ክርስቲያን አልሄድሁ፣ ሃይማኖት አልተማርሁ፣ ምግባርም አልሠራሁ፣ ሰንበትንም አላከበርሁ፣ የተራበ አላበላሁ፣ ለሥጋዬ ስጥር ስግር ስላፋ ስማስን ነበርሁ እንጂ፡፡ እንደ እናንተ ያለም መኖሩን አይቼ ሰምቼም አላውቅም›› ትላቸዋለች፡፡ ከዚህ በኋላ መላእክተ ብርሃን ‹‹ወይ ነፍስ! እንዴት ለደገኛው መንግሥተ ሰማያት ተፈጥረሽ ለገሃነመ እሳት ሆንሽ? በሥላሴ አምሳል ተፈጥረሽ የዲያብሎስ መረገጫ የሰይጣናት መራወጫ ሆንሽ!?›› ብለው አዝነው አልቅሰው ይሔዳሉ፡፡
(እዚህ ጋር አባታችን አባ ኪሮስ የጻድቅ ሰውና የኃጥእ ሰው ነፍስ ከሥጋ ስትለይ በጌታችን ፈቃድ በግልጽ እንደተመለከተ ከገድሉ አውጥተን እንነግራችሁ ዘንድ እንወዳለን፡- ‹‹ጌታችን ለአባ ኪሮስ ‹የነፍስን ከሥጋ መለየት ታይ ዘንድ ወደ አንዲት አገር ትሔድ ዘንድ አዝሃለሁ፣ ካየህም በኋላ ወደ በዓትህ ተመለስ› ብሎት ከእርሱ ተሰወረ፡፡ አባ ኪሮስም በአንደኛው ቀን ተነሥቶ ሲሔድ ከአንዲት ሀገር ደረሰ፡፡ በዚያም ፈጽማ የታመመች አንዲት ሴት አገኘና እርሷ ወዳለችበት ቤት ገባ፡፡ መላእክትን በአጠገቧ ሲመላለሱ ተመለከተ፡፡ በእጃቸው መሰንቆ የያዙ አሉ፣ የገነት አበባ የያዙም አሉ፣ ልብሰ መንግሥትም የያዙ አሉ፣ የጽድቅ ድባብም የያዙ አሉ፡፡ ሁሉም በአንድነት ‹ፈጽሞ ደስ ይበልሽ፣ ከመከራ ወደ እረፍት፣ ከችግር ወደ ብልጽግና ነይ!› ይሏታል፡፡ እንደግድግዳ ከበው ይህን ሲነጋገሩ ከመላእክት አንዱ ስሙ ገብርኤል የሚባል ወደእነርሱ መጣ፡፡ ‹በግድ እንለያት ዘንድ አላዘዘንምና ስለ እርሷ ምን ትላላችሁ! የገነትን አበባ አሽቷት እንጂ› አላቸው፡፡ እንዳዘዛቸውም አፈረጉ፡፡ ነፍስዋም በመዓዛ ገነት በተመስጦ ከሥጋዋ ተለየች፡፡ አባታችን አባ ኪሮስም መላእክትን ‹ነፍስ ከሥጋ ስትለይ እንዲህ ነውን?› አላቸው፡፡ መላእክትም ‹ኪሮስ ሆይ! እንዲህ አትበል፣ ይህ የምታየው ክብር ለጻድቃን ብቻ ነው፡፡ ለኃጥእ ሰው ግን መልአከ ሞት ከሠራዊቱ ጋር በሚያስፈራ ግርማ ይመጣባቸዋል፡፡ የእርሱንም ሥራ በዐይንህ ታይ በጆሮህም ትሰማ ዘንድ አግባብ አይደለም› አሉት፡፡ ይህንንም ነገር ነግረውት መላእክት ወደ ሰማይ ዐረጉ፡፡ አባ ኪሮስም የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ እያደነቀ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ኪሮስ ሦስት ቀን ቆይቶ ወደ ሀገር ወጥቶ ሔደ፡፡ መላእክተ ጽልመት የእሳት በትሮችን ይዘው ሲሽቀዳደሙ አየ፡፡ አባ ኪሮስም ደንግጦ የሚሆነውን ይረዳ ዘንድ ወደ እነርሱ ሔደ፡፡ በዚያም በጽኑ ደዌ የተያዘ አንድ ሰው ነበር፡፡ መላእክተ ጽልመት እንደግድግዳ ከበው በእሳት በትር ይደበድቡታል፡፡ ነፍሱንም ‹አንቺ ጎስቋላ ነፍስ ነይ ውጭ፣ እንደሥራሽም ዋጋሽን ተቀበይ…› እያሉ ይሰድቧታል፡፡ በዚህም ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ አባ ኪሮስን በእጁ ያዘው፡፡ ከድንጋጤም የተነሣ ነፍሱ ከሥጋው እንዳትለይ ከእራሱ እስከ እግሩ ጥፍር ድረስ በገነት አበባ አሸውና ‹…መጨረሻውን ታይ ዘንድ ጽና› አለው፡፡ ያንጊዜም መልአከ ሞት መጥቶ በዚያች ነፍስ ላይ መርዙን ተነፈሰባት፣ በአፉም ጎርሶ ውጦ አኝኮ መልሶ ተፋት፡፡ ሦስት ጊዜም መላልሶ እንዲህ አደረጋትና ለመላእክተ ጽልመት ሰጥቷቸው ሔደ፡፡ መላእክተ ጽልመትም ከእነርሱ ለአንዱ በጥፍሩ አሲዘው እስከ ሦስተኛ ሰማይ አውጥተው ወደ ምድር ጣሏት፡፡ ሦስት ጊዜም መላልሰው እንዲሁ አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ እንደሥራዋ ታገኝ ዘንድ ወደላይ አሳርገው ከእግዚአብሔር ፊት አደረሷት፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም አባታችን አባ ኪሮስን ‹የጻድቃንንና የኃጥአንን ሞት አይተሃልና ይህን አስተውል› አለው፡፡ አባ ኪሮስ ግን ከድንጋጤው የተነሣ ታመመ፣ ማናገርም ተሳነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ‹አባ ኪሮስ ሆይ! አንተም እንዲህ ትሆናለህን?› አለው፡፡ ይህንንም ብሎ በፊቱና በሁለቱ ጆሮው እፍ አለበት፡፡ ልቡንም በዳሰሰው ጊዜ ፍርሃትና ድንጋጤ ከእርሱ ተወገደለት፡፡ ወዲያም ቅዱስ ገብርኤል ወደላከው ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አባ ኪሮስም ፈጽሞ እያዘነ ወደ ‹…ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ፣ የማዝነው ለዚያ ሰው ብቻ አይደለም ለራሴም ነው እንጂ…› እያለ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡ በበዓቱም ሆኖ በዕለቱ ዘጠኝ እልፍ ይደግድ ጀመር፣ እንባውም እንደውኃ ይፈስ ጀመር፡፡ ጌታችንም ወደ እርሱ መጥቶ እስካረጋጋውና እስካጽናናው ቃልኪዳንም እስከሰጠው ድረስ እንዲሁ በታላቅ ተጋድሎ ኖረ፡፡)
መላእክተ ብርሃን ‹‹ወይ ነፍስ! እንዴት ለደገኛው መንግሥተ ሰማያት ተፈጥረሽ ለገሃነመ እሳት ሆንሽ? በሥላሴ አምሳል ተፈጥረሽ የዲያብሎስ መረገጫ የሰይጣናት መራወጫ ሆንሽ!?›› ብለው አዝነው አልቅሰው ይሔዳሉ ወዳልነው ነገር እንመለስ-ከዚህ በኋላ መላእክተ ጽልመት የእሳቱን መንዶ፣ የእሳቱን መጋዝ ይዘው መጥተው እንደ ግድግዳ ቆመው አስጨንቀው አስጠብበው ይጠይቋታል፡፡ ምን ብለው ይጠይቋታል? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ በማን ታመልኪ ነበር? የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን ታምኛለሽን?›› ብለው ይጠይቋታል፡፡ እርሷም ያልተማረች ከሆዷ በቀር ሌላ የማታውቅ ናትና ‹‹እኔስ የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን አላውቅም፡፡ ለሥጋዬ ስጥር ስግር ስላፋ ስማስን ነበርሁ እንጂ፣ ሃይማኖት አልተማርሁ፣ ምግባር አልሠራሁ፡ እናንተማ ወዳጆቼ ዘመዶቼ አይደላችሁምን? የመከራችሁኝን ሰምቼ ያዘዛችሁኝን ሠርቼ እኖር ነበር እንጂ›› ትላቸዋለች፡፡
የክፉ የኃጥእ ሰው ነፍስ መላእክተ ጽልመትን የት ታውቃቸዋለችና እንዲህ ትላቸዋለች? ቢሉ የክፉ ሰው ነፍስ እንደሆነች ገና በቁመናዋ ሳለች በህልምም በራእይም ከመላእክተ ጽልመት ጋር ገሃነመ እሳት እየወረደች ታይ ነበረችና ስለዚህ ‹‹አውቃችኋለሁ›› ትላቸዋለች፡፡ ቀድሞም አጋንንት ለእርሷ ያዘኑ መስለው ‹‹አንቺ ነፍስ ሰንበትን ብታከብሪ፣ ምጽዋት ብትመጸውቺ፣ ዓሥራት በኩራት ብታወጪ ቦታሽ ይህ ስለሆነ ምን ያደክምሻል? ይልቅስ ቅጠፊ፣ ስረቂ፣ ነፍስ ግደይ፣ ሰንበትን ሻሪ፣ ጾም ግደፊ፣ ጸሎት አቁሚ፣ ዋርሳ ውረሽ፣ ዝሙት ፈጽሚ… ይህንና የመሳሰለውን አድርጊ እያሉ ሲመክሯት ነበርና ስለዚህ ‹‹አውቃችኋለሁ›› ትላቸዋለች፡፡
ከዚኽም በኋላ መላእክተ ጽልመት ‹‹ለራስሽ አንቺ እገዛ እነዳ፣ እበላ እጠጣ፣ እለብስ፣ እደላደል፣ እቀማጠል ብለሽ እንጂ አንቺ ለእኛ ምን ውለታ ውለሽልናል? ቆርሰሽ አላጎረስሽን ጠልቀሽ አላጠጣሽን! አንቺ ኩሩ ትዕቢተኛ እንግዲህ ነይ ውጪ! በቁመናሽ የሠራሽውን የምግባርሽን ዋጋ ብድራቱን ክፈይ…›› እያሉ ራስ ራሷን እየቀጠቀጡ ያስጨንቋታል፡፡ ያስጠብቧታል፡፡ ‹‹ንዒ ፃኢ ከመ ትትፈደዪ ፍዳ አበሳኪ›› እንዳለ ድርሳነ ሰንበት፡፡ ከዚኽ በኋላ መልአከ ሞት ከአድማስ እስከ አድማስ ተስተካክሎ ቁሞ፣ ጥርሱን አግጦ ዐይኑን አፍጦ ይታያታል፡፡ ጥርሱም በመልአኩ ክንድ 88 ነው፡፡ የመልአኩ ክንድ አንዱ በሰው ክንድ 44 ነው፡፡ የአንድ ዐይኑ መቃድ ስፋት 3 ዓመት ከመንፈቅ ያስኬዳል፡፡ የ2ኛው ዐይኑ መቃድ ስፋት 3 ዓመት ከመንፈቅ ያስኬዳል፡፡ በጠቅላላው የሁለት ዐይኑ መቃድ 7 ዓመት ያስኬዳል፡፡ ቁመቱ ደግሞ ከምድር እስከ ሰማይ ነው፡፡ ከዚኽም በኃላ 3 ጊዜ ተራምዶ መጥቶ ከፊቷ ይቆማል፡፡ ያችም ኃጥእ ነፍስ በዚህ ደንግጣ ስትጨነቅ ተንፈንጥራ