አቡ መርየም አዳማ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


هدفنا الذب عن السنة.....................
ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች የሚሰራጭበት ቻናል ነው። በተጨማሪም ተውሂድንና ሽርክን እንዲሁም ሱናንና ቢድአን እንዲሁም የቢድአ ሰዎችን ለሰዎች በፁሁፍና በሙሀደራ መልክ ግልፅ ማድረግ
https://telegram.me/abumerymadama

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ
🚫   ምቀኝነትን ተጠንቀቅ

   ምቀኝነት የልብ በሽታ ሲሆን አላህ ለባረያው የሰጠውን ፀጋ እንዲወገድ መመኘትና ለዚህም አስባብ ማድረስ ነው ። የዚህ አይነቱ ምቀኝነት በክፋት የመጨረሻው ደረጃ የደረሰው አይነት ሲሆን መጨረሻ ላይ የሚጎዳው ባለቤቱን ነው ። ምክንያቱም የአላህን ውሳኔ ለመቀየር መታገል ስለሆነ አይሳካምና ። አላህ ከባሮቹ ለሻው በሚሻው ነገር ይለየዋል ወይም ስኬታማ ያደርገዋል ። ይህ ማለት በሰዎች እይታ ነው ምክንያቱም የመጨረሻው ስኬት ከጀሀነም ተጠብቆ የጀነት መሆን ስለሆነ ። ይኼኛውን ስኬት ደግሞ ከአላህ ውጪ የሚያውቀው የለም ። ነገር ግን በምቀኝነት በሽታ የተለከፈ ሰው ይህን ፀጋ በሚያይ ጊዜ ውስጡ በምቀኝነት እሳት ይነዳል ። ከዚህ በላይ ምን አይነት ጉዳት ይኖራል ።
      ምቀኝነተ በሁሉም ላይ ሊኖራ የሚችል አስቀያሚ ባህርይ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ታግለው ይደብቁታል ። ግልፅ አያደርጉትም ለዚህም አላህን በመፍራት ይታገዛሉ ። የተበላሸ መንፈስ ያላቸው ወራዶች ግን ከላይ ለመግለፅ በተሞከረው መልኩ የአላህን ውሳኔ ወይም መሺአ ለመቀየር ይታገላሉ ። እንቅልፍ ያጣሉ ፣  ይብከነከናሉ ፣ ጨጓራቸውን ይልጣሉ በዚህም የዱንያ ላይ ቅጣት ያገኛሉ ።
    የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ እንደ አይጥ ነው ። አይጥ ጥሩ ነገርን  ከስር እየቦረቦረች ለማጥፋት ትዳክራለች ። ይሁን እንጂ ሀሳቧ ሳይሳካ የወጥመድ እራት ትሆናለች ። የምትያዘውም አንገትዋ ወይን አፏ ነው ።
    ምቀኝነት መጀመሪያ የጀመረው ኢብሊስ ነው ። በአባታችን ኣደም ላይ በመመቅኘት ። አላህ አባታችን ኣደምን ከጭቃ ከፈጠረው በኋላ ለመላኢካዎች ስገዱለት አላቸው ። መላኢካዎችም የጌታቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ሰገዱ ። ከእነርሱ ጋር የነበረው ኢብሊስ ግን አልሰግድም አለ ። እንዳይሰግድ የከለከለውም ምቀኝት መሆኑን እንዲህ ብሎ መሰከረ : –

« وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ قَالَ أَأَسْجُدُ لِمَنْ خَلَقْتَ طِينًا »

                         الإسراء  ( 61 )

" ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ወዲያውም ሰገዱ ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ፡፡ «ከጭቃ ለፈጠርከው ሰው እሰግዳለሁን» አለ ፡፡ "

« قَالَ أَرَأَيْتَكَ هَٰذَا الَّذِي كَرَّمْتَ عَلَيَّ لَئِنْ أَخَّرْتَنِ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَأَحْتَنِكَنَّ ذُرِّيَّتَهُ إِلَّا قَلِيلًا »

                 الإسراء   ( 62 )

«ንገረኝ ይህ ያ በእኔ ላይ ያበለጥከው ነውን
እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስህተት በእርግጥ እስባቸዋለሁ» አለ ፡፡"
        ኢብሊስ ሊሰግድ የከለከለው ሁለት ነገር ነበር ። ኩራትና ምቀኝነት ። ኩራቱን ከጭቃ ለፈጠርከው ልስገድ ወይ በማለት ገለፀው ። ምቀኝነቱን ደግሞ ይህ ነውን ከኔ ያስበለጥከው በማለት ገለፀው ። በዚህም ከአላህ እዝነት የተባረረና እስከቂያማ የሚረገም ሆነ ።
     ምቀኝነት አላህ ለባሪያው የሰጠውን ፀጋ እንዲፃረር ያደረገው ሰው በመፃረሩ ልክ ከአላህ እዝነት የመራቅና የመረገም ድርሻ አለው ።

       አላህ በዱንያ ላይ በምቀኝነት እሳት ከመንደድ ይጠብቀን ።

አንገብጋቢ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ

  https://t.me/bahruteka


Репост из: Abu abdurahman
ሴት ልጅ ስለ ዲኗ ብትማር !


ሴት ልጅ ስለ ዲኗ ብትማር ለማያውቁ እህቶቿ መመራት ሰበብ ለዋለሉ መንገድ ለጠፋባቸው ስነምግባራቸውን ላጡ ሀያዕ ለጠፋባቸው ፣ በመጥፎ ጓደኞች ለተጎዳች እህቷ ሂዳያ ማግኘት ሰበብ ትሆናልች ።

የአሏህ ዲን የመልዕክተኛው መንገድ የሶሃቦች ፈለግ ሀራም ሀላል ቢድዓ ሱና ተውሒድ ሺርክ የሚታወቀው እውቀት እንጂ ሌላ መንገድ የለውም ።

* ሴት ልጅ ስትማር ነው ያላትን ሀቅ እና ያለባት ግዴታ ልትረዳ የምትችለው ።

ውጭ ወታ በሚበር በሚህራብ በሚዲያ ባትታወቅ ውጭ ላይ የሚሰሩትን የሚታወቁትን ፣ ኸጢቡን፣ ኢማሙን ፣ ፈቂህ ሙደሪሱን ፣ ነህዊይ ሙፈሲሩን፣ የምታቀርብ ፋብሪካ ነች ።

አሏህ ሴቶቻችን ለኢስላም ለሙስሊም የሚጠቅሙ ያድርጋቸው ከሸረኞች ሴራ ወጥመድ ያርቃቸው

https://t.me/abuabdurahmen


የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲን በተለያየ መንገድ የማጠልሸት ሴራ
—————ክፍል 2
አይ ሳዑዲ!
ጠላቶቿ መዘርዘር የሚችሉት ጥቂት ኃጢያቶቿን ቁጭ ብለው ይለቃቅማሉ፣ እኛ ደግሞ ሌተ ከቀን መልካም ስራ በመስራት ደፋ ቀና እያለች መልካም ስራዋን አብዝታ ቆጥረን ልንዘልቀው አልቻልንም!!

ስለ እነዚያ በኢስላም ስም ስለሚነግዱ ነጋዲዎች ንገሩኝ እስኪ? ቁጭ ብለው የሙስሊሙን ደካማ ጎን ጠብቀው ከማስተጋባት በስሜት እንዲጋልብ ከማድረግ የዘልለለ ለእስልምና ምን ውለታ ነው የዋሉት??
ንጉሶቿ ከየትኛውም ፖለቲካ እችላለሁ ከሚሉ የአለማችን ፖለቲከኞችና የሀገር መሪዎች የላቀ የፖለቲካ ብቃት ያላቸው ንጉሶች ናቸው!። ይህን የፖለቲካ ብስለትና ብቃትም እንደ ሀገራቸውና እንደመላው የአለም ሙስሊም ሀገራት ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነፃፀር የላቀ ጥቅም በሚያስገኝ መልኩና ጉዳትን በሚከላከል መልኩ በአግባቡ ይጠቀሙበታል!። የማንም በዲኑ ስም የሚነግድ የፖለቲካ ነጋዴ ጩሀት ያለ አቅጣጫ እንዲሄዱ አያደርጋቸውም!።

አንዳንድ ሰዎች ለሳዑዲና ለንጉሶቿ ያለቸው ጥላቻ፣ አንዳንዴ የሚከሰቱ ኃጢያቶቿ እነሱ እንዲኖሩባቸው ከሚመኙዋቸው ከባባድ ወንጀሎች ህጋዊ ሆነው ከተስፋፉባቸው፣ ሺርክና ሰዶማዊናት  በግልፅ በመንግስት ደረጃ ፈቃድ አግኝተው ከተንሰራፉባቸው ሀገራት አንፃር እሩብ ያህል እንኳን ሀገሪቷ ላይ ኃጢያት ተንሰራፍቶ አይደለም!!

የሚደንቀው ሁል ጊዜ አል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን ሳዑዲን ለማጠልሸት የሚጥሩበትን መንገድ እንደየ ቦታው መለያየታቸው (መቀያየራቸው) ነው።

- ሸሪዓን ለሚወደውና ለሚደግፈው ለሙስሊሙ የህብረተሰብ ክፍል ልክ ለዲኑ እንደተቆረቆረ "ሳዑዲ ሸሪዓን ጥሳ እንዲህ አደረገች፣ እንዲህ አደረገች፣ በቃ እኮ አሁንማ ተበላሸች፣ አለቀላት፣  በአውሮፓዎች ቀኝ አገዛዝ ወደቀች…ወዘተ" እያሉ ያታልሉታል።

- አውሮፓዎች ጋር ሲሄዱ ደግሞ "ሳዑዲ አንባገነን ናት፣ ዲሞክራሲን አታከብርም፣ ሴቶችን አፍናለች፣ በነፃነት መናገር የለም…" የመሳሰሉትን እያሉ ሳዑዲ ላይ ያነሳሱዋቸዋል። ሁልጊዜም ትግላቸው ሳዑዲን እንደ ቱኒዚያ፣ሶሪያ፣ግብፅና ሊቢያ… ለማውደም ነው። እኔን ይበልጥ የሚገርመኝ ደግሞ እዚሁ ቁጭ ብሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሳዑዲን እንዲጠላ የሚያራግቡ የነ ሰልማነል አውዳ ቡችሎች ናቸው!።

በውስጧ ያሉት ኢኽዋኖች ለሳዑዲ ባላቸው ጥላቻ ከውጮች አይሻሉም፣ ውጪ ያሉት ከውስጦች አይሻሉም፣ ሆኖም ግን አላህ በረህመቱ ከሺዓም፣ ከአይሁድም፣ ከኢኽዋንም፣ ተንኮልና ሴራ ጠብቋታል!። ኢንሻአላህ ወደፊትም ይጠብቃታል!!።

አመራሮች ላይ ችግሮች የሉም ፍፁም ናቸው ማለቴ እንዳልሆነ ይሰመርበት!፣ ነገር ግን እንደ ኢስላም ሙስሊሙ ህብረተሰብ መሪውን ሲሳሳት በዓሊሞቹ መምከር ማስመከር ነው እንጂ፣ እየተቹ ከተቻለ ለጠላት አሳልፎ መስጠት፣ ይህ ካልተሳካም የእርስበርስ ጦርነት ቀስቅሶ የሙስሊሙን ደም ማፋሰስና ሸሪዓዊ ነገሮች እንዲወድሙ ማድረግ የዘመናዊ ኸዋሪጆች የኢኽዋኖች ልዩ መገለጫ እንጂ ፈፅሞ ሸሪዓው ያስቀመጠው የሙስሊሞች ስርኣት አይደለም!።

እኔ ሙስሊሙን ህብረተሰብ አደራ የምለው ነገር ቢኖር፣ የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲንና ዓሊሞቿን አላህ እንዲጠብቅ፣ መሪዎቿን ሲሳሳቱ አላህ እንዲያስተካክላቸው ከልብ ዱዓ እንዲያደርግ ነው።
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


ያልገባችሁ ራሳችሁን ለማንቃት ሞክሩ
➩➪

🔎 አፍሪካ ቲቪ ላይ የሚታዩት እና ነሲሃ ቲቪ ላይ የሚታዩት ሰዎች እንደው አንድ ላይ ሆናችሁ ብናያችሁ የበለጠ ሞራላችንን ❴ይጨምራል❵
🔎 እኔ እነዚህ ❴በነሲሃ ቲቪ ዱዓቶች እና አፍሪካ ቲቪ ዱዓቶች❵ ላይ ብዙ ልዩነት ያለ አይመስለኝም። ለማንኛውም ጥሩ  ጥሪ ነው። ኢስላማዊ ቲቪዎች አንድ ላይ በመሰብሰብ አላማቸው አንድ መሆኑን...
🔎 የበለጠ አንድነት ስለሚያመጣ እንዲያስቡበት እና እንዲገብሩት ጥሪ አደርጋለሁ።

🎙 በኢኽዋኖች የሚዘወረው ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን

ልብ-በሉ ጉዳዩ [የነሲሃ ቲቪ ሰዎች ከአፍሪካ ቲቪ ሰዎች ❮ኢኽዋሮች❯ ጋር መደመራቸው] ለሁሉም ግልፅ እየሆነ ነው።

በየመድረኩ በአንድ መታየታቸው አብረው መጓዛቸው አላጠግብ ያላቸው አንዳንድ ሰዎች በዚህ መልኩ በቲቪ አንድነታቸው እንዲበሰር ጠይቀዋል

ሙመይዓዎች ተደምረዋል ሲባል የሚየንቀጠቅጥህ ሁሉ አሁን ምን ትመልሱ ይሆን? ለነገሩ 70 ኡዝር ካልቻላችሁም የማላቀው ኡዝር አለ በሚል ትተኙ ይሆናል። ምክንያቱም በዚህ መልኩ እንዲታስብ የሚያደርግ ክኒን አቅመዋችኋልና።

🏝 ለማንኛውም አስኪ አንድ ካልሆኑ ለዚህ መልስ ይስጡት! ልዩነት አለን ይበሉት እስኪ እኛ ከኢኽዋን ጋር አንድ አይደለንም በማለት ያስቀምጡ!!!
    ➪ በፍፉአያደርጉትም ምክንያቱም ተደምረዋልና አዎ ቁርጥህን አዎቅ ኢድغاም ከደረጉ ሰንብተዋል። አንተ ግን አሁንም ሙሪድ ነህ? አላህ ይድረስልህ!

🔎 ኢልያስን ብትጠይቁት «እና ምን ይጠበስ» ማለቱ አይቀርም። ከዚህ በፊትም ይህንኑ ስላለ! ለማንኛውም ንቁ!

🏝 ••⇣⇣  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


Репост из: የቡታጅራ ሰለፍዮች ዉዝግብና ከጀርባው ያሉ ሴራዎች
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አውቀሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ነው::

ውድ ሰለፊዮች እንደሚታወቀው ሙመይዓዎች ከየትኛውም ፊርቃ በላይ ሱናን ለማጥፋት መታተር ከጀመሩ ሰንበትበት ማለቱ ይታወቃል በመሆኑም ከሚጠቀሙበት ትልቁና ከዋናዋና መንገዳቸው አንዱ=-
■ ከሱፍዮች ከአህባሾች ጋር ሲሆኑ ሱፊ ሰለፊ አንባባልም በማለት ((በመመለስ ላይ የነበሩ አባቶቻችን የመሸወዳቸው ሰበብ በመሆን))ማለትምአባቶቻችን ያሉበት መንገድ ትክክል እንደሆኑ እና የከዚ በፊቱ እነሱ ላይ የሚሰነዘረው ትችት ስህተት እንደሆነና በቸኳዮች,በነሱ ቋንቋ ባልበሰሉ አካላቶች የመጣ እንደሆነ እንዲገነዘቡ በማድረግ አብሮ በአንድ መድረክ በመቆም በፊት ለፊታቸው መስክረው በመውጣት እና በተግባርም ጭምር ሰለፊያን እውነታዋን የሚያብራሩ መሻይኾችና ኡስታዞች በየመስጂዱ በየዳዕዋ መድረኩ,በየመድረሳው እያሳደዱ የነሱን ድብቅ ሴሪና እኩይ ተግባር ያልተረዱ አካላቶችንም ጭምር በማስተባበር እየተጓዘ ይገኛሉ

ነገር ግን በጣም ሚያሳዝነውና ኡሱሉ ሰላሳ ይቃጠል በተባለበት በአህባሽ ፊትና ዘመን ሆኖ ማያውቀውን አሁን እየሆነ ይገኛል::አባቶቻችን ጋ ቤትለቤት እየዞሩ ከእናንተ ጋር ለምን ተጨመራቹ ለምን አትጠየፏቸውም ብለው ነው የተጣሉን በማለት የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት በየመስጂዱ ሁዝ,ዋጂባት,ኪታቡተውሂድ ወዘተ የሚቀሩ ልጆችን ከአህባሽ, ከሱፊይ እና ከተብሊግ ጋር በመሆን እየበተኑ ይገኛሉ

ግን በጣም ሚዓጅበው ወጣቱ ይህን ረቂቅ ፖለቲካቸው ተገንዝቦ በነቂስ እነሱን በመቃወም ከሰለፊይ መሻይኾች መሆኑ ይህ የአላህ ተዓምር ነው ም/ቱም ባለስልጣን ይዘዋል,ባለሃብቶች ይዘዋል,የጠመሙ ፊርቅዎች ባጠቃላይ ይዘዋል ነገር ግን ሰለፊያ ቀንበቀን እያበበች ትገኛለች,ም/ቱም ሰለፊዮች የተደገፉት የአለማቱ አስተናባሪ አላህ ነውና::

https://t.me/yebutajiraselefiyochchanel


Репост из: مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)
🔵ውድ ቀናቶች እየደረሱ ነው

ሁለተኛ ዙር ወርሐዊ ፕሮግራማችን ከፊታችን ጁሙዓህ (20/03/2017) ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ይቆያል ኢን ሻእ አላህ

የኪታቦቹ ዝርዝር ለማስታወስ

١. مقدمة في أصول التفسير
የኪታቡ pdf
⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬
https://t.me/medresetulislah/6612

٢. الأصول من علم الأصول
የኪታቡ pdf
⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬
https://t.me/medresetulislah/6634

٣. مختصر سيرة الرسول ﷺ
የኪታቡ pdf
⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬
https://t.me/medresetulislah/6639

٤. بيان فضل علم السلف عل على علم الخلف
የኪታቡ pdf
⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬
https://t.me/medresetulislah/6620

٥. بلوغ المرام
የኪታቡ pdf
⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬
https://t.me/medresetulislah/6630

٦. متممة آجرومية
የኪታቡ pdf
⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬⏬
https://t.me/medresetulislah/6624

المدرس:- 🎙 فضيلة الشيخ أبو عبدالحليم عبدالحميد بن ياسين اللتمي

🕌 በአልኢስላሕ መድረሳ



https://t.me/medresetulislah


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ሙመይዓዎችን ተጠንቀቋቸው!!
—————
ውድ የሆነች ገሳጭ ምክር!!
、、、、、、
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሓዲ ዑመይር አል-መድኸሊ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“በሸይኽ አልባኒና በሌሎችም የሱንና ሊቃውንቶች መካከል አለመግባባቶች ይከሰቱ ነበር ብለን በተደጋጋሚ ከአንድ ጊዜ በላይ ነግረናችኋል፣ ነገር ግን ወላሂ በጠቅላላ በዓለም ደረጃ የሰለፊዮች ሶፍ (አንድነት) ላይ አንድም ተፅእኖ አልፈጠረም ነበር!!። አሁን ግን የፊትና ባለ ቤት የሆኑ ገና ትናንሽ ተማሪዎች ሆነው ፊትናን በመፍጠር በሱኒዮች መካከል ተፅእኖ ለማሳደር የሚፈልጉ በቀን እና ሌሌት ኢማም ሆነው ያነጋሉ (ብቅ) ይላሉ። ሁለት ቀን ለማቅራት ቁጭ ይልና በቃ እርሱ ኡስታዝ ነው፣ ለእርሱ የሚወግኑ ማንም የእርሱን ስህተት ሊያርም የሚነሳን አካል የትኛውንም እርምት የማይቀበሉ ቡድኖች ሆነው ብቅ ይላሉ። የሚታረምበት መንገድ ምንም ያህል ግልፅ በሆነ ማስረጃ የተሞላ ቢሆን (አይቀበሉም)። በቃ ልክ ዱኒያ ቁጭ ብድግ የምትል እስከሚመስል ይደርሳሉ፣ ምክንያቱም እነዚያ ለእርሱ ወግነው ቡድንተኛ ሆነዋል። ይህ ኡስታዝ ምናልባትም ገና ምስኪን የዲን ተማሪ ይሆናል፣ ምናልባትም ጥሩ ነገር ሊኖረው ይችላል፣ ነገር ግን ወገንተኝነቱ ምንድነው?!።

የሂዝቢዮች (ቡድንተኞች) ባህሪ (ስነ-ምግባር) ወደ ከፊል ሰለፊዮች ገብቷል። ወላሂ ይህቺ ስነ-ምግባር በመካከላችን አልነበረችም!፣ ወላሂ ፊት ለፊታችን ሸይኽ ኢብኑ ባዝና ሸይኽ አልባኒ ሌሎችም በጃሚዐተል ኢስላሚያ ተከራክረዋል፣ ይህ ከመሆኑም ጋር ወላሂ ሰለፊዮች ላይ አንዳች ተፅእኖ አላሳደረም ነበር። ሸይኽ አልባኒ ኪታቦችን ፅፈዋል፣ ከፃፏቸው ኪታቦች ውስጥም ከሩኩዕ በኋላ እጆችን ደረት ላይ ማስቀመጥ ቢድዐ ነው ብሏል፣ ከመሆኑም ጋር ግን ወላሂ በሰለፊዮች አንድነት ለይ አንደም የፈጠረው ተፅእኖ አልነበረም። ሱፊዮችና ኩራፊዮች ወጣቱን አንዱን በአንዱ የሸይኽ ኢብኑ ባዝንና የሸይኽ አልባኒ የመስአላ ልዩነት ተጠቅመው ሊመቱት ፈለጉ ወላሂ ምንም መንገድ አላገኙም!።

ወንድሞቼ በእነዚህ ነገሮች ላይ ነቃ ልትሉ ይገባል!፣ ለአገሌና ለአገሌ ብላችሁ መወገንን ተውት!፣ ለአንድም ሰው አትወግኑ የሰለፊያን ደዕዋ ትለያያላችሁ፣ ይህን ተግባር በጭራሽ አንወድላችሁም!። አንዳችሁ በሌላው ላይ ይታገስ፣ ከፊላችሁ ሌላውን በጥበብ ይምከር፣ ለአገሌና ለአገሌ መወገን ቡድንተኛ መሆን ውስጥ አትግቡ!፣ በዚህ አካሄድ ሰለፊያ ተበጣጥሳለች፣ ይህቺ ቡድንተኞች (ሂዝቢዮች) ወደ እናንተ (ወደ ሰለፊዮች) ያስገቧት ተግባር ናት። እንዲህ ላሉ  ነገሮችም ከእናንተ ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋልና ተውዋት ባረከላሁ ፊኩም!። ደጋግ ቀደምቶቻችሁ ወደነበሩበት ተደጋጋሚ የሆነ በጥበብና ገሳጭ በሆነ መልኩ የመመካከርና የላቀች በሆነችዋ ባህሪ የማጌጥ ታሪክ ተመለሱ!።

እንዲሁም ወደ ጀርህና ተዕዲል ኪታቦች ስትመጣ በግለሰቦች ጉዳይ ላይ አለመግባባቶችን ታገኛለህ፣ አንደኛው (በደረሰው ልክ) ትክክል ነው ይለዋል፣ ሌላኛው ደግሞ ተሳስቷል ብሎ ጀርህ ያደርገዋል፣ ይህ ከመሆኑም ጋር ግን የሀዲስና የሱና ባለቤት በሆኑት ሰለፊዮች መካካል ክርክሮችንና ቡድንተኝነትን አታገኝም። ምክንያቱም እነሱ  ነገሮችን ገርና ቀላል በሆነ መንገድ መረዳት ይችሉ ነበር፣ ባልተግባቡባቸው ነገሮችም እንዲህ አይነት ጥሩ ስነ-ምግባር እንዲኖራቸው የሚያደርጋቸው መመዘኛዎችና መርሆች አሉዋቸው፣ ከዚህ ውስጥም ጀርህ አል-ሙፈሰር አለ።

ከመሆኑም ጋር ከነርሱ ውስጥ "እርሱ ጀርህ ያደረገው ለእኔ አጥጋቢ አይደለም፣ አለያም ማድረጉን ወድጄ መቀበል እኔን አይዘኝም (ግድ አይለኝም)።" የሚል አይገኝም ነበር፣ ሌሎችንም መሰል በመክሯሯትና በትቢት (በአፈንጋጭነት) ሀቅን የማይቀበሉባቸውን መንገዶችን አይጠቀሙም ነበር። በመካከላቸው በቢድዐ ባለቤቶች ጉዳይ ላይ አለመግባባቶች አይገኙም ነበር። የእውቀት ባለቤት የሆነ አካል አንድን የቢድዐ ሰው "ሙብተዲዕ ነው" ብሎ ብይን ከሰጠበት በኋላ ልዩነት አይኖራቸውም ነበር። ምንም ያህል  ያ  ሙብተዲዕ በውሸትና በማምታታት ጥግ ቢደርስ ሙብተዲዕ ለተባለው አካል የሚከላከል ሌላ ግንባር አይፈጠርም ነበር። ልክ በዚህ ጊዜ ሰለፊዮች ላይ እየተከሰተ እንዳለው ፊትና አይከሰትም ነበር። አህሉሱናዎች ከእንዲህ ያለው ፊትና እና ከባለቤቶቹም ጤነኞች (ሰላም) ነበሩ!። ምክንያቱ ደግሞ ሚዛናዊና ሀቅን ወዳድ መሆናቸውና (በዲናቸው ጉዳይ) ከዱኒያ ጥቅማጥቅምና ገንዘብ የራቁ በመሆናቸው ነው። የቅርብ ሰው በሆነውም በሩቁም፣ በወዳጅም በጠላትም ሀቁን ይናገራሉ፣ በሀቅ ላይ ፍትሃዊ ሆነው ያስተካክላሉ።

ለዚህም ነው ታሪካቸውን በተደጋጋሚ ስንቃኝ በሀቅ እርስ በርሳቸው በአንድነት የተጣበቁ (የተሳሰሩ) ሆነው በቢድዐና በጥመት ባለቤቶች ላይ አሸናፊና የባለይ ሆነው እንጂ አናገኛቸውም። አህሉሱናዎች በዚህ እርስበርሳቸው በመጣበቃቸውና በመተሳሰራቸው በተደጋጋሚ ታሪካቸው ሲቃኝ በቢድዐና በጥመት ባለቤቶች  የበላይ ሆነው ነበር።

አሁን ላይ ግን የቢድዐ ሰዎች የበላይ ሆነውባቸዋል፣ ወንድሞቼ አሁን ላይ የቢድዐ ሰዎች የበላይ ሆነውባቸዋል፣ ምክንያቱ ደግሞ ወደ ሰለፊያ የሚጠጉ ሰዎች በሚኖሩት የተበላሸ አኗኗር ነው!!። አላህ ለመልካም ነገር ይግጠማችሁ!!፣ ጉዟችሁንም በሀቅ ላይ ያፅናው!!።” [አዝ-ዘሪዓህ ኢላ በያኒ መቃሲዲ ኪታብ አሽ-ሸሪዓህ 2/589-590]
ትርጉም:- ✍🏻ኢብን ሽፋ: ሸዕባን 21/1442 ዓ.ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join አድርገው ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ወላሂ በጣም ያሳዝናሉ ሁለቱም ግለሰቦች ማለትም (ሳዳት ከማል እና የኛው ጉድ ሱሩር አወል)::
____


👉 ሳዳት ከማል የሰው ሸይጣን ከእነርሱ ጋር አንድ ከምሆን የሚቀብረኝ አጥቼ አሞራ ይብላኝ ሲላቸው የነበሩት አሕባሽና ሱፍዮችን አሁን እድሜ የጠገቡ የህዝቡ ሀላፊነት የተጣለባቸው የማይቸኩሉ በሳሎች ይላቸዋል ።
የሑደይቢያን ስምምነት ለምን እንዳመጣው ለራሱም የገባው አይመስለኝም ። ከአሕባሽና ሱፍዮች ጋር አንድ ለሆኑት ነሲሓዎች ወይስ የጥምር መጅሊሱ ከማን ጋር ስምምነት አድርጎ ይሁን ? እኛ እስከምናውቀው መጅሊሱ ከመንግስት ጋር ያደረገው ስምምነት የለም ። የመጅሊስ አመራሮች የአሕባሽ የሱፍይ የኢኽዋንና የነሲሓዎች ጥምር ነው ። የድሮዎቹ የሰው ሸይጣን የተባሉትም በአሁኑ መጅሊስ ላይ አሉ ። ታዲያ ሳዳት ድሮ ነበር ትክክል ወይስ አሁን ? ወይስ አልተቀየረም በነበረበት አቋም ላይ ነው ?
የሱልሕ ሁደይቢያውን መልስ በክፍል ሶስት የሱልሕ ሁደይቢያ ስምምነት ለዝንባሌ መገልገያ መረጃነት ላይ ይጠብቁ ።

ክፍል አንድን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/bahruteka/5221

ክፍል ሁለትን ደግሞ
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

https://t.me/bahruteka/5229

አላህ ሐቅን አውቀው ከሚፀኑት ጋር ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka


Репост из: የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
ስህተት ከማንም ይከሰት ስህተት ከመሆን አያስወጠውም ግን ለምን ይሆን ሱዑዲን የሚጠሏት

እንደምንሰመው እና እንደምናነበው የተለያዩ የጠላት ቀስቶች ወደዚች የተከበረች ምድር ይወረወራሉ ግን ለምን❓

➥ምክንያቱም ሱዑዲየህ ማለት በውስጧ የቀብር አምልኮ ለፋጡራን አምልኮ መስጠት የሌለባት ሀገር ስለሆነች
➥ምክንያቱም እሷ-በቁርአን እና በሀዲስ ስለምትመራ በዚች ሀገር ውስጥ ኢንቲኻብ(election)፣ፓርላማ፣ፓርቲ፣የምእራባዊያን ህግጋቶች የሚባሉ ነገሮች በጭራሽ ስለሌሉ
➥ምክንያቱም የነሷራ እና የአይሁድ የሌሎችም እምነት በዚች ሀገር ተቀባይነት ስለሌላቸው
➥ምክንያቱም እሷ-ለዲን እውቀቶች እና ለዑለማዎች አሳቢ ሀገር ስለሆነች ለዚህም ሲባል የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችን እና ኮሌጆችን ገንብታ እና አዘጋጅታ ከተለያዩ ሀገራት ተማሪዎችን ትቀበላለች።

أما أعداء المملكة العربية السعودية🇸🇦
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
ይሁዳ፣ነሷራ፣ራፊዷህ፣ኸዋሪጅ፣የኢኽዋን ጥርቅም በየዐይነታቸው የሚጠሏት እሷ የተውሂድ ሀገር ስለሆነች ብቻ ነው።

እንጂማ የትክክለኛ እምነት ባለቤቶች እኮ እሷ ከወንጀል ጥብቅ የሆነች ሀገር ናት አላሉም ለምትፈጽመውም ስህተት አላጸደቁም አውገዘዋል የሸኽ ፈውዛንን እና የሌሎችንም ትክክለኛ ዑለማዎች እንዴት የተወገዘን ነገር እንዳዎገዙ አዳምጥ!።እንዲህ ከመሆኑ ጋር እሷ እኮ ብቻኛ የሆነች ከማንኛውም ሀገር በበለጠ መልኩ ለተውሂድ እና ለሱና ተቆርቋሪ የሆነች ሀገር ናት።

እኛ ስህተት አትፈጽምም እያልነ አይደለም ልትፈጽም ትችላለች ታዲያ ይህ ስህተት ሲፈጸም ከትክክለኛ እምነት ባለቤቶች ምንድን ነው የሚጠበቀው?

➫➫➫
➀የእውቀት ባለቤቶች በሸሪዐህ መርህ መልኩ መልስ ይሰጣሉ ይመክራሉ።

➁በኛ ላይ የሚጠበቀው እነሱ ለወንጀል ተጋላጭ ስለሆኑ አሏህ እንዲያስተካክላቸው ዱዐእ ማድረግ ነው።ልክ ሰለፎቻችን ሲፈጽሙት እንደነበረው
يقول الفضيل بن عياض: (لو أن لي دعوة مستجابة ما جعلتها إلا في السلطان).
ለኔ ተቀባይነት ያላት ዱዐእ ብትኖረኝ (ልክ እንደመልእክተኞች ማለቱ ነው) በሙስሊሞች ጉዳይ ላይ በተሾመ ባለስልጣናት እንጂ ለሌላ አላደርጋትም
...ሌሉችም ቀደምቶች እንዲህ ነበሩ

➫እነዚህ ደጋግ ቀደምቶቻችን ከሙስሊሞች ባለስልጣናት ጋር አስመልክቶ የነበራቸው ሁኔታ እንዲህ ነበር። ከልጆቻቸው፣ከሚስቶቻቸው፣ከቤተሰቦቻቸው አስበልጠው ለባለስልጣናቶች ነበር ዱዐቸው
ይህም ከአህሉ-ሱና መሰረቶች አንደኘው መሰረት ነው።

በኛ ዘመን ያሉ የተውሂድ እና የሱና ጠላቶች ግን ሱዑዲያ የሆነ ስህተት ላይ ስትወድቅ አቧራ ያስነሳሉ ለሽርክ ለቢድዐ ሲሆን ደግም ምላሶቻቸውን ይለጉማሉ፣የዱሪህ አምልኮ መጣራቀሚያ እና የፊልም መነሃሪያ የሆነችውን ቱርክ በአድናቆት ይሰቅላሉ
يا سبحان الله❗️ اين ذهب عقول هؤلاء(جماعة الإخونجنية ومن اقتفى اثرهم) .أفلا يتوبون الى الله ويستغفرونه.

📢 الفرق بين السعودية والتركيا كما بين السماء والأرض

➂ሸሪዐው ጥሩ ባለው ነገር ሲያዙን እሺ መርሃባ ብለን መታዘዝ ነው።በሌላ በኩል ቢመቱንም፣ገንዘባችን ቢቀሙንም፣ቢበድሉንም በሀዲሱ እንደመጠው

አንተ ሱዑዲን የምትጠለው! ምንም ብትጠላት የዓለም እምብርት የሆነችው ከዕበህ የምትገኘው በሷ ነው ለከዕበህ መቼም ጀርባህን ሰጥተህ አትሰግድ!

ከጠላቶቿ ተንኮል እና ከመጥፎ ነገር አሏህ ሱዑዲን ይጠብቅልን!
እና ሸሪዐችንን ተጥቢቅ ለማድረግ የሚሞክሩትን ሀገር
ሁሉ አሏህ ያግዛቸው!

✍️Join ➘➘➘

https://t.me/sead429


Репост из: Bahiru Teka
👉 መገላለጥና አደጋው
♨️♨️♨️♨️

➴ ከዚህ የተጠለ ➴➴➴
https://t.me/bahruteka/5557

⛱ የሴት ልጅ አለባበስ አላህ ባስቀመጠው መመሪያ ካልተገደበና ልቅ ከተደረገ በምድር ላይ ለሚንሰራፉ ጥፋቶች ምክንያት ይሆናል። ሴት ልጅ ክብር የሆነ ገላዋን ኢስላም ባስቀመጠላት የክብር አለባበስ ካልጠበቀችው የሚቸረቸር ሸቀጥ ነው የሚሆነው።

🔎 ምእራባዊያን ሳይወዱ በግዳቸው የሴትን ልጅ ክብርነት ኢስላም እንዲቀበሉ ሲያደርጋቸው አዛኝ መስለው ራቁቷን እንድትሆንና እንድትረክስ «የሴት ልጅ ነፃነት» በሚል ማላዘን ጀመሩ። ይህን ጩኸታቸው ደግሞ አንዳንድ ከእስልምና ስሙን እንጂ የማያውቁ ምስኪኖች ያስተጋቡታል።
    
🏝 ስሙን ለሰው አወረሰው እንዲሉ የራሳቸውን በሴት ልጅ ላይ የነበራቸው ንቀትና ቦታ ያለመስጠት ወደ እስልምና በማስጠጋት ኢስላም ሴትን የሚበድልና የሚጨቁን ለማስመሰል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ይህ ድካማቸው ኢስላምን ለሚያውቅ ከንቱነታቸውን ከማረጋገጥ ያለፈ ሚና አይኖረውም።
    
🔍 በጣም የሚያሳዝነው ግን በአሁኑ ጊዜ አብዛኛው ሙስሊም እህቶቻችን በምእራባዊያኑ ወጥመድ የገቡ ይመስላል። የክብር ማማ ላይ ያስቀመጣቸውን ኢስላም አስተምሮ ትተው የውርደት ካባ ሊያከናንቧቸው የሚሯሯጡ የኢስላም ጠላቶችን ሽንገላ አምነው ተቀብለው ስራ ላይ እያዋሉ ነው። ሊፕስቲክ ተለቅልቀው፣ ሜካብ ተቀብተው በጉርድና በታይትም ጭምር አደባባይ የሚወጡ ሙስሊም ሴቶችን ማየት የተለመደ ሆኗል።
👉 የተሻሉ ከተባሉ ጠባብና ቅርፅን ከፋፍለው የሚያሳዩ ከሩቅ እዩኝ የሚሉ የሚመስሉ ልብሶችን ለብሰው ምን ይሉት ይሁን የማይታወቅ ከፊት ለፊት ግማሽ ፀጉራቸውን የሚያሳይ ሻርፕ ነገር ጣል ያደርጋሉ። ከዚህ በጣም የከፋው ደግሞ ሙስሊም ማህበረሰብ የሚበዛበትና የከተማዋ እምብርት የሚባሉ አካባቢዮች ላይ በሀብታም ነጋዴ ሚስቶች ዙሪያ የሚታየው ነው። እነዚህ አካላት ዘመናዊ መኪና ይዘው ገቢና ያስቀመጧት ሚስታቸው ከገቢና ስትወርድ ሌላውን ተከተለኝ የምትል ነው የሚመስለው። የሱ ሚስት ሆኗ ሳለች አለባበሷ ግን የሌላ ያስመስላታል። ይህ ነጋዴ ምናልባት ሐጅ እገሌ የሚባል ሊሆን ይችላል።‼

➩ አብዛኛው ከተማችን ላይ ከጎረምሳ ጋር የሚታዩ ለብሰዋል እንዳይባል ራቁታቸውን የሆኑ አለበሱም እንዳይባል ጨርቅ በላያቸው ላይ የጣሉ ሙስሊም ሴቶች የኛ ሚስቶች፣ ልጆች፣ እህቶች ናቸው የሚሆኑት ነገር ግን እኛ እንዳላየን ሆነን ነው የምናልፈው። የዚህ አይነቱ ሙንከር ማስቆም ካልቻልን ልንጠላው ይገባል። ዱዓቶች፣ ኡስታዞች፣ ኢማሞች፣ ዑለሞች ይህን ነገር ካላወገዙ አላህ በወረርሽኝ፣ መድሃኒት በሌለው በሽታና በተለያዩ መቅሰፍቶች ህዝቡን ይቀጣል።
👌 ይህን አስመልክተው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፦

🏖 "إن الناس إذا رأوا المنكر فلم يغيروه أوشك أن يعمهم الله بعقابه"
📚 أخرجه الترمذي بسند حسن صحيح

"ሰዎች መጥፎ ነገር ሲሰራ አይተው ካልቀየሩት አላህ በቅጣቱ ሊያጠቃልላቸው ይደርሳል።"

አላህ አውቀው ከሚተገብሩ ባሮቹ ያድርገን

https://t.me/bahruteka


Репост из: Bahiru Teka
👉 መገላለጥና አደጋው
♨️♨️♨️♨️

🏝 እንከን የለሹ የኢስላም አስተምሮ ለሴት ልጅ ክብር በማጎናፀፍና አንገቷን ከሰው እኩል ቀና አድርጋ እንድትሄድ በማድረግ የመጀመሪያው መለኮታዊ የህይወት መመሪያ ነውየምእራቡ አለም ሴት ልጅ ሰው ነች ወይስ እንሰሳ እያለ ጉባኤ ያደርግ በነበረበት የጨለማ ዘመን ነው ኢስላም በማያሻማ መልኩ ከሰባት ሰማይ ከዐርሹ በላይ መለኮታዊው የአላህ ቃልን መሰረት በማድረግ በመልካም ስራ፣ በኢማን፣ በመጪው ዐለም ምንዳ ከወንድ እኩል መመሪያ ውስጥ በማስገባት በአደባባይ ያወጀው ።

👉 ታዲያ ኢስላም ለሴት ልጅ እንዲህ አይነት ክብር ሲያጎናፅፍ ልትከተላቸው የሚገቡ መርኾችን በማስቀመጥ ነው። ሴቷን ብቻ ሳይሆን ወንዱንም ጭምር ህይወቱ በመለኮታዊው የአላህ መመሪያ እንዲመራ አዟል። በመሆኑም ሙስሊሞች ከአምልኮ ተግባራቸው በተጨማሪ አለባበሳቸውም ምን መምሰል እንዳለበት አስተምሯል። የሴት ልጅ አካል ከወንዱ በተለየ መልኩ ለተቃራኒ ፆታ መስህብ የሆነ በመሆኑ አለባበሷ ይህን የሚከላከል እንዲሆን መስፈርት አስቀምጦ ለሚተገብረው ምንዳ በመስጠት አሻፈረኝ ላለ ቅጣት መኖሩን ደንግጓል።

👌 ከእነዚህ ውስጥ የሚከተሉትን እንደማሳያ እንመልከት፦

🏝 «وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَىٰ ۖ وَأَقِمْنَ الصَّلَاةَ وَآتِينَ الزَّكَاةَ وَأَطِعْنَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ إِنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيُذْهِبَ عَنكُمُ الرِّجْسَ أَهْلَ الْبَيْتِ وَيُطَهِّرَكُمْ تَطْهِيرًا»
📚 الأحزاب ٣٣

🏝 "በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ። ሶላትንም በደንቡ ስገዱ። ዘካንም ስጡ። አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ። የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ ! አላህ የሚሻው ከእናንተ ላይ እርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው።"

🏝 «يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا»
📚 الأحزاب ( ٥٩ )

🏝"አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።"

🏝 «وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ»
📚 النور ( ٣١ )

🏝 "ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ። ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ። ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ

🏝 «وَالْقَوَاعِدُ مِنَ النِّسَاءِ اللَّاتِي لَا يَرْجُونَ نِكَاحًا فَلَيْسَ عَلَيْهِنَّ جُنَاحٌ أَن يَضَعْنَ ثِيَابَهُنَّ غَيْرَ مُتَبَرِّجَاتٍ بِزِينَةٍ ۖ وَأَن يَسْتَعْفِفْنَ خَيْرٌ لَّهُنَّ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ»
📚 النور ٦٠

🏝 "ከሴቶችም እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ተቀማጮች (ባልቴቶች)፤ በጌጥ የተገለፁ ሳይኾኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡ ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው።"

➴➴ ቀጣዩን ለማግኘት ↙️
https://t.me/bahruteka/5557


Репост из: አቡ ሀሳን abu hessan أبو حسان
🏝 ታላቅ የሙሃዶራ ፕሮግራም!

الـسلام عليـكـم ورحـمـة الله وبــركاتـه

🔎 የተከበራችሁ ወንድም እህቶቻችን እነሆ በአሏህ ፍቃድ የፊታችን ቅዳሜ ማለትም በቀን 14/3/2017 ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።

👉
በአላህ ፍቃድ እጅግ ብዙ እውቀት የሚቀስሙበት ፕሮግራም ነውና ወዳጅ ዘመድዎን ጋብዘው በግዜ ይገኙ!

🪑 ተጋባዥ እንግዶቻችን፦
🎙
ሸይኽ አብዱል`ሐሚድ ብን ያሲን አቡ አብዱልሃሊም አላህ ይጠብቃቸው

ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 3፡00  ጀምሮ

🕌 ቦታ፦ በዋቸሞ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ  (ዳሩል ሂጅረተይን መስጅድ)

🏝 ግዜያችንን ለዲናችን!!!
                                                                  🕋
ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ #ስነ_ምግባር ነው!!!

👉 for further information join us on telegram Chanel
👇👇👇
https://t.me/WCUMSJ2015

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


አምር ብን ቀይስ “ሰዎች ወደዝንባሌ መከተል ያስገደዳቸው ምንድን ነው?” በማለት ኢብን ኡተይባንቨ ጠየቅሁት፡፡ እርሱም  “ክርክር ነው”  በማለት ምላሽ ሰጠኝ፡፡  

5-በፈትዋ ላይ መዳፈር

አንተ ገና ተማሪ በመሆንህ ፣ ፈትዋ ለመስጠት አትዳፈር፡፡

ሶሃቦች ጥያቄ ሲቀርብላቸው  መልሱን ወደ ወንድሞቻቸው ማስተላለፍ ይወዱ ነበር፡፡

አብዱረህማን ብን አቢለይላ የሚከተለውን ተናግሯል ፡

"أدركت عشرين ومائة من أصحاب النبي صلى الله عليه وسلم من الأنصار ، إذا سئل أحدهم عن الشيء أحب أن يكفيه صاحبه" أخرجه الدارمي 135

አንድ መቶ ሀያ የሚሆኑ ከአንሷር የሆኑ የረሱል ሶሃቦችን አግኝቻለሁ፡፡ ስለአንድ ነገር ከተጠየቁ በጓደኛው (መልስ) ይብቃቃ ነበር፡፡”

6-ባወቀው አለመስራት

የእውቀት አላማው ለተግባር ነው፡፡  አንድ ተማሪ የእውቀትን ፍሬ ካጠፋው፡፡ ይህንን ፍሬ መልሶ ለማግኘት ጥረት እንኳ ቢያደረግ በቀላሉ ማግኘት አይቻልም፡፡  

በእውቀታቸው መስራትን በተው ሰዎች ላይ  
አላህና ረሱል ﷺ  በጥብቅ አውግዘዋል፡፡

وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ الَّذِي آتَيْنَاهُ آيَاتِنَا فَانسَلَخَ مِنْهَا فَأَتْبَعَهُ الشَّيْطَانُ فَكَانَ مِنَ الْغَاوِينَ
وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَاهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُ أَخْلَدَ إِلَى الْأَرْضِ وَاتَّبَعَ هَوَاهُ ۚ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ الْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ۚ ذَّٰلِكَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ فَاقْصُصِ الْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

"የዚያንም ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን ከጠማሞቹም የኾነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው፡፡ በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡"

(አእራፍ ፡ 175-176)

 
https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

 


ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ

 ክፍል - 11

የእውቀት እንቅፋቶች

በዚህ ክፍል እውቀት ፈላጊዎቸ  - በተለይም ጀማሪዎች  - ልፋታቸውን ከንቱ  ፣ በእነርሱ ላይ ወንጀል እንዲረጋገጥ የሚያደርጉ ለእውቀት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን በአላህ ፈቃድ ማስጠንቀቅ እንፈልጋለን ፡  

1- እውቀት አለኝ ብሎ በሰዎች ላይ መኩራት

አጫጭር እና ረጃጅም የሆኑ ኪታቦችን በመቅራቱ በነፍሱ መደነቅ ፣ ወንድሞቹን በንቀት አይን መመልከት፡፡
የእውቀት ትሩፋቱ ለባለቤቱ የአላህን ፍራቻ ማውረሱ ነው፡፡

ኢብን መስኡድ የሚከተለውን ተናግረዋል

"ليس العلم بكثرة الرواية ولكن العلم الخشية"

“እውቀት ብሎ ማለት (ሐዲስ) በብዛት በመዘገብ (ወይም በማውራት) አይደለም ፣ እውቀት ብሎ ማለት አላህን መፍራት ነው”

(አቡኑዓይም "ሂልያ" በተባለው ኪታብ : 1/131 ላይ ዘግቦታል)

ይህ ኩሩ ሰው ከምን እንደመጣ ወዴት እንደሚሄድ ጠንቅቆ ቢያውቅ ኖሮ ኒያውን አስተካክሎ ከዚህ በሽታ ለመዳን ጥረት ባደረገ ነበር።
የእውቀት አስፈላጊነቱ ባወቁት ለመተግበር ፣ በእርሱ ሙስሊሞችን ወደቀጥተኛው መንገድ ለመምራት ነው፡፡

ሀሰን አልበስርይ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡

"إنما الفقيه الزاهد في الدنيا ، البصير بدينه ، المداوم على عبادة ربه عز وجل"

“(በሸሪዓ) አዋቂ የሚባለው ለዱንያ (ከፍተኛ) ትኩረት የማይሰጥ ፣ በዲኑ አዋቂ  ፣ በጌታው አምልኮ ዘውታሪ የሆነው ነው፡፡”

(አቡ ኑዓይም  “አልሂልያ” በተባለው ኪታቡ : 1/147 ዘግቦታል)

2-ከሙብተዲእ እውቀትን መውሰድ

ሙብተዲዕ የዲን ተቃራኒ የሆነውን ለነፍሱ ይወዳል፡፡ አንደበቱ ባይናገረውም ባህሪውም “አላህ ዲኑን አላሟላውም ፣ ሙሐመድም ዲኑን ሙሉ በሙሉ ለኡማው አላደረሱም፡፡” የሚል ነው።

ባህሪው እንደዚህ አይነት ከሆነ ሰው ጋር መቀመጡ ጉዳት እንጅ ጥቅም አያስገኝም፡፡ አብሮት የተቀመጠውን አካል ቢድዓ ላይ ባይጥለው እንኳ ቢያንስ በዲኑ ላይ ጥርጣሬ እንዲኖርበት ያደርጋል። የዋለለ አቋም እንዲይዝ ያደርገዋል፡፡

ነብዩ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡

"إنما مثل الجليس الصالح ، وجليس السوء كحامل المسك ، ونافخ الكير ، فحامل المسك إما أن يحذيك ، وإما أن تبتاع منه ، وإما أن تجد منه ريحا طيبة ، ونافخ الكير إما أن يحرق ثيابك ، وإما أن تجد منه ريحا خبيثة"

ደግ ከሆነ ሰው ጋር የሚቀመጥና ክፉ ሰው ጋር የሚቀመጥ ሰው ምሳሌው ፣  ልክ ሽቶ እንደ ተሸከመ  እና ወናፍ እንደሚነፋ ሰው አምሳያ ነው፡፡ ሽቶ የተሸከመ ሰው  ከእርሱ ይሰጥሃል  ወይም ከእርሱ ትገዛለህ ወይም ከእርሱ መልካም ሽታ ታገኛለህ፡፡ ወናፍ የሚነፋ ሰው ደግሞ ልብስህን ያቃጥላል ወይም ከእርሱ ቆሻሻ  ሽታ ታገኛለህ፡፡”

(ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ኢማሙ ነወውይ የሚከተለውን ተናግረዋል፡

“በዚህ (ሐዲስ) ከደጋጎች ጋር መቀመጥ ያለውን ደረጃ ነው፡፡  ከመልካም ፣ ትሁት ፣ ስነምግባራቸው የተከበረ ፣ አላህን የሚፈሩ የእውቀት እና የአዳብ ባለቤቶች ጋር መቀመጥ ያለውን ደረጃ እንማራለን፡፡ ክፉ ከሆኑ ሰዎች ፣ ከቢድዓ ባለቤቶች ፣ ሰውን ከሚያሙ ፣ ወይም አመጸኛነቱና ባጢሉ ከበዛ ሰው እና የተለያዩ ነውሮች ካላቸው ሰዎች ጋር  መቀመጥን ደግሞ ከለከለ”

(ሸርህ ሶሂህ ሙስሊም ፡ 5/484)

ኢብን መስኡድ የሚከተለውን ተናግሯል ፡

"لا يزال الناس بخير ما أخذوا العلم عن الأكابر ، وعن أمنائهم وعلمائهم ، فإذا أخذوا من صغارهم وشرارهم هلكوا" أخرجه ابن المبارك في "الزهد" 815

“ሰዎች ከታላቆች ፣ ከታማኞች ፣ ከአሊሞች  እስከያዙ ድረስ በመልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም ፤ ከታናናሾች እና ከተንኮለኞች እውቀትን ከያዙ ደግሞ ይጠፋሉ፡፡”

 ኢብን አል ሙባረክ፣ “ከታናናሾች” ማለት ከቢድዓ ባለቤት ማለት ነው ብሎ ተርጉሞታል።

የእውቀት ባለቤቶቸ ፡ ከቢድዓ ባለቤት ጋር መቀመጥን አውግዘዋል፡፡ ከእነርሱ እንዴት እውቀት ይወሰዳል?

ሀሰን እና ኢብን ሲሪን የሚከተለውን ተናግረዋል ፡

"لا تجالسوا أصحاب الأهواء ، ولا تجادلوهم ، ولا تسمعوا منهم" أخرجه الدارمي (401) بسند صحيح

“የልብ ወለድ ባለቤቶች ጋር አትቀመጡ ፣ አትከራከሯቸው ፣ ከእነርሱም አትስሙ”

3-ቡድንተኛነት

በዘመናችን ያለው በሽታ የቡድንተኛነት በሽታ ነው፡፡

አላህ የሶሀቦችን ባህሪ እንደሚከተለው ተናግራል

مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ

"የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡"

(ፈትህ ፡ 29)

እውቀትን በመፈለግ ነፍስን ማጥራት  ፣ በልብ ውስጥ አላህን መፍራት ይገኛል፡፡  ወደ ቡድንተኛ ፣  ወደዘረኝነት ዳእዋ ማድረግ የእወቀትን ፍሬ ያበላሻል፡፡

ቡድንተኛነት ረሱል ﷺ የተዋጓት መከፋፈል ነች፡፡

ቡኻሪ  ጃቢርን  - ጠቅሰው የሚከተለውን ትክክለኛ ሐዲስ ዘግበዋል፡-

ከነብዩ ﷺ ጋር ዘመቻ ወጣን፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙሐጅሮች አብረዋቸው ነበሩ፡፡   ከሙሀጅሮች መካከል አንዱ አንሷሩን  መታው፡፡ አንሷሩ በጣም ተቆጣ፡፡ “አንሷሮች ሆይ!” በማለት ጥሪ አደረገ፡፡ ሙሐጅሩ ደግሞ “ሙሐጅሮች ሆይ!” በማለት ጥሪ አደረገ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ወጡ፡፡ የሚከተለውንም ተናገሩ ፡-

“የጃሒልያ ባለቤቶች ጥሪ ምንድነች?!” በማለት ጠየቋቸው፡፡ ከዚያም “ምንድን ነው ሁኔታቸው?” በማለት ተናገሩ፡፡ ሙሐጅሩ አንሷሩን መምታቱ  ተነገራቸው፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ንግግር ተናገሩ፡-

"دعوها فإنها خبيثة"

“ተዋት እርሷ ቆሻሻ (ጥምብ) ነች፡፡”

ሙስሊም ከእርሱ በመያዝ የዚህ ተመሳሳይ ሐዲስ ዘግቧል፡፡

ወገንትኝነታችን ለረሱል ፣  ለሱናቸው ፣ ለሱና ባለቤቶች መሆን አለበት፡፡ 

ሸይኽ አል'አልባኒ “አል'ፈታዋ አል'ኡለማእ አል'አካቢር” በሚባለው ኪታብ ከገጽ (97 - 98) ላይ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

 “ የ 'ሰለፍያ' ዳዓዋ በማንኛውም መልክ ቡድንተኛነትን ትዋጋለች፡፡  የዚህ ምክንያት  ደግሞ ግልጽና ግልጽ ነው፡፡ የፊረቆች የዳዕዋ ጥገኝነት ከወንጀል ንጹህ ወዳልሆኑ አካላት ሲሆን  የሰለፍዮች የዳዕዋ ጥገኝነት ግን ከወንጀል ጥብቅ ወደሆኑት የአላህ መልእክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም  - በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ 'ሰለፍይ' ነኝ ብሎ የሚሞግት አካል  ቁርዓንና ሐዲስን መሰረት አድርጎ  በ 'ሰለፎች' ጎዳና ሊጓዝ ይገባዋል፡፡  አለበለዚያ ስም ብቻውን የተጠሪውን ማንነት ሊወክል አይችልም፡፡”

4-በሸሪዓ ጉዳዮች መከራከር

በሸሪዓ ጉዳዮች መሟገትን ፣ መከራከርን ተጠንቀቅ፡፡ ምክንያቱም መከራከር ፣ መጨቃጨቅ  የሙብተዲዖች መንገድ ነው፡፡

ኡመር ኢብን አብዱል አዚዝ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡

"من جعل دينه غرضا للخصومات أكثر التنقل" أخرجه الآجريي في "الشريعة" 56

“እምነቱን የክርክር ቦታ ያደረገ መገለባበጥን ያበዛል”


🌐 ወሳኝ መዳመጥ ያለብት

✅ ሳዑዲ ላይ በተፈፀመው ጉዳይ  ላይ ሰፍ ያለ ማብራሪያ

↩️ من فساد عقيدتك وانتكاس فطرتك أن تثور وتغضب بسبب العري والفسوق في السعودية وأما الشرك بالله حول القبور في بلدك فليس شيء عندك

🎙 በኡስታዝ ኢሊያስ አወል አቡ ሷሊህ አል ኡሰይሚን አላህ ይጠብቀው!

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞
@AbuImranAselefy


Репост из: Abu abdurahman
#ከፈተና_ለመራቅ ከሚረዱ _ምክንያቶች መካከል ፡-

1- ቁርዓንን በመቅራት በመሀፈዝ በመስራት መቀጣጨት . ባጭሩ ለቁርዓን ግዜ መስጠት

2- እውቀትን በመፈለግ ላይ መጠመድ

3- መልካም ስራዎችን ማብዛት .

4- በዲናችን ላይ እንድንፀና አሏህን ሆሌም ፅናትን መለመን.

5- የመልእክተኛውን ﷺ የህይወት ታሪክ ማሰብ እና ማስተንተን.

6–ቀደምቶች በፈተና ግዜ ይመርጡት የነበረውን መንገድ መውደድ

7- ጥሩ ጓደኞችን ማፍራት

8- በዲን ላይ ሆኖ መታገስ

9_ ስሜተኝነትን መራቅ ከስሜታችን ጋር አለመነጋር

10 ፈተናው ያለበትን ቦታ መራቅ እሰከተቻለ መራቅ ከፊትናው አለመቀራረብ

አላህ በዱንያም በመጨረሻውም አለም ላይ እንዲያፀናን እንለምነዋለን...

https://t.me/abuabdurahmen


🟢ማስጠንቀቂያ ለኢኽዋኖችና ለአጋሮቻቸው

በሀገራችን የኢኽዋን አንጃ መሪዎችና ተመሪዎች ብዙ የዲን መሰረቶችን እየናዱ ጉድ አስብለዋል:: ያሻቸውን ክልክል (ሀራም) ያሸቸውን የተፈቀደ (ሀላል) ሲያደርጉ ጭፍን ተከታዮችና አጋሮቻቸው ደንዝዘዋል::

🟢ጥያቄዎች
👉የሚከተሉትን የአላህን ንግግሮች አልተረዳችሁምን ?!

# يَقُولُ الله تَعَالَى﴿وَلا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَذَا حَلالٌ وَهَذَا حَرَامٌ لِتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ}
قال ابن كثير: "وَيَدْخُلُ فِي هَذَا كُلُّ مَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لَيْسَ لَهُ فِيهَا مُسْتَنَدٌ شَرْعِيٌّ،
أَوْ حَلَّلَ شَيْئًا مِمَّا حَرَّمَ اللَّهُ، أَوْ حَرَّمَ شَيْئًا مِمَّا أَبَاحَ اللَّهُ"

# { اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ }

👉ጣጉት ምን እንደሆነ ቀጣዪን የኢብኑ ቀይምን ገለፃ አታውቁትምን ?!
-: (وَالطَّوَاغِيتُ كَثِيرُة، وَرُؤُوسُهُمْ خَمْسَةٌ: إِبْلِيسُ لَعَنَهُ الله، وَمَنْ عُبِدَ وَهُوَ رَاضٍ، وَمَنْ دَعَا النَّاسَ إِلَى عِبَادَةِ نَفْسِهِ، وَمَنْ ادَّعَى شَيْئًا مِنْ عِلْمِ الْغَيْبِ، وَمَنْ حَكَمَ بِغَيْرِ مَا أَنْزَلَ الله).

👉እወቁ ተጠንቀቁም: ህግ አውጪው አላህ እንጂ የመጅሊስ መሪዎች አይደሉም::
👉ሁሉም የመሰለውን ሳይሆን አላህ የተደነገገው ዲን ይከተል ::

http://t.me/Abuhemewiya


#ከዐቂዳህ_መበላሸት፤ከፍጥረትህ መገላበጥ የተነሳ ሳኡዲ በመራቋቷና (እርቃን ላይ በመሄዷ)፤ ወንጀል ላይ በመውደቋ ምክንያት ትቆማለህ፤ትቆጣለህ። ሀገርህ ላይ ባለ ቀብር ዙሪያ ግን በአሏህ ላይ ሲጋራበት አንተ ዘንድ ምንም ነገር የለም (ምንም አይመስልህም)።


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ከሱና በኋላ ቢድዐ እንጂ የለም!!
———
ኢብኑ ቁዳመህ አልመቅዲሲይ (ረሂመሁላህ) ኢንዲህ ይላሉ: -
“ ከሰለፎቹ መንገድ ሌላን መንገድ የተጓዘ ወደ መጥፊያው ታደርሰዋለች፣
ከሱና ያዘነበለ በእርግጥ ከጀነት አዘንብሏል፣
አላህን ፍሩት! ለነፍሳችሁ ፍሩ፣ ነገሩ ከባድና ውስብስብ ነው፣ ከጀነት በኋላ ጀሀነም እንጂ ምን አለ?
ከሀቅ በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ?

ከሱና በኋላም ቢድዓ (በሃይማኖት ፈጠራ) እንጂ የለም!! ”
[ተህሪም አን-ነዘር ፊኩቱቢል ከላም 71]
✍🏻ኢብን ሽፋ #join ⤵️
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Показано 20 последних публикаций.