ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


የኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሕይወትና ትምህርት ይቀርብበታል።
https://t.me/abagiyorgismnale
ለሌሎች በማጋራት መንፈሳዊ ግዴታችንን እንወጣ
ለጥያቄዎችና ለአስተያየት
@Dnmikii @feke17

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


እንኳን ለመምህረ ዓለም ለአፈ በረከት አፈ መአዛ አፈ ጳዝዮን አፈ መዓር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፍልሰተ አጽም በሰላም አደረሰዎ ቅዱሱን ከወደዱት 5 ደቂቃ ብቻ ስጡን የፍቅርዎን መግለጫ  ሙሉ ገቢው በጦርነት ምክንያት ጣራው ሳይቀር ፈርሶ በችግር ላይ ላለው ራያ ቆቦ ወረዳ የኤፍራታ (የአረቋቱ) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድነት ገዳም የሆነውን ዝማሬ Etart media ላይ በመስማት ይደግፉ 👇
ይሄው ሊንክ

https://youtu.be/MBKSklYDrmk?si=EltgbSJvHVCm09cW 


     
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

‘እግዚአብሔር  በጽድቁ ከሚመካ ጻድቅ ይልቅ ስለ ኃጢአቱ የሚያለቅስ ዘማዊን ይወድዳል’  ይላል፡፡  በእርግጥም ራስን አጽድቆ የሌላውን ሰው ኃጢአት የማሰብን ያህል ኪሳራ በክርስትና ሕይወት የለም፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርበው የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት ሲቆጥር ሳይሆን የራሱን በደል ሲቆጥር ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‘እኔ መተላለፌን አውቃለሁና ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና’ እንዳለው እግዚአብሔር ኃጢአትህ ተሰረየችልህ የሚለው ሰው የራሱን ኃጢአት ዘወትር የሚያስብ ሰው ነው፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ትህትና እና ትዕቢት

https://youtu.be/L0Kl-ye3cPQ?si=CSbvp_ywSMN5Mg32

https://youtu.be/MkcI30AYzDI?si=ThkOTCGDbdQ-O0ao








«#ሁሉን_የፈጠረ፥ ሁሉን የፈጸመ፥ ሁሉንም የጀመረ፥ ሁሉን የያዘ፥ ሁሉንም የጨበጠ እግዚአብሔር። መላእክትና የመላእክት አለቆች፥ መናብርትና ሥልጣናት፥ አጋዕዝትና ኃይላት፥ ፀሐይና ጨረቃ፥ ከዋክብትም ድርገታትም የሚሰግዱለት፤ ተገዦቹና ጉልቱም ናቸውና። በሁሉ ባለጠጋ ሲሆን ራሱን ከሁሉ ደሀ አደረገ። ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው፥ እስከ ሞትም አደረሰው።»
#ቅዳሴ_ማርያም (ቊ. ፩፻፳፮–፩፻፳፯)።




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም (እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ) ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ፡፡
ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፡፡
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፡፡
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ፡፡
እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ፡፡
ወተመይጠት ማርያም ሀገረ እስራኤል አቡሃ።
ነቢራ በግብፅ ኣርብዓ ወክልኤተ አውራኀ፡፡
ይሰግዳ ላቲ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ።
እምይእዜሰ ነገፍኩ ላሀ ፡፡
ለእምየ በእትወታ ረኪብየ ፍሥሓ፡፡

🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜

ትርጉም
እመቤቴ ማርያም ሆይ እስከመቼ ድረስ በባዕዳን አገር ትኖሪያለሽ?
ወደ አገርሽ ገሊላ አሁን ተመለሺ እንጂ
ናዝራዊ ከሚሰኝ ሕፃን ልጅሽ ጋር ተመለሺ
ዖዝያን ንጉሥ ስለ ቅዱሳን ክብር እንደተናገረው፥ አንድም በንጉሥ ዖዝያን ዘመን ስለ ቅዱሳን ክብር እንደተነገረው
የልጅሽ የብቻ አባቱ ከሰማይ ሆኖ ከግብፅ ምድር እንደሚጠራው፥ እንደጠራው እንድትኖር
ማርያም ወደ አባቷ አገር ወደ እሥራኤል ተመለሰች
በምድረ ግብፅ በስደት አርባ ሁለት ወራትን ከኖረች በኋላ፥ ኖራ
የጢሮስ ልጆች ስጦታውን አቅርበው ይሰግዱላታል፥ ይስገዱላት፥ እንደሰገዱላት
እኛም እንዲሁ ስጦታዋ የሆነ ምስጋናዋን አቀረብንላት
በእመቤታችን ከግብፅ ምድር መመለስም ልቦናችን ሐሴት አደረገች።

🌹@weldwahid🌹


ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥15

ጢሞቴዎስ በሕጻንነቱ ያነባቸው የነበሩት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው ካልን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው በዚያን ሰዓት ገና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አልተጻፉም ነበርና።

ብሉይ ኪዳን በሐዲሰ ኪዳን የተብራራ ስለ ክርስቶስ የሚናገር በውስጡ ሐዲስ ኪዳን የተሰወረበት መጽሐፍ ነው ሊቁ አውግስጢኖስ ይህንን በግልጥ ነግሮናል።


ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ “ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል፡” እንዳለው እኛ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በሙሴ ሕግና በነቢያት መጻሕፍት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገሩትን ከመማር ብሉይና ሐዲስን አስተባብሮ ከመያዝ ወደ ኋላ እንል ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍት አያሰናብቱንም ።የዮሐንስ ወንጌል 1፥45

ዲ/ን ዘሚካኤል እሸቱ
ህዳር 5/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ /ኢትዮጵያ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በሰማዕቱ የእስጢፋኖስ ወዳጆች ፤ ሰማዕቱ አለሁ ይበላችሁ።


((((. ጥቅምት 27. ))))

+++ አባ ጽጌ ድንግል +++

#የማኅሌተ_ጽጌ ደራሲ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ነው፡፡ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) የተወለደውም በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲሆን፤ ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት ነበረ፡፡

በዕለታት በአንዱ ቀን በጻዲቁ በአቡነ ዜና ማርቆስ በተገደመው ደብረ ብስራት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ሄዶ ሳለ ጻዲቁ አቡነ ዜና ማርቆስ በትንቢተ ኢሣይያስ የተነገረውን በኅብረ አምሳል ያጌጠውን ‟ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ ፤ ከእሴይ ግንድ በትር ትወጣለች ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል" የሚለውን ሲያነብ ቢሰማ ቀድሞውንም ቃሉን የሚያውቀው ይሁንና ትርጓሜውን ያልተረዳ መሆኑን ጠይቆ እንዲተረጉሙለት ቢጠይቅ ጻዲቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ንባቡን ከትርጓሜ ትርጓሜውን ከምስጢር አስማምቶ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ የሚለው ንባብ ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡

+ በእንተ ማኅሌተ ጽጌ +

ማኅሌተ ጽጌ ከሁለት የግዕዝ ቃላት ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ #ማኅሌት ማለት ኀለየ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውን ምስጋና፣ መወድስ ማወድስ ማለት ነው፤ #ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ፣ የፍሬ ምልክት፤ ውበት፣ ደም ግባት ማለት ነው፡፡

🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨✨

#ማኅሌተ_ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር እና ሲተረጎም ደግሞ የአበባ የፍሬ ምስጋና መዝሙር መወድስ ማለት ነው፡፡ ይህም አበባ ተብላ የተጠራች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ፍሬ የተባለው ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎች እና ፍሬዎች እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡

የአባ ጽጌ ድንግል በረከታቸው ይደርብን🙏🙏🙏


"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/


በረከታቸው ይደርብን 🙏🙏
የህንድ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤ/ክ ፓትርያርክ ማር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።


ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥቅምት ፲፯
በዓለ ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ


በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ!


#ሁልጊዜ በዓይነ ልቡናዬ አይሻለሁ በሃሳቤም በየሥፍራው ሁሉ አገኝሻለሁ በተኛሁ ጊዜ እኔን ለመጠበቅ የነቃሽ ነሽ፡፡ ከመኝታዬም ስነቃ እኔን ለማንሣት የተዘጋጀሽ ነሽ፡፡
#ስቀመጥም እኔን ለመምከር ትደርሻለሽ፡፡ በቆምሁም ጊዜ በቀኜ ትቆሚያለሽ በተናገርሁም ጊዜ አንደበቴን ለማጣፈጥ ታከናውኛለሽ፡፡ በዝምታዬም ጊዜ ለመጠበቄ ማሞገሻ ነሽ ኃሴትም ባደረግሁ ጊዜ ተድላ ደስታ ነሽ፡፡
#ባዘንሁም በተቆረቆርሁ ጊዜ የኃዘኔ መጽናኛ ነሽ፡፡ ባለቀስሁም ጊዜ የልቅሶዬ መተዊያ ነሽ፡፡ በዘመርሁ ጊዜ ለእጄ እንደ መሰንቆ ለጣቶቼም እንደ በገና ነሽ፡፡
#በተራብሁም ጊዜ ለሆዴ ትመግቢኛለሽ ፤ በተጸማሁም ጊዜ እኔን ለማርካት የሕይወት ውሃን የተመላሽ ነሽ፡፡ የተፍገምገምሁም ጊዜ እኔን ለመደገፍ እጅሽን ትዘረጊያለሽ፡፡ በወደቅሁም ጊዜ እጅሽን ዘርግተሽ ታነሺኛለሽ።

አርጋኖን ዘሐሙስ






#ድንግል ሆይ የኔን አመንዝራነቴን እናገራለሁ ያነቺን ንጽሕና የልጅሽን ቸርነት አወራለሁ፡፡
#ድንግል ሆይ የኔን ስሕተት ያንቺን ማማለድ የልጅሽንም መታገስ እናገራለሁ፡፡
#ድንግል ሆይ የኔን ስንፍና ያንቺን ምክር የልጅሽንም ይቅርታ እናገራለሁ፡፡

መጽሐፈ አርጋኖን

Показано 20 последних публикаций.