ህዋሓት ከፍቶት በነበረው ጦርነት በሳምሪዎች ንፁህን ከተጨፈጨፉበት ማይካድራ መነሻዉን ያደረግ ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሰር ውሏል። መነሻውን ማይካድራ መዳረሻዉን ደግሞ ሳንጃ በሚባል ስፍራ ያደረገ አንድ የቤት ተሸከርካሪ አውቶሞቢል ውስጥ በድብቅና በስውር 3 ብሬኖች አንድ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ለማጓጓዝ የሞከሩ አዘዋዋሪዎች ገና ከጅምሩ የንስር ዓይን ባላቸው ሰላዮች ክትትል ስር ስለነበሩ ለፀጥታ አካላት በተሰጠ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ በፀጥታ አካላት እጅ የወደቁት እና በቁጥጥር ሰር የዋሉት ሁለት ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ደብቀው ለማስተላለፍ ከሞከሯቸው መሳሪያዎች ጋር መሆኑን ከታማኝ ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል።