በሙሐዘ ጥበባት Daniel Kibret
በድሮ ዘመን ሙንጣዝ የሚባል ወጠጤ ነበረ። አንዷን ልጅ በግድ ካላገባሁ ብሎ ሠፈር በጠበጠ። እሷ ደግሞ ሞቼ እገኛለሁ አላገባውም። አይመጥነኝም አለች። ዘመዶቿም በግድ አይሆንም አሉት።
ሙንጣዝም የጣልያን ዘመን ቆመህ ጠብቀኝ ይዞ ሸፈተ። እሱ በረሃ ገባ ልጂቱም አገባች።
በዚህም በዚያም እየሄደ ይበጠብጥ ጀመር። ወንድሞቿም ዙሪያውን ከብበው ከጫካ አላስወጣው አሉት።
ልጂቱም ወለደች።
ሙንጣዝም ያደዘድዝ ጀመር።
ልጂቱም ልጇን አሳድጋ ዳረች።
ሙንጣዝም ከብት ይዘርፋል፤ ሰው ይገፋል።
የልጅ ልጇም በተራዋ ልጇን አሳድጋ ዳረች።
ሙንጣዝም በንዴት ሰው ይገድላል፤ እሷን ለማግባት ሲል ሕጻናት ይደፍራል።
የልጂቱም የልጅ ልጇ በተራዋ ወለደች።
ሙንጣዝም ይፎክራል፤ ይረብሻል፤ ይበጠብጣል። መጣሁ፤ ደረስኩ፤ ላገባት ነው ይላል፡፡
የልጂቱ የልጅ፣ ልጅ፣ ልጇ አገባች።
ሙንጣዝ አረረ፤ ደበነ፤ ጎፈየ፡፡ ትግሉን እየረሳ በረሃ ያገኛቸውን ሦስት አራት ሚስቶች አገባ፡፡
ሙንጣዝም ለሚስቶቹ “እናንተን ያገባሁት እርሷን ለማግባት ብዬ ነው” አዠብሎ ደሰኮረ፡፡
የልጂቱ የልጅ፣ ልጅ፣ ልጇ ወለደች።
የልጅ ልጅ፣ ልጆችም እንዲህ ብለው ዘፈኑበት
ሙንጣዜ ሙንጣዜ የኔ ድብልብል
ጥጆቹ የሚያሥሩት የብረት ቃጭል