🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
ቁ/275
የዕለተ ረቡዕ 29/7/1446 ዓ.ሂ ትምህርት
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽
🔗
https://tinyurl.com/yexcwhe6▪️1/ እኔ ባለ ትዳር ነበርኩ እና ከባለቤቴ ጋር ሀይድ ላይ እያለሁ ግንኙነት እናደርግ ነበር እና እኔ ስለ ዲኔ ምንም ግንዛቤ አልነበረኝም እሱ ግን ቁርኣን አክትሟል ግን የተረዳው አይመስለኝም እና አሁን እንደማይፈቀድ እያወቀ ይሁን ሳያውቅ ግንኙነት ያደረገኝ አላውቅም እኔ በጤናዬ ችግር ያመጣብኛል የሚል ስጋት እንጂ በዲን እንደማይፈቀድ አላውቅም እሱንም ለመጠየቅ አሁን ተለያይተናል አንገናኝም እና ከፋራ አለብኝ ወይ ካለብኝስ ከፋራው ምንድን ነው?
▪️2/ በኒካህ ላይ ዝሙት የሰራ ሰዉ የሸሪአ ህግ በሌለበት ሀገር ምን መደረግ ነው ያለበት በርግጥ ከወንጀሉ ተውበት አድርጓል ተፀፅቷል እና አሁን የሸሪአ ህግ ያለበት አገር ነው ያለው እና አሁን ባለበት አገር ተቀጥቅጦ መገደል አለበት? ካልሆነ ደግሞ ምን ማድረግ አለበት?
▪️3/ ኡስታዝ እኔ ጅልባብ ቤት ነው ምሰራው እና አንዳንድ እህቶች ኺማር ባትሸጪ የሚል አስታያየት ይሰጡኛል እና ከሸሪያው አንፃር ኺማር መሸጥ እንዴት ነው?
▪️4/ ባሌ በሁለት ፍች ሶስቱንም ፈትቼሻለሁ ብሎኝ ነበር መልሳ እንታርቅ አለኝ እኔ ኒካህ የለህም ወርዷል አልኩት ጥያቄ ፈጠረብኝ።
▪️5/ ሴት ያለ መህረም አንድ ቀን ከነለሊቱ የሚያስኬድ ጉዞ ሲባል ባሁኑ ዘመን በፕሌን ብቻዋን 6 ሰዓት እና ከዛ በላይ ያለን ጉዞ መሄድ ትችላለች ወይ?
▪️6/ በእስልምና ለትዳር ነው ተብሎ መጠናናት ተብሎ ሴትና ወንድ ጎደኛ ሆኖ ለአመታት ሚቆይ ነገር አለ እንዴት ይታያል? አንድ ወንድ ሚፈልጋትን ሴት በምን መልኩ ነው ሚጠይቃት እኔም አዲስ ሙሽራ ልሆን ነው ዱዓ አርጉልኝ።
▪️7/ ለሴት ልጅ ከአካባቢዋ ራቅ ያለ ዩኒቨርስቲ ለመማር መሄድ እና እዛው ሁና መማሯ እንዲሁም ቤተሰብ ለመጠየቅ መመላለሷ ከ ሸሪዓ አንፃር እንዴት ይታያል?
▪️8/ የኢሻዕ ሰላት ከሌሊት 6 ሰዓት በኃላ መስገድ አይቻልም ይላሉ እና ይህ ነገር ማስረጃ ይኖረዋልን?
▪️9/ ሱቅ ላይ ጥቁር የፀጉር ቀለም እና ካርታ መሸጥ እንዴት ይታያል?
▪️10/ አንድ ሰው ዘመድ ከመሆኑ ጋር በራሱ ጊዜ ያለምክንያት ቢርቀን እና በተደጋጋሚ ለማናገር ስንሞክር ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ ወይም የሚርቀን ከሆነ ከዛ ሰው ጋር መራራቁ ዝምድና መቁረጥ ይባላል?
▪️11/ ባለትዳር ነኝ ልጆችም አሉኝ ባለቤቴ ቤተሰቦቼን አያከብርልኝም ሲመጡም ደስተኛ አይደለም ለነሱ ጥሩ ቢመስልም ለኔ ግን አድሳቀቅ ነው እሚያደርገኝ ቤተሰቦቼም አይረዱኝ አኔም አላወራ ቅሬታ መፍጠር ስለማልፈልግ አሁን ላይ ግን ፍች መጠየቅ ፈለኩ በዚሁ ምክነያት ምን ይመክሩኛል?
▪️12/ አንዲት እህቴ ከባሏ ጋር ተፉተው ነበር 3 ወር ሳይሞላት ረጃእቱ ብያለሁ ብሎ ለዘመዶቿ ብር ሰጥቷል እሷ እኔ አልፈለገውም አለች እና ኒካሁ እንዴት ነው?
▪️13/ አንዲት ጓደኛዬ ዝምታ ታበዛለች እና ሰዎች ደግሜ ከኩራት ያዩታል እሷ ኩራትን አስባ አይደለም ተፈጥሮዋ ነው ከሸሪአ አንፃር እንዴት ይታያል?
🔹🔸🔹🔸🔹🔸
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ፔጆቻችንን ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🌐
https://zadalmead.com/✔️
https://telegram.me/ahmedadem✔️
https://facebook.com/yenegew✔️
https://www.youtube.com/@Zadul-Mead✔️
https://x.com/zadul__mead✔️
https://www.instagram.com/zadulmeadአላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197