የተደበቀው ምስጢር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"ጥበብ በኛ ዘንድ ቦታዋ ጥልቅ ነው ዳሩ በጅ የያዙት ወርቅ እንደመዳብ ይቆጠራል"
"ታሪካችንን እንመርምር ቁመን ከሆነ እንደዛፍ ስር ሰደን እንጠንክር ወድቀን ከሆነ መውደቃችንን እንደ ዘር ቆጥረነው እንደገና ሺ ሁነን እናቆጥቁጥ"
ለማንኛውም አስተያየት
@Yibekal16
Join us
🌚 @TibebeEthiopia 🌚
✍ "ሴማዊ"
"ሐበሻዊ" ✍
🌚

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


"...አዕምሮ ማለት በእግዚአብሔር አርአያ ከተፈጠረች ከነፍስ ባሕርይ የሚገኝ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና አዕምሮህን በክፋት ሃሳብ ቦታ ሁሉ እየበተንክ ለከንቱ ስራ የጨረሰክው እንደሆነ ጌታው አምኖ የሰጠውን ወርቅ ላዝማሪ ፣ ለዘዋሪ ፣ ለመሸታ ፣ ለጨዋታ እያደረገ ጨርሶ እንደሚቀጣ እብድ ተቆጥረህ ወደ እግዚአብሔር ቅጣት እንዳታልፍ አዕምሮህን ለክፋት ስራ እንዳታባክን ተጠንቀቅ..

...ሃሳብህ ብዙ የሚመኝ አንድን ይዞ የማይሰራ ሲሆንብህ ሰይጣን በጎ ስራ እንዳትሰራ በጥበብ ሰንሰለቱ እንዳሰረህ ዕወቅ ስለዚህ አንተ አንድ ሁነህ የሀሳብህን ልጎም በየስፍራው አትልቀቅ...

..እምነት ያለው ብርቱ የተባለው ሰው የሚስትበት ከንቱ ሃሳብ ከትሩፋት ስራዬ እጠቀማለሁ ማለቱ ነው ይህም ትልቅ ትምክህት ነው በአምላክ ቸርነት እንጂ የትሩፋቱ ስራው እና ዕውቀቱ ለንፅህና ዋጋው አይደለምና ለሰው የሚጠቅመው በቸርነቱ መታመን ነው..."

ከልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ
"ፍኖተ አእምሮ" መፅሐፍ የተወሰደ ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


የኛ ታላቅ ክብር የሚመጣው ባለመውደቅ ሳይሆን ነገር ግን ከውድቀታችን ደጋግመን በመነሳት ነው ።
(ገፅ 419)

መልካሙን መንገድ ማወቅ አንድ ነገር ነው በዚያ ላይ ለመሄድ መቻል ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው ።
(ገፅ423)

ክፉውን ማየትና ማዳመጥ የክፋት መጀመሪያ ነውና ተጠንቀቁ ።
(ገፅ 419)

ከ "ጥበብ ከጲላጦስ" መፅሐፍ የተወሰደ ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


ቃላትን ለመመስረት ፊደላትን አዋቅረን ስንጽፍ በተለምዶ ትክክል የሚመስሉን እና ትክክለኛ አፃፃፋቸው ከብዙዎቹ በጥቂቱ እነሆ !!

ሀሳብ - ሐሳብ
አሀዱ - አሐዱ
ስርዓት - ሥርዓት
ምስራቅ - ምሥራቅ
ስልጣን - ሥልጣን
እለት - ዕለት
ትንሳኤ - ትንሣኤ
ማህተም - ማኀተም
ህይወት - ሕይወት
ባህሪ - ባሕርይ
ሀረግ - ሐረግ
ሃይል - ኃይል
አውድ - ዓውድ
እፅ - ዕፅ
ፍትህ - ፍትሕ
ህግ - ሕግ
ንጉስ - ንጉሥ
መንግስት - መንግሥት
አይነት - ዓይነት
ኃጢያት - ኃጢአት
ጸሀይ - ፀሐይ

ብዙ ግዜ ስንጽፍ ትኩረት አንሰጥም ነገር ግን የሰው ልጅ የመጀመሪያ ቋንቋ ከሆነው ግዕዝ የተወጠነው አማርኛ ቋንቋ ከፊደል ፊደል የተለያየ ትርጉም እንዳለው ማስተዋል አለብን ።

ለምሣሌ :- ሥጋ

🔘 ሥጋ :- ብዙ ጊዜ የሆቴሎችና ሥጋ ቤቶች ባነር ላይ እገሌ "ስጋ ቤት" እየተባለ ሲለጠፍ አስተውላለሁ ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው ለእንስሳ ከሆነ "ሥጋ" ነው የሚባለው ስጋ ካልን የሰው ስጋን ነው የሚያመለክተው ።

ከሞላ ጎደል ለምንጠቀማቸው የፊደላት ውህደት (ቃላት) እያስተዋልን ትርጉማቸውን ብንጠቀም እላለሁ ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


"...ኢትዮጵያ የተዘጋጀ ትውልድ ኖሯት አያውቅም ስላለው ኑባሬ ፣ ስላለው ስርዓትና መሪ እንጂ በቀጣይ ምን ዓይነት መሪ ያስፈልጋል ብሎ የሚጠይቅና የሚዘጋጅ ትውልድ የላትም ኢትዮጵያ የሚጋጅ መሪ እንጂ የሚዘጋጅ መሪ ኖሯት አያውቅም ትውልዱ ለታናሽ ነገር ሳይሆን ለታላቅ ነገር ራሱን ማዘጋጀት አለበት ትውልዱ የጋራ ራዕይ፣ የጋራ ህልም ፣ የጋራ ትልም እንዲኖረው ነው ዋናው አላማችን ይህ አላማችን ሟች አለመሆኑን እኛም ባላንጣዎቻችንም ማወቅ አለባቸው እኛም የምንመኘው በተስፋ የተሞላ ብርሃናማ ትውልዱ ነው..."

ዣንቶዣራ ገፅ 125
ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


"...ይልቁንስ ልምከርህ ልጄ ገንዘብ አትውደድ ክፉ ትሆናለህ መጠጥም ሌላም ነገር ከልክ በላይ አትውደድ ወይ ያዋርድሃል ካልሆነ የሰው ፊት ያቆምሃል ሴትም ከልክ በላይ አትውደድ መልካም ካልሆነች ክብርህን ነጥቃ ክብረ ቢስ ታደርግሃለች አደራ የማታከብርህን ሚስት እንዳታገባ በጣም ወዳህ ከምታዋርድህ አክብራህ ባትወድህ ይሻልሃል ስትጣላ ክብረ ነክ ስድብ አትሰዳደብ በስድብ ከምትተዳደፍ ብትደባደብ ይሻልሃል ድንበር አታብዛ በሁሉ ዘራፍ አትበል ግን ለክብርህ ዘብ ሁነው ክብርህ የትም እንዲወድቅ አትፍቀድ የድሎች ሁሉ ምስጢር ክብር ነው..."

ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ
ከክብር መፅሐፍ የተወሰደ

"የድሎች ሁሉ ምስጢር ክብር ነው" ይህ መልዕክት ደግሞ ከ የተደበቀው ምስጢር ነው ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


"...ያላነበበ ጭንቅላትና ጨጓራ አንድ ናቸው ሁለቱም ባዶ ሲሆኑ አሲድ ያመነጫሉ..."

"...የዶሮ ጭንቅላት ሲኖርህ ሐገር ጥራጥሬ ትመስልህና በትነህ ልትቆረጣጥማት ያምርሃል..."

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


"የሔዋን አለመታዘዝ ቋጠሮ በማርያም ታዛዥነት ተፈታ"

ቅዱስ ኤሬንዮስ

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


ፈላስፋው ዲዮጋንን እንዲህ ጠየቁት ።

ሞት እንደምንድን ናት ?

ዲዮጋንም መለሰ
"..ሞትስ ባለጸጎችን የምታስደነግጣቸው ድሆችን የምትናፍቃቸው ናት አለ.."

ከ"አንጋረ ፈላስፋ" መፅሐፍ የተወሰደ ።
አንጋረ ፈላስፋ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት እና በኋላ የነበሩ ፈላስፎች የተናገሯቸውን ጥበባዊ ንግግሮች የያዘ መፅሐፍ ነው ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


"...ያዘነና የተራበ ሕፃን በምድራችን ላይ እስካለ ድረስ ታላቅ ፈጠራ ፣ ትልቁ ግኝት የሚባል ነገር የለም... "

አልበርት አንስታይን

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


የሽቱ ዓይነቶችና ስማቸው

መሳብሔ - ሽቱ
ርሔ - ሽቱ ናስራ
ተፋህ - የሙዝ ሽቱ
ጥፋህ - የትርንጎ ሽቱ
ጵርስቅቅላ - ሽቱ
ቀናንሞ - ሽቱ
አበሞ - የቀረፋ ሽቱ
ፈርከሊስ - ሽቱ
ሰንድሮስ - የዕጣን ሽቱ
ቀናንሞስ - የጠንበለል ሽቱ
አስጳዳቶስ - የእንጨት ሽቱ
አንክሶ - የጥርኝ ሽቱ
ጠርቤንቶስ - የጽድ ሽቱ
ኔቂጥሩ - የሽቱ ውሀ
ሳባ የሽቱ - ተራራ
ሰንሰሪቋት - የሰንደል እንጨት
ደርሰኒ - የመድኃኒት ሽቱ

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


ከግዕዝ የተወሰደው የግሪኩ ፊደል ቅጅ ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


ከግዕዝ የተቀዳው የዕብራውያን ፊደል ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


ብሂለ አበው

"ለጥበቡ ባሕር ድንበር የለውም ለትእዛዙም ይቅርታ መስፈርት ለመንግሥቱ ስፋት ዐቅም የለውም ለአገዛዙም ስፋት ወሰን የለውም ሳይጠይቅ ህሊናን ይመረምራል ሳይመረምር ልቡናን ይፈትናል ያለ መብራት በጨለማ ያለውን ያያል ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተገለጠ ነው"
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ

"ሰው ለሰላም የተሠራ መሣሪያ ነው"
ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ

"ሰው እንደ እምነቱ ይጠቀማል እንደ እምነቱም ይጎዳል"
ሊቀ ትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ

"ወዳጄ ከጸሎት ተለይተህ ክቡር እግዚአብሔርን ርዳኝ ሳትል እግዚአብሔር በጻፋቸው መጻህፍት ያለውን አነበዋለሁ እተረጉማለሁ አትበል በመጽሐፍ ያለውን ትርጓሜ ምሥጢር የማውቅበትን ዕውቀት ስጠኝ በል እንጂ"
ማር ይስሐቅ

"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃዱ የሰዎች ድኅነት መሆኑን ተናግሯል ነገር ግን ሰው መዳንን ካልፈቀደ ራሱን ወደፈቀደበት ይጨምራል"
ባስልዮስ ዘቂሳርያ

"ቅናትን በልቡ ውስጥ የሚሸሽግ ሰው በጭኑ ላይ እባብ የሚያስቀምጥ ሰውን ይመስላል ጭስ ንቦችንን እንደሚያባርር ሁሉ ጥላቻም እውቀትን ከልብ ውስጥ ያባርራል"
ቅዱስ ኤፍሮም ሶርያዊ

"የንስሐ አባት ማለት እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት ሰው ማለት ነው"
አቡነ ሺኖዳ

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


አነበባችሁት ?

ውድ የዚህ ቤተሰብ አባላት እስካሁን ድረስ ሐገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ስላለው መከራ እንዲሁም ይመጣል ስለተባለው ንጉሥ ቴዎድሮስ በገዳማውያን አባቶቻችን በኩል ተነግሯል እየተባልን ብዙ የሰማነው ያነበብነው ፅሑፍ አለ ነገር ግን እውነታውን ማወቅ ከፈለጋችሁ ከላይ ያለውን በ pdf የተለቀቀውን ሰነድ አንብቡት ።

በራሳቸው በአባቶቻችን የእጅ ፅሑፍ የተከተበ ወቅታዊ መልዕክት ነው ።

ለሁሉም አድርሱ ‼️

@TibebeEthiopia


የገዳማውያን አበው መልእክት.pdf
10.2Мб
የገዳማውያን አባቶች መልዕክት ‼️

እባክዎ ተረጋግተው ያንብቡት ❗️

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


መጽሐፍ_ቅዱስ_እና_የሕክምና_ሳይንስ_በመጋቤ_ሐዲስ_ሮዳስ_ታደሰ_@BOOKALEM.pdf
13.6Мб
• መጽሐፍ ቅዱስ እና የሕክምና ሳይንስ
• በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


ስለ ቻናሉ !!

በዚህ ቤተሰባዊ ቻናል የሚተላለፉ ታሪካዊ፣ ጥበባዊ ፣ አነቃቂ ጦማሮች በእኛ ተለይተው ተቆርጠው ተቀንሰው ከባድ ሀሳቦችም ከሆኑ በተቻለ አቅም በደንብ አብራርተን ምቹ በሆነ አቀራረብ ከትበን ነው የምናስተላልፈው የሰው ሀሳብ አናስተላልፍም የሰው ከሆነም ለባለቤቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ እንሰጣለን እንጂ የሰው ጦማር የእኛ እንደሆነ አድረገን አናቀርብም የእኛን ጦማሮች ሌላ አካላት የራሳቸው አስመስለው ሲያስተላልፉ አይተን ታዝበናል ይህ በኛ ቤት የለም የሌላ ከሆነ ባለቤትነት እንሰጣለን ።

በዚህ ቻናል የሚተላለፉ ጦማሮች በኛ የተዘጋጁ እንጂ ከሌላ ኮፒ የተደረጉ አይደሉም ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


ሢመተ ማዕረጋት ወተጸውዖ አስማት

ዓፄ - ኃያል የማይወቀስ ታላቅ የሕዝብ አባት ።
ዕቴጌ - እኅትየ እኅቴ የኛ እመቤት የእኛ ወይዘሮ ።
ልዑል - ተለዓለ ከፍ ከፍ አለ ከፍተኛ ማዕረግና ደረጃ ያለው ንጉስ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ቤተ ሰብእ ወልደ ንጉሥ ።
ልዕልት - ከፍተኛ ማዕረግ ያላት የንጉሣዊያን ቤተ ሰብእ ወለተ ንጉሥ ።

ከዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ "የግዕዝ መማሪያ" መፅሐፍ የተወሰደ ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


🕊 እምነትን መሠረት ያደረገ የጥበብ ሀብት ለእርሱ ለፍቅር ባለቤት በፍቅር ላይ የተመሠረት ኑሮ 🕊

🕊 ኃይል አለ በክብርና በልዕልና የነበረ ፣ ያለ እንዲሁም ዘለዓለም የሚኖር ማንም ቀና ብሎ ለማየት የማይቻለው የማይቋቋመው እነርሱ ግን ገደብ በሌለው ፍቅር ሁል ግዜ ከኃይሉ ጋር አብረው ይውላሉ ያድራሉ 🕊

🕊 በእምነት ላይ የተመሠረተ ነፍስ የምትረካበት ኑሮ 🕊

በረከታቸው እና ምልጃቸው ኢትዮጵያን ይጠብቅ 🙏

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚


💥 በቅርቡ አስገራሚ ነገርን በተከታታይ ይዤላችሁ እቀርባለሁ ይኸውም ረቂቅ የሆነው በቀደምት ኢትዮጵያውያን ብራና የተዳሰሰው "ቀመረ ምጽአት" ነው። በተለይ ከ20 በላይ ምስጢራዊ ጥንታዊ የሒሳብ ቀመሮችን ፈትሸን በጥበብና በማስተዋል ቁልፍ ኮዱን እንከፍታለን።

💥 የግንቦት ወር (May) ለዚህ ቀመር የመጨረሻው መጀመሪያ ሆኖ ለፕላኔቷ ሁሉ ምልክት ሆኖ እንዴት እንደተሰጠ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ካለ ታላቅ ክስተት ጋር በ YouTube Channel ላይ በቀጥታ ሥርጭት አቀርብላችኋለሁ። በዚያው እንድዳስስላችሁ የምትፈልጉት ከርዕሱ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ብቻ ካላችሁ አድርሱኝ።

[እምነት፣ እውነት፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ አመክንዮ ሰውን ነጻ ያወጣሉ]
መ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ


የዩቲዩብ ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉለት ። https://www.youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg

ይሄ ደግሞ የቴሌግራም ቻናሉ ነው ።
@Rodas9

እያበረታታን እየደገፍን ከመምህራችን እውቀትን ፣ ጥበብን እንቅሰም ።

🌚 @TibebeEthiopia
@TibebeEthiopia 🌚

Показано 20 последних публикаций.

988

подписчиков
Статистика канала