#ዜና: በኢትዮጵያ ሲሰለጠኑ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አባላት ስልጠናቸውን አጠናቀው መመረቃቸው ተገለጸ
ስልጠና ሲሰጣቸው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አዳዲስ ምልምል አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ማሰልጠኛ ማዕከል ስልጠናቸውን ጨርሰው መመረቃቸው ተገለጸ።
ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የተመረቁት የሶማሊንድ ወታደሮች በኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ በተከታታይ ዙር የተጠናከረ ስልጠና ሲሰጣቸው ከነበሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት መካከል መሆናቸውን እና 8ኛ ዙር ሰልጣኞች መሆናቸውን ሆርን ዲፕሎማት በድረገጹ አስነብቧል።
በታላቅ ድምቀት በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት መታደማቸውን የጠቆመው ዘገባው በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር አጉልቶ ያሳየ ነው መባሉን አስታውቋል።
በምረቃ ስነስርአቱ ላይ በክብር ከታደሙት እንግዶች መካከል የሶማሌላንድ ብሄራዊ ጦር አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኑህ እስማኤል ታኒ ይገኙበታል ያለው የድረገጹ ዘገባ የጦር አዛዡ በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ መገኘት ሶማሌላንድ ብሔራዊ የመከላከያ አቅሟን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ያሳየ ነው ነው ሲል ገልጿል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የሶማሊላንድ ወታደሮች በተከታታይ በኢትዮጵያ ስልጠና መውሰዳቸውንም አውስቷል።
@TheNationPost