🎶🥁🥁🎶
🥁🎹🎹🥁
እንዴት አይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት ተስፋን ልቤ አይጥልም
እንዴት እንዴት አልጨክንም
🎼
እንዴት አይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት ተስፋን ልቤ አይጥልም
እንዴት እንዴት አልጨክንም
🥁🎶🎶🥁
🎼🥁🥁🎼
እየታየ እምቢታሽ ዕድሜዬን ሲያነክት
በማያረጅ ልቤ መጠበቅ አልታክት
ምን ዓይነት መፍቀድ ነው አቅም የሚሰባብር
አለሁ ለማትወጂኝ ተስፋዬን ስገብር
🎶
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
🎼🎹🎹🎼
ፊት እየነሳሽኝ ልቤ አልደነደነም
ሽሽትሽ እንድቆርጥ ምክንያት አልሆነም
እንደው ስራ አጣሁ አንቺን እንደመሣል
እንዴት ገዳዩ ደጅ ሰው ይመላለሳል
🎶
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
🎹🥁🥁🎹
እንዴት አይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት በቃኝ ብዬ አልምልም
እንዴት ባንቺ አልጨክንም
አልጨክንም አልጨክንም
አልጨክንም አልጨክንም
🎹🥁🥁🎹
ነፃ አልወጣ አልኩ እንጂ ተስፋን ተላቅቄ
መገፋትንማ አውቃለሁ ጠንቅቄ
መውደድ ጸጋም ቢሆን ለልብ የሚታደል
ወድጄ አስጨንቄሽ አልፈጽምም በደል
የስሜት ስካር ነው ፍቅር ሌላ ስሙ
ወድቆ መቅረት አለ ጸንቶ እንደመቆሙ
እንዴት አልጨክንም ብልም እየከፋኝ
ካጉል ተስፋ እሚያስጥል አንዳች መላ ጠፋኝ
ጠፍቼም ሞከርኩት እንዳላይሽ ምዬ
መጥቼም አየሁት ይሉኝታዬን ጥዬ
እንደው ድካም ሆነ በተስፋ መጠውለግ
ሠላሜ አልተገኘም ቢፈለግ ቢፈለግ
ቢፈለግ ቢፈለግ
🎶
እንዴት
እንዴት
እንዴት
እንዴት
🥁🎹🎹🥁
እንዴት አይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት ተስፋን ልቤ አይጥልም
እንዴት እንዴት አልጨክንም
🎼
እንዴት አይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት ተስፋን ልቤ አይጥልም
እንዴት እንዴት አልጨክንም
🥁🎶🎶🥁
🎼🥁🥁🎼
እየታየ እምቢታሽ ዕድሜዬን ሲያነክት
በማያረጅ ልቤ መጠበቅ አልታክት
ምን ዓይነት መፍቀድ ነው አቅም የሚሰባብር
አለሁ ለማትወጂኝ ተስፋዬን ስገብር
🎶
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
🎼🎹🎹🎼
ፊት እየነሳሽኝ ልቤ አልደነደነም
ሽሽትሽ እንድቆርጥ ምክንያት አልሆነም
እንደው ስራ አጣሁ አንቺን እንደመሣል
እንዴት ገዳዩ ደጅ ሰው ይመላለሳል
🎶
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
🎹🥁🥁🎹
እንዴት አይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት በቃኝ ብዬ አልምልም
እንዴት ባንቺ አልጨክንም
አልጨክንም አልጨክንም
አልጨክንም አልጨክንም
🎹🥁🥁🎹
ነፃ አልወጣ አልኩ እንጂ ተስፋን ተላቅቄ
መገፋትንማ አውቃለሁ ጠንቅቄ
መውደድ ጸጋም ቢሆን ለልብ የሚታደል
ወድጄ አስጨንቄሽ አልፈጽምም በደል
የስሜት ስካር ነው ፍቅር ሌላ ስሙ
ወድቆ መቅረት አለ ጸንቶ እንደመቆሙ
እንዴት አልጨክንም ብልም እየከፋኝ
ካጉል ተስፋ እሚያስጥል አንዳች መላ ጠፋኝ
ጠፍቼም ሞከርኩት እንዳላይሽ ምዬ
መጥቼም አየሁት ይሉኝታዬን ጥዬ
እንደው ድካም ሆነ በተስፋ መጠውለግ
ሠላሜ አልተገኘም ቢፈለግ ቢፈለግ
ቢፈለግ ቢፈለግ
🎶
እንዴት
እንዴት
እንዴት
እንዴት