. እግዚአብሔር ቀን አለው
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ዘማሪ ካሳሁን ለማ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ለቅሶ ማታ ቢሆንም ጠዋት ደስታ ይሆናል
ሁሉን ቻዩ ጌታ እግዚአብሔር ቀን ያዛል (2x)
አዝ:- ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ
እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (2x)
እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ
እግዚአብሔር ቀን አለው (2x)
አልገፋ ብሉ ትላንት ያስቸገረኝ
ከፊቴ እየቆመ አላሳልፍ ያለኝ
ታሪክን በታሪክ በሚሽረው ጌታ
ሁሉ ተለወጠ በቃ ሲል አበቃ (2x)
አያሳፍር ለተደገፉበት
ይታመናል ተስፋ ላረጉበት
መልካም አምላክ ሁሌም ባለፀጋ
እንደርሱ የለም ፈጥኖ የሚረዳ (2x)
አዝ:- ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ
እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (2x)
እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ
እግዚአብሔር ቀን አለው (2x)
አንድ ጊዜ ቃሉን ሲሰጥ ሊሰራ ሲነሳ
ነገር ሁሉ ይለወጣል ከእርሱ የተነሳ
እኔም ይሄ ገብቶኝ ተደግፌዋለሁ
በኃያላን መሃል ኃይል የ እግዚአብሔር ነው
በኃያላን መሃል ኃይል የ እግዚአብሔር ነው (2x)
ኃይል የእግዚአብሔር ነው (8x)
ለቅሶ ማታ ቢሆንም ጠዋት ደስታ ይሆናል
ሁሉን ቻዩ ጌታ እግዚአብሔር ቀን ያዛል (2x)
አዝ:- ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ
እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (2x)
እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ (እግዚአብሔር)
እግዚአብሔር ቀን አለው (4x)
🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣👇 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 🎼
➥ @Yemezimur_Maikel
➥ @Yemezimur_Maikel