ㅤ ㅤ ✍ በዳንኤል ክብረት
የክፋት ሶፍትዌር
ሰውዬው ወደ ፈጣሪው ይጸልያል፡፡ ሲጸልይም " እባክኽ ከሰው ሁሉ በላይ የምኾንበት ነገር ስጠኝ " ይለዋል ፡፡ ታድያ የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ አምላክ ጸሎቱን ሰማው ፡፡ " ምን እንድሰጥኽ ትፈልጋለኽ ? ነገር ግን አስተውል ለአንተ አንድ ነገር ከሰጠኹህ ለባልንጀራኽ ሁለት አድርጌ እሰጠዋለኹ " ሲል ፈጣሪው መለሰለት ፡፡
ሰውዬውም ከፈጣሪው ከሚያገኘው ነገር ይልቅ በሌሎቹ ሊበለጥ መኾኑ አሳሰበው ፡፡ እናም " የምጠይቀው ነገር ጓደኞቼ ሊየንሱበት የሚችሉበት ነገር መኾን አለበት " ብሎ አሰበ ፡፡ አስቦም አልቀረ መልሱን አገኘው ፡፡ "ፈጣሪ ሆይ ÷ አንድ ዐይኔን አጥፋልኝ " ሲል ለመነ -ስለምን እንዲህ ሲል ለመነ ቢሉ እርሱ በጠየቀው መሠረት " አንድ ዐይኑ ሲጠፋ የጓደኛው ሁለቱም ዐይኑ ይጠፋሉ!እንደ ምን እንዲህ ያለ ነገር ሊያስብ ቻለ ቢሉ የክፋት ሶፍትዌር ተጭኗላ!
ምንጭ ዳንኤል ክብረት(የሁለት ሐውልቶች ወግ 2003 ዓ.ም ገጽ 87
@Zerusoutlying