🔴አስተርአእዮ በሰማይ ኮነ//♦️ማርያም ስምሽ ይጣፍጣል! ልዩ የእመቤታችን ዝማሬ♦️
#አስተርእዮ_ማርያም
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
አስተርእዮ ማለት ትርጓሜው "መታየት፣ መገለጥ" ማለት ነው
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሰረት አንድነቱም ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት እስከ ጥር መጨረሻ ያለው ዘመን አስተርእዮ በመባል ይታወቃል
የእመቤታችንም በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርዕዮ ውስጥ ስለሚከበር "አስተርእዮ ማርያም" ይባላል