ሰሞኑን the living legend ክርስቲያኖ ሮናልዶ ስለ complete player ከተናገረው ንግግር በመነሳት በውጪም በውስጥም social midia ላይ ብዙ እየተባለ ነው ፣ ስለ complete player በእኔ መረዳት የሆነ ነገር ልበል መሰለኝ ፣
በእግር ኳስ ግብ ጠባቂዎችን ትተን የon field ተጫዋቾችን ባብዛኛው የመከላከል እና የማጥቃት ብለን ልንከፍላቸው እንችላለን ፣ አማካዩች ሆነው በዋናነት ተቀዳሚ ተግባራቸው ማጥቃት የሆነ አማካዩች ይኖራሉ እንዲሁም መከላከል ዋነኛ ስራቸው የሆነም ይኖራሉ ሁለቱንም በእኩል ባላንስ አድርገው የሚፈፅሙ ብዙም ባይሆኑም ይኖራሉ ፣ ተከላካዩች ዋነኛ ስራቸው መከላከል ነው አጥቂዎች ደግሞ ማጥቃት ነው ስለዚህ ለጊዜው ግብ ጠባቂዎችን ትተን ስለ on field ተጫዋቾች እናወራለን ፣ የcomplete player debate ሁሌም ያለው የማጥቃት ተጫዋቾች ጋር ብቻ ስለሆነ ለዛሬ ሌሎቹን ትተን እነሱ ጋር ብቻ እናተኩር ፣
ስለማጥቃት ተጫዋች ስናነሳ የማጥቃት ተጫዋቾች ምን ምን skill ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን ማየት ያስፈልጋል ፣
የመፍጠር ( creativity) ማለትም ከምንም ነገር ለቡድናቸው የግብ እድል ሊፈጥር የሚችል አዎንታዊ impact የሚፈጥር ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ ፣ Play making ይሄም ከላይኛው ጋር ተቀራራቢ ቢሆንም የበለጠ የቡድንን የማጥቃት ቅርፅ እና ፍሰትን የሚወስኑ እንቅስቃሴዎችን ለሚከውኑ ተጫዋቾች የምንሰጠው ነው ባብዛኛው እኚህ ተጫዋቾች አማካዩች ናቸው አንዳንዴ 10 ቁጥር ወይም 9 ተኩል ወይም 8 ተኩል ተጫዋቾች ይሄን ሚና ይወጣሉ፣
Passer እግር ኳስ በዋናነት የሚከወንበት skill ይሄ ነው የማጥቃት ተጫዋቾች ደግሞ ይሄ የበለጠ ያስፈልጋቸዋል ፣ Dribbler ይሄ ከሁሉም የበለጠ የሚያስፈልገው ለማጥቃት ተጫዋቾች ነው በተለይ successful dribbler ከሆኑ ቡድናቸውን ይጠቅማሉ፣
Chance created ወይም Assist ቡድናቸው ለሚያስቆጥረው ጎል የመጨረሻ እድል ፈጣሪ ወይም ከመጨረሻው በፊት ያለ እድልን የሚያመቻቹ .. final assist የሚያደርጉ የበለጠ creditቱን ይወስዳሉ ፣ Goal scorers ይሄኛውን ትንሽ ሰፋ አድርገን ልናየው እንችላለን ከክፍት እንቅስቃሴ ..ከቆመ ኳስ ..በግል ጥረት ..ከርቀት …ከቅርብ በtap in ..በጭንቅላት እያልን ልንጠቅስ እንችላለን ፣
እንግዲህ እኚህ በዋናነት የማጥቃት ተጫዋቾችንን rate ልናደርግባቸው ከምንችላቸው መለኪያዎች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው ፣ ከእነዚህ የማጥቃት ተጫዋቾች መለኪያነት በመነሳት complete, incomplete, most complete እያል rate ማድረግ እንችላለን ማለት ነው ፣ ወይም Specifically complete striker ፣ complete midfielder እያልን categorize ማረግም እንችላለን.. ከፍ አርገነውም the most complete player ልንልም እንችላለን ፣
የብራዚሉ ሮናልዶን እናንሳ እሱ ለmost complete striker እንደ ምሳሌ ባብዛኞች የሚጠቀስ pure አጥቂ ተጫዋች ነው ፣ ጎል በማንኛውም መልኩ ያስቆጥራል ( በጭንቅላቱ የማስቆጠር ትንሽ ድክመት አለበት ) አንድ አጥቂ ሊኖረው ይገባል ተብሎ የሚታሰበው ክህሎት ሁሉ አለው ተብሎ ይታመናል ፣ ብዙዎች በተራ ጨዋታ የማይሞክሩትን እና ቢሞክሩትም የማይሳካላቸውን ፔዳላዳን በእግራቸው ብቻ መከላከል የሚችሉ ተከላካዩች ላይ ሳይሆን በእግሩም በእጁም መጫወት የተፈቀደለትን በረኛን ለዛውም በታላቁ የአለም ዋንጫ መድረክ አታሎ አልፎ ጎል ለማስቆጠር ሮናልዶን መሆን አለብህ..he is the complete no .9 ፣
አንዳንዶች Complete striker ማለትን ከእንደ ኢንዛጊ አይነቱ በዚህም በዛም ብሎ ጎል ከሚያስቆጥር አጥቂ ጋር ያምታቱታል ፣ ኢንዛጊ በእግሩ ..በግንባሩ ..በሆዱ ..ከፈለክ በቂጡ ሁላ ጎል ያስቆጥርልሃል...ስለ most complete striker ለማወቅ ከፈለግህ ከብራዚሉ ሮናልዶ በላይ define የሚያደርግልህ አታገኝም ፣
Most complete attacking midfielder ጋር ከመጣን ስለ ዚዳን ብዙ ስለተባለ ይቆየን ፣ ስለሱ የተፃፈውን ማንበብ የተባለውን መስማት እና የሱን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ቪድዮችን ማየት በቂ ነው ፣ ባጭሩ ዚዳን ኳስ ይጫወታል ሳይሆን ሜዳ ላይ ይደንሳል ብንል ይቀለናል ፣ በአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ቡፎንን የሚያህል ታላቅ በረኛ ከፊት ለፊቱ ቆሞ በፓኔንካ ( ቺፕ) ፔናሊቲ የማስቆጠር በራስ መተማመንም ሆነ ችሎታ ከዚዳን ውጪ ማን ሊኖረው ይችላል?
ስለ most complete player ካነሳን ተጫዋቹ በአጠቃላይ the most complete offensive player ለመባል ከላይ መጀመሪያ ባነሳናቸው መስፈርቶች ቢያንስ ባብዛኞቹ እጅግ ምርጥ መሆን አለበት ፣ ምርጥነቱ ከምን አንፃር ብለን ከጠየቅን ፣ በቁጥርም ( quantity) በጥራትም (quality) ልንል እንችላለን ፣ መቼም የእግር ኳስ አለም ብዙ ተጫዋቾች አሳይቶናል .. ይሄ ምርጡ የተሟላው ተጫዋች ማነው ?
እኔ እግር ኳስ Artistic ም ስለሆነ ከቁጥርም ባሻገር Eye test እና style of playing የሚባሉ ነገሮች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው ባይ ነኝ ፣ እንደዛም ቢሆን ቁጥሮችም ግን እጅግ ብዙ ዋጋ አላቸው፣ ጎል ማስቆጠርን ብቻ ነጥለን ካየን አለማችን ከገርድ ሙለር በላይ ጎል አስቆጣሪ አይታለች ? አይመስለኝም...almost ከተጫወታቸው ጨዋታዎች እኩል በሚያስብል መልኩ ግብ ያስቆጠረ ጀርመኖቹ Bomber der Nation የሚሉት ጎል አዝናቢ ጨራሽ አጥቂ ነው ፣ በግሉ የወርቅ ጫማ እና የባሎንዶር ያሸነፈ ፣ እንደ ቡድን ቻምፒየንስ ሊግን አውሮፓ ዋንጫን እና የአለም ዋንጫን ያሳካ ነው ፣ ገርድ ሙለር ያለጥርጥር ከምርጦቹ አንዱ ነው ግን ማንም ሰው እሱን አይደለም the most complete player ሊለው ቀርቶ the most complete striker ነው የሚለው ብዙ ሰው አናገኝም ፣ ለምን ? ምክንያቱም ከቁጥርም ባልተናነሰ መልኩ eye test እና stayle of playing እንዲሁም የተሟላ ክህሎት የሚባሉ ነገሮች ስላሉ ፣ ለብዙ ሰው ከገርድ ሙለር ይልቅ የብራዚሉ ሮናልዶ የተሻለው የተሟላ አጥቂ ነው ፣
እስቲ ከላይ በዘረዘርናቸው መስፈርቶች መሰረት Ranking table እናዘጋጅ ፣ ለሁሉም መስፈርቶች የall time list Generate እናድርግ እናም የምንም ጊዜ ምርጦችን top 10 በየመስፈርቱ እንለያቸው ፣
በassist ጎራ እነ ፕላቲኒ ማራዶና ዚዳን ቻቪ ኦዚል ደብረይነ የመሳሰሉትን ታገኛላችሁ ፣ በጎል አስቆጣሪነት እነ ፔሌ ገርድሙለር ክርስቲያኖ የብራዚሎቹ ሮማርዮ እና ሮናልዶ ፣ ቫንባስተን ሆንሪ ሱዋሬዝ ሌዋኣ እያላችሁ ትዘረዝራላችሁ ፣
በእርግጠኝነት ሁሉንም ተጫዋቾች በሚያስብል መልኩ በሁሉም ካትጎሪዎች ውስጥ አታገኙዋቸውም ፣ ምትሃተኛውን ዚዳንን በጎል አስቆጣሪዎች ጎራ የብራዚሉን ክስተቱን ሮናልዶ በአሲስት ጎራ አይደለም እስከ 10 ባለው ደረጃ ቀርቶ እስከ 20 ኛ ብትፈልጉዋቸው አታገኟቸውም ፣
የማጥቃት ተጫዋቾች ምርጥ ናቸው ብለን በምንለካበት category ውስጥ በሁሉም መስፈርት ለዛውም ከላይ ሆኖ ያገኘሀው እሱ ተጫዋች ያለጥርጥር የምንም ጊዜው ምርጡ Complete player ነው
ከሊዮኔል ሜሲ ውጪ ከላይ ያሉት Criteria የሚያሟላ ማንም የለም
✍️
@ebralem09 🔥👏