Temari Podcast - ተማሪ ፖድካስት


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Образование


የዩቲዩብ ቻናላችን መቀላቀል አትርሱ 👇👇👇
https://youtube.com/@temari_podcast?si=--vADFvenliwbocx

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


በድጋሚ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበትን አድራሻ https://register.eaes.et/Online በመጠቀም በበየነ መረብ መመዝገብ ይችላሉ።

ይህ የበይነ መረብ ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከልማግኘት ይችላሉ።

ከዚህ መልዕክት ጋር የተያያዙ መረጃዎች ተመዝገቢዎች በቀላሉ መመዝገብ እንዲችሉ አጋዥ ስለሆኑ ተጠቀሙባቸው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@Temari_podcast
@Temari_podcast


#MattuUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፈኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ልብስ

Note:
የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-B የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ምዝገባችሁ በበደሌ ካምፖስ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

@Temari_podcast
@Temari_podcast




#WolloUniversity

በ2017 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደሴ ግቢ፣
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ኮምቦልቻ ግቢ።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@Temari_podcast


#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ የ PhD ፕሮግራም መስጠት ጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው PhD in Coffee Science የመጀመሪያ ቀን ትምህርት የመጀመሪያ Class በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ታሪክ በቡና ሳይንስ የ PhD ፕሮግራም በመጀመር ቀዳሚው ዩኒቨርሲቲ ሆኗል።

በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸው 34 ተማሪዎች ባለፈው ሰኔ ያስመረቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በመስኩ በማስተርስ መርሐግብር ተማሪዎችን በማሰልጠንም ላይ ይገኛል።

@Temari_podcast






ዛሬ December 22 አለም አቀፍ የአጭር ሰዎች ቀን ነው።

አጭር ቁመት ያላቸው ከእንደ ማህተመ ጋንዲ ካሉ ታዋቂ መሪዎች እስከ ሲሞን ቢልስ ያሉ ታዋቂ አትሌቶች ታላቅነት በቁመት እንደማይለካ የሚያረጋግጡልን ምሳሌዎቻችን ናቸው።

ይህን ለአጭር ጓደኞቻችሁ አካፍሉ እና ምን ያህል ኃያላን እንደሆኑ አስታውሷቸው።



@Temari_podcast


የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT)

የ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

👉For Registration: https://ngat.ethernet.edu.et/login

@Temari_podcast


#Wolaita_Sodo_University

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፡-

በ2017 የትምህርት ዘመን ከኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን ታህሳስ 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን እናስታዉቃለን፡፡

👉 ማሳሰቢያ 1

1.ምዝገባ (በአካል ቀርበው) ታህሳስ 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ.ም
2.አጠቃላይ ገለፃ (orientation) ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
3.ትምህርት የሚጀመረው ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

👉 ማሳሰቢያ 2

ሁሉም ተማሪዎች ሲመጡ፡-
1.የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት (ዋናው እና ኮፒው)
2.ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ
3.አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

👉 ማሳሰቢያ 3
ከA አልፋበት አስከ Z ድረስ የስማችሁን የመጀመሪያ ፊደል በማየት በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ የተመደባችሁበትን ካምፓስ ከምስሉ በመለየት እንድትመዘገቡ፣ ገለፃ ላይ እንድትሳተፉ እና ትምህርት እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲው ያሳስባል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

👉 የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

@Temari_podcast
@Temari_podcast


በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

📘 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት  ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል። የምዝገባ ቦታለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

📘 ቦረና ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

📘 ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡


#BorenaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast


#DiredawaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast


#UniversityofGonder

በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት 👉 ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል።


የምዝገባ ቦታ፡- ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast






#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@Temari_podcast
@Temari_podcast


የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና

የኦሮሚያ ት/ት ቢሮ ላይ ከ4 ቀን በፊት እንደጻፈው በሰማያዊ ከለር የተከበበት
"የዘንድሮ ፈተና
🔹 Grade 9 & 10: old curriculum
🔹 Grade 11 & 12: new curriculum
እንደሆነ እና ተማሪዎች ለእዚህ እንዲያዘጋጁ" ተናግሯል

@Temari_podcast
@Temari_podcast


Upcoming video ቻናላችን ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ጠብቁ 👇👇

https://youtube.com/@freshman_tricks?si=S-CjNc7qdA_UMxv4

Показано 19 последних публикаций.