤቱ አባላት የHግ መወሰኛው ምክር ቤት ውስጥ ከተሰባሰቡ በኋላ በረንዳው ላይ ወጥተው ደጅ ለሚጠባበቀው ታዳሚ እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታ ሰጡ፡፡

በመቀጠል ቃለ መሐላውን የሚያስፈጽሟቸው ዳኛ "በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትነት የተጣለብዎትን ኅላፊነት በታማኝነት ይወጣሉ? ብለው ጠየቋቸው፡፡

ጆርጅ ዋሽንግተን በአዎንታ ቃለ መሐላቸውን ሰጡ፡፡

ይህ ቃለ መሐላ እንዳለ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ውስጥ የተቀመጠ ነው፡፡ ዳኛው ጆርጅ ዋሽንግተን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምለው ቃል እንዲገቡ ለማድረግ ነበር ያቀዱት፡፡

ነገር ግን የሚከናወንበት ሰዓት ሲቃረብ ዳኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንዳላመጡ ባወቁ ጊዜ በጥድፊያ ሰው ተልኮ ከሌላ ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ በውሰት መጥቶ ጆርጅ ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸው ፈጸሙ፡፡

ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸውን ከፈጸሙ በኋላ ያዘጋጁትን ንግግር በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት ፊት አነበቡ፡፡

ዊሊያም ማክሌይ የተባሉ ሴኔተር በግል ማስታወሻቸው ላይ ዋሽንግተን ንግግራቸውን ሲያነቡ ተጨናንቀው እጃቸው ይንቀጠቀጥ እንደነበር ማንበብ አስቸግሯቸው እንደነበረም ጽፈዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዚደንት ዋሽንግተን ግር ቢላቸውም ሥነ ሥርዓቱ እጥር ጥፍጥ ያለ እንደነበር አክለዋል፡፡

ቶማስ ጀፈርሰን በ1801 ዓ.ም

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1801 ዓ.ም የሦስተኛው ፕሬዝደንት የቶማስ ጄፈርሰን በዓለ ሲመት ደግሞ ከጆርጅ ዋሽንግተን በዓለ ሲመት ይበልጥ ቀለል ብሎ የተከናወነ ነበር፡፡

ቶማስ ጄፈርሰን ወደ በዓለ ሲመቱ ሥነ ሥርዐታቸው የሄዱት ከሳቸው በፊት እንደነበሩት ሁለቱ ቀደምቶቻቸው በሠረገላ ሳይሆን በእግራቸው ተጉዘው ነው፡፡

የአሜሪካ ምክር ቤት ካፒቶል ሲደርሱ ብዙ ሕዝብ ሲጠብቃቸው ነበር፡፡

ንግግራቸውንም አዘጋጅተው ነበር፡፡ ነገር ግን ድምጻቸው በጣም ድክም ያለ ስለነበረ ንግግራቸውን ሊሰማ የቻለው በጣም ጥቂት ሰው እንደነበር ታሪክ መዝግቦታል፡፡

ቢሆንም ዛሬ ያ የቶማስ ጄፈርሰን የበዓለ ሲመት ንግግር በአሜሪካዊያን ዘንድ በሚገባ ይታወቃል፡፡ በምርጫ ዘመቻው ወቅት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የነበረውን አስቀያሚ ጭቅጭቅ ለማርገብ ያደረጉት ንግግር አድናቆት አትርፏል፡፡

ሆኖም የምርጫው ዘመቻው ጭቅጭቅ የተወው አስከፊ ገጽታ ቀጠለ እና ከጄፈርሰን ጋራ የተፎካከሩት ከሳቸው በፊት የነበሩት ፕሬዚደንት ጆን አዳምስ በጄፈርሰን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ቀሩ፡፡ በዓለ ሲመቱ ነገ ሊሆን በዋዜማው ምሽቱ ላይ ጓዛቸውን ጠቅልለው ከዋይት ሐውስ ወጡ እና ወደቦስተን ተመለሱ፡፡

ዊሊያም ሄንሪ ሃሪሰን በ1841 ዓ.ም

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1841 የዘጠነኛው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሄንሪ ሃሪሰን የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓት ታሪክ ሳይወሳ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ ተወሳ ለማለት አይቻልም፡፡ ሲመረጡ የ68 ዓመት ሰው የነበሩት ዊሊያም ሃሪሰን በዘመኑ ከነበሩት ፕሬዝደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ነበሩ፡፡

ታዲያ እንደሚባለው በፕሬዝደንትነት ለማገልገል ጠንካራ መሆናቸውን በጣም ረጅም ንግግር በማድረግ ለማሳየት አስበው ነው ይባላል ኃይለኛ ቅዝቃዜ በነበረበት የበዓለ ሲመታቸው ዕለት ጭንቅላታቸውን በብርድ ቆብ ሳይሸፍኑ ካፖርትም ሳይደርቡ ቆመው ረጅሙን ንግግራቸውን አደረጉ፡፡ ያ በሆነ በወሩ አዲሱ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሃሪሰን ታምመው ሞቱ፡፡

ሥልጣን ላይ ሆነው ሕይወታቸው ያለፈ የመጀመሪያ ፕሬዝደንት ናቸው፡፡ ሐኪማቸው ፕሬዝደንቱን ለሕልፈት የዳረጋቸው የሳምባ ምች ወይም ኒውሞኒያ ነው ብለዋል፡፡፡በተለምዶ ግን ብዙዎች ረጅሙ ንግግራቸው የገደላቸው ፕሬዚደንት ይሏቸዋል፡፡

የሐሪሰን አሟሟት እ አ አ በ2014 ምርምር ተደርጎበት ነበር፡፡ ተመራማሪዎቹ ጄን ሜክሂዩ እና ፊሊፕ ሜክውላክ ሃሪሰን የሞቱት በሳምባ ሕመም ሳይሆን በሌላ ምክንያት ነው ይላሉ፡፡ እነሱ እንደሚሉት ሃሪሰን የታመሙት ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ ወዲያውኑ ሳይሆን ቆይተው ከሦስት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ የነበራቸውም የሕመም ስሜት ድካም እና ጭንቀት እንጂ ሳምባቸው ላይ እንዳልነበረ ይናገራሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ በጊዜው ዋሽንግተን ዲሲ ጥሩ የፍሳሽ ማስወገጃ አገልግሎት ስላልነበራት የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ከኋይት ሐውስ በቅርብ ርቀት ሜዳ ላይ ይፈስ ስለነበረ ምናልባት በባክቴሪያ የተበከለ ውሃ ጠጥተው ሳይታመሙ አልቀሩም ሲሉ ተመራማሪዎቹ ድምዳሜአቸውን ኒው ዮርክ ታይምስ ላይ አስነብበዋል፡፡

የ30ኛው ፕሬዚደንት ካልቭን ኩሊጅ በ1923 ዓ.ም

ስለ ፕሬዝደንቶች በዓለ ሲመት ሲወሳ ታዲያ የሁሉም የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት አይረሴ ነው ማለት አይደለም፡፡ የ30ኛው ፕሬዚደንት ካልቭን ኩሊጅ በዓለ ሲመት ቀዝቀዝ ባለ ድባብ ከተከናወኑት ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኩሊጅ እ አ አ በ1923 ነሃሴ ወር ውስጥ ብዙም የሥራ ኃላፊነት ስላልነበረባቸው ቨርሞንት ወደሚኖሩት
ቤተሰቦቻቸው ቤት ለዕረፍት ሄደው ነበር፡፡

አንድ ቀን ሌሊት በተኙበት አባታቸው ይቀሰቅሷቸው እና ቴሌግራም እንደተላከላቸው ይነግሯቸዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ ዋረን ሀርዲንግ አርፈዋል የሚል መርዶ የያዘ ቴሌግራም ነበር፡፡ በዚያ ኩሊጅ ፕሬዝደንት ሆኑ፡፡

ኩሊጅ በግል ማስታወሻቸው ላይ ይህንን ባውቅኩ ጊዜ መጀመሪያ ተነስቼ ቆምኩ እና ጸለይኩ፡፡ ከዚያም ከሕገ መንግሥቱ ውስጥ የፕሬዝደንት ቃለ መሐላው ያለበትን አውጥቼ ለአባቴ ያዘው ብዬ ሰጠሁት፡፡ ከዚያም ተመልሼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ብለው እንደጻፉ ተመልክቷል፡፡

ሊንደን ጆንሰን 1963 ዓ.ም

ቀደም ሲል ከተነገረው በተጻራሪ ድንገተኛ ሐዘን የተመላበትን ሊንደን ጆንሰን 36ኛው ፕሬዚደንት ሆነው ቃለ መሓላ የፈጸሙበትን ቀን አይረሴ ነው፡፡ ጆንሰን ቃለ መሃላ የፈጸሙት ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በሰው እጅ በጥይት ከተገደሉ ከአንድ ሰዓት ተኩል በኃላ ነበር፡፡
ጆንሰን በፕሬዝደንታዊው አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋን ውስጥ ቀኝ አጃቸውን ከፍ አድርገው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የተነሳው ፎቶግራፍ ታሪኩን ይናገራል፡፡ በስተቀኛቸው ባለቤታቸው በስተግራቸው የሟቹ ፕሬዚደንት ባለቤት ጃኪ ኬኔዲ አጅበዋቸው ይታያሉ፡፡


Репост из: ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus
የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ


በከባድ ብርድ ምክኒያት የትረምፕ ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት በቤት ውስጥ እንዲከናወን ተወሰነ
--------

የአሜሪካ ተመራጭ ኘሬዝደንቶች ከቤት ውጭ በሚካሄድ በዓለ ሲመት ስነስርዓት ነበር ቃለ መሃላ የሚፈፅሙት።

አሁን ግን በዋሽንግተን ባለው ከባድ ብርድ ምክንያት የዶናልድ ትራምኘ የቃለ መሃላ ስነስርዓት በምክር ቤቱ ሕንፃ ካፒቶል ሂል እንዲከናወን ተወሰኗል።

ቃለ መሃለው በሚፈፀምበት የፊታችን ሰኞ በዋሽንግተን እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ይኖራል በመባሉ ነው የተመራጩ ፕሬዚደንት ቃለ መሃላ በምክር ቤቱ ውስጥ እንዲከናወን የተወሰነው።


የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የቀድሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጊ የትራምፕን መምጣት ተከትሎ ወደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

ቲቦር ናጊ የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መወገድ አለበት በሚል የሚታወቁ ሲሆን በቅርቡ የሶሪያው መሪ በሽር አልአሳድን መውደቅ ተከትሎ ኢሳያስም የአሳድ እጣፈንታ ይጠብቀዋል በማለት በማህበራዊ ሚዲያቸው መለጠፋቸው ይታወሳል።

የቀድሞ በ ኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ቲቦር ናጊ እንደ ህዳሴው ግድብ በመሳሰሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ ጎን በመሰለፍ የሚታወቁ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ውዴታም በአደባባይ የሚገልፁ ጉምቱ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሲሆኑ ከወዲሁ ኢሳያስና ግብፅን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ዜና መሆኑ ተዘግቧል ።


የአሜሪካው ተመራጭ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሌጋሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በመምራት በበዓለ ስመታቸው እንዲገኙ መጋበዛቸው ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የምታደሙ የአፍሪካ መሪዎችንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ስም ዝርዝር በአዘጋጆቹ በኩል ይፋ ተደርጓል።

እንደ ደይሊትራስ ዘገባ ግብዣው በጥር 13 ቀን 2025 ለወጣቱ የናይጄሪያ የንግድ ሥራ መሪ ዶ/ር ኡዞቹክ በተላከ ደብዳቤ “ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕን በማክበር የመድብለ ባህላዊ ጥምረት የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ የምረቃ ቦል አስተናጋጅ ኮሚቴን በመወከል እንዲገኙ ስንጋብዝ በታላቅ ክብር ነው ይላል ብሏል።

ይህ ታላቅ ዝግጅት በጥር 20፣ 2025 በዋሽንግተን የሚካሄድ ሲሆን በማዳም ፍራንያ ኢ ካብራል ሩዪዝ መሪነት ከአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት በቀረበው ሀሳብ እንደተገለጸው ላበረከቱት ልዩ አስተዋፅዖ እና አመራር እውቅና በመስጠት፣ በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ በመገኘታችን ታላቅ ክብር እንሰጣለን ብሏል።

በዚሁም የወቅቱን የአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በዩኤስ ፕሬዝዳንታዊ የትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የሚመሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደሆኑም ዘገባው ጠቅሷል።
WT


የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክቶክ የብሔራዊ ጸጥታ አደጋ በመደቀኑ እንዲዘጋ ካልሆነም እዲሸጥ ለሚጠይቀው የፌደራል ህግ ድጋፍ መስጠቱ ተሰማ፡፡
በፍርድ ቤቱ ዛሬ በተካሄደው የቃል ክርክር የቻይናው ባይትዳንስ ንብረት የሆነው ቲክቶክ እንዲታገድ በሙሉ የድምጽ ድጋፍ ማሳለፉን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
በአሜሪካ ከ170 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚ ያለው ቲክቶክ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ ይሰጣል በሚል ነው እንዲሸጥ ካልሆነም እንዲዘጋ የሚል ክስ የቀረበበት።
ዛሬ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ቲክቶክ ከእሁድ ጀምሮ የሚታገድ ሲሆን እግዱ ተግባራዊ ሲሆን መተግበሪያውን አዳዲስ ተጠቃሚዎች ማውረድ እንደማይችሉ እና ነባር ተጠቃሚዎች ደግሞ ማዘመን (አፕዴት) እንደማችሉ በመረጃው ተገልጿል።
ዶናልድ ትራምፕ የቲክቶክን ጠቀሜታ መገንዘባቸውና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን እንዲያዘገይ ጠይቀው የነበረ ሲሆን ጉዳዩን በድርድር እፈታዋለሁ ማለታቸው ይታወሳል።
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 9 ዳኞች ያሉት ሲሆን የሀገሪቱን ህገ መንግስት የሚጻረሩ ጉዳዮችን የመስማት፣ ለህግ ትርጓሜ የመስጠት፣ የሲቪል መብቶችን የማስጠበቅ፣ በግዛቶች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን የመፍታት፣ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮች የመምራት ስልጣን አለው፡፡


Репост из: Teddy Hawassa
(ቴዲ ሀዋሳ)

የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ? የመንጣቱ ምክንያት ምንድን ነው?

የጥገና እድሳት እየተከናወለት ያለው ታሪካዊው የፋሲል ግንብ በቅርቡ ይፋ መደረጉን ተከትሎ መወዛገቢያ መሆኑ አልቀረም። ታሪካዊው ሽሯሟ ቀለም ያለው የፋሲል ግንብ ቀለሙ ነጥቶ መታየቱ ለበርካታ መላምት ክፍት እንዲሆን አድርጎታል።

የታሪካዊው ግንብ ቀለም ለዘመናት ከሚታወቅበት ተለውጦ ለምን ነጣ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳም ምክንያት ሆኗል።

ለዚህ ምላሽ የሚሰጡት በጥገና እድሳቱ በአማካሪነት እንዲሁም በጥናት የተሳተፉት አንጋፋው አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ የፋሲል ግንብ የተሠራበትን የግንባታ ግብዓት በመጥቀስ ነው።

የፋሲል ግንብ ህንጻ ከመቶ ዓመታት በፊት ሲገነባ በአነስተኛ ድንጋዮች እና በኖራ ሲሆን፣ ለረጅም ዓመታት ዝናብ፣ በፀሐይ እና በተፈጥሯዊ ሂደቶች ውስጥ ሲያልፍ በርካቶች የሚያውቁትን ይሄንን "ሽሯማ" መልክ እንዳመጣ ፋሲል ጊዮርጊስ ይናገራሉ።

አሁን እድሳቱ የተደረገበት ኖራ አዲስ በመሆኑ ቀለሙ ነጣ እንዳለም ያስረዳሉ ይላሉ።

ፋሲል እንደሚገልጹት የእድሳት ሥራው የተከናወነው የፋሲል ግንብ በመጀመሪያ በተገነባበት ማቴሪያል (ቁስ) በዋናነት በኖራ እና በድንጋይ ነው።

"የቅርስ አጠባበቅ ሕግን በተከተለ መልክ ነው የተሠራው" ይላሉ።

"የኖራው አዲስ መሆን ብቻ ይሄንን ነጣ ያለ ቀለም አምጥቷል" የሚሉት አርክቴክቱ ፋሲል የኖራ እና የድንጋይ መልኩ ከተወሰነ ዓመታት በኋላ ወደ ድሮው መልኩ ይመለሳል ይላሉ።

ልዩነቱ አዲስ የመሆን እና የማርጀት ጉዳይ ነው ሲሉም አጽንኦት ይሰጣሉ።

የፋሲል ግንብ መጀመሪያ ሲሠራ ኖራው ለብዙ ወራት ወይም ለዓመታት ተቀብሮ የነበረ ሲሆን፣ አሁንም ሲታደስ መነሻውን ተከትሎ ኖራው ለበርካታ ጊዜያት እንዲቀበር ተደርጎ ጥገናው መካሄዱን ጠቅሰዋል።

ቅርሶች በተፈጥሮ፣ በፀሐይ፣ በዝናብ፣ በአቧራ ምክንያት በዓመታት ቀለማቸው እየተቀየረ የሚሄድ ሲሆን፣ ይሄኛውም ከዓመታት በኋላ የሚታወቀውን ቀለም ይይዛል ይላሉ።

በዓለም አቀፉ የቅርስ ጥገና ሕግ መሠረት ዋነኛው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በተሠራበት ቁስ (ማቴሪያል) ታድሷል ወይ? የሚለው ነው የሚሉት ፋሲል፤ በተሠራበት ድንጋይ እና ኖራ መልሶ መጠገኑ ዋናው ነገር እንደሆነ አስረድተዋል።

"ይህንንም በትክክል መሥራቱን አረጋግጠናል" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ።

በአንዳንድ ሁኔታዎች የድሮ ቀለሙን ለማምጣት ለመልክ ሲባል ኬሚካል እንደሚቀላቀል የሚጠቅሱት አርክቴክት ፋሲል፤ እነዚህ ግን ኬሚካል ነክ ነገሮች ስለሆኑ ያልታሰበ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

"ቀለሙ እንደ ድሮው ቢመስል እንወድ ነበር፤ ሆኖም ለቀለም ተብለው የሚጨመሩ ነገሮች ያልታሰበ አደጋን በቅርስ ላይ ያመጣሉ" በማለት ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

አክለውም በዓለም የቅርስ አጠባበቅ ደረጃ ዋነኛው ነገር ቅድሚያ የሚሰጠው የመነሻ ሃሳቡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኖራው ትክክለኛ እና አስተማማኝ በመሆኑ የጥንቱ እንደያዘ የጥገና እድሳቱ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

"መነሻውን ሳይለቅ ጥርሳችንን ነክሰን የሠራንበት ነው" ሲሉ የሚናገሩት ፋሲል፣ የቀደመ መልኩ በጊዜ ብዛት ይመጣል ሲሉ የነበረው ገጽታ በጊዜ ሂደት እንደሚመለስ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ታዲያ ይሄ በርካቶች በቀደመ መልኩ (ሽሯሟ) መልክ የሚያውቁት የፋሲል ግንብ መቼ ተመልሶ ይመጣ ይሆን? በሚል ቢቢሲ አርክቴክቱን ጠይቋአዋል።

ዝናብ ሲመታው እና የአየር ሁኔታዎች ሲፈራረቁበት እየተቀየረ ይሄዳል የሚሉት ፋሲል፤ ህንጻው ወደ ቀደመ ቀለሙ ለመመለስም ከሦስት እስከ አራት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ፋሲል እንደሚገልጹት "አንዳንድ ቦታ ላይ በጣም የጠቋቆሩ [የግንቡ አናት ላይ] አካላት ነበሩ" ድንጋዮቹ ወደ ነበሩበት ለመመለስ እስከ አምስት ዓመት ድረስ የሚደርስ ወይም የግንቡ አናት ላይ ያሉትን ጠቆር ያሉትን የቀደመ ገጽታ ለማምጣት ከዚያ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድ ያስረዳሉ።


ከሃሰተኛ ምስል ይጠንቀቁ።
የሎስ አንጀለስን አካባቢ ባወደመው ሁለት ትላልቅ ሰደድ እሳት 11 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ባለሥልጣናቱ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ተጎጂዎችን እንደሚያገኙ ይጠብቃሉ።
በጥቂት አጋጣሚዎች፣ ጓደኞች እና ቤተሰብ ስልክ ላይ ነበሩ እና የሚወዷቸውን የመጨረሻ ደቂቃዎች አንድ ላይ ማሰባሰብ ችለዋል።  አንቶኒ ሚቼል መስመሩ ከመጥፋቱ በፊት "እሳቱ በጓሮው ውስጥ ነው" ብላ ለልጇ ተናግራለች።  ለሌሎች፣ ተስፋ የቆረጡ ጸሎቶች ወይም እንባዎች በፍፁም አይረሱም።

ፖሊስ በመጪዎቹ ቀናት ተጨማሪ ተጎጂዎችን እንደሚያገኝ ይጠብቃል፣ ስድስት ንቁ እሳቶች አሁንም እየተቃጠሉ እና የነፍስ አድን ሰራተኞች ከ10,000 በላይ ህንፃዎችን አመድ እና ፍርስራሽ በማጣራት ላይ ናቸው።  የሎስ አንጀለስ ካውንቲ የህክምና መርማሪ ጽህፈት ቤት “በእሳት ሁኔታዎች እና የደህንነት ስጋቶች” ምክንያት የተወሰኑ አካላትን መለየት ብዙ ሳምንታት ሊወስድ ይችላል።  የእሱ ድረ-ገጽ እንዲህ ይላል፡- “እባክዎ እንዲሁም እንደ የጣት አሻራ እና የእይታ መታወቂያ ያሉ ባህላዊ የመለያ ዘዴዎች ላይገኙ እንደሚችሉ እና እነዚህን ሟቾች ለመለየት ተጨማሪ ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

የሎስ አንጀለስ አውዳሚ ሰደድ
እሳት ሲስፋፋ አንዳንድ ተጎጂዎች የማያቋርጥ እሳቱን ለመመለስ ሲሞክሩ ሞቱ።  ሌሎች አረጋውያን ወይም አካል ጉዳተኞች ከአልጋው ላይ ታፍነው ሞተዋል፣ከሚያቃጥል ሙቀት ማምለጥ አልቻሉም።  አንዳንዶች ሌሎችን ለመርዳት ሲሉ ሞተዋል። ያሳዝናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ ሃሰተኛ ፎቶዎችና ምስሎች እየተሰራጩ ሲሆን እነዚህም ምስሎች ሐሰኛ ናቸው።


https://www.tiktok.com/t/ZTYKwc942/
አንተነህ is LIVE | TikTok
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ወደ አዲስ አበባ. | Check out አንተነህ LIVE videos on TikTok! Watch, follow, and discover the latest content from አንተነህ.


Репост из: FBC (Fana Broadcasting Corporate)
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮዽያ መጡ እላለሁ ሲሉ ገልጸዋል።








የኦሮሞ ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ አሳትሞ ያሰራጨውን "አልጸጸትም" የተሰኘ መጽሐፉን PDF ሙሉውን በነጻ አሰራጭቶታል። የማንበብ ፍላጎቱ ላላችሁ ሼር አድርገነዋል። መልካም ንባብ።




የኦሮሞ ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ አሳትሞ ያሰራጨውን "አልጸጸትም" የተሰኘ መጽሐፉን PDF ሙሉውን በነጻ አሰራጭቶታል። የማንበብ ፍላጎቱ ላላችሁ ሼር አድርገነዋል። መልካም ንባብ።


#ኢትዮጵያ #ሶማሊያ

ኢትዩጲያ እና ሶማሊያ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን አሳወቁ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ስለመወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል ተብሏል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር ይገባልም ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጻል፡፡

Показано 19 последних публикаций.