ኤልሮኢ፡ (⚜ትምህርት⚜)
ወርሃ ፅጌ የእመቤታችን ስደት
የእናታችን የድንግል ማርያም ስደት ታሪክ
ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5 ያሉት ቀናተ, ሳምንታት "ወርሃ ፅጌ"በመባል ይታወቃል።ብዙዎች "ፆመ ፅጌ" ብለው ይጠሩታል ነገር ግን በቤተ ክርስቲያናች በፍትሃ ነገስት የተደነገጉት 7 አፅዋማት አሉ።
ይህ ወቅት ፆመ ፅጌ ለመባል በቤተክርስቲያናችን ቅኖተ መሰረት ከእነዚህ ከ 7ቱ አፅዋማት ጋር አልታወጀም ስለዚህም "ወርሃ ፅጌ እንላለን" ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በፈቃደኝነት የእመቤታችን ፍቅሯን ለመግለፅ ስደቷን ለማሰብ ከልጇ ዘንድ ምህረትን ለማግኘት ከድንግል ማርያም በረከትና ምልጃ ረድኤትንም ለማግኘት መፆም ይችላል።
እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፉ በሕልም ታይቶ "ሄሮድስ ህፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና ተነሳ ህፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብፅ ሽሸ፤ እስከነግርህም ድረስ በዚያ ኑር" እርሱም በሌሊት ተነስቶ ህፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብዝ ሄደ።
ከእግዚአብሔር ዘንድ ልጄን "ከግብፅ ጠራሁት" ተብሎ በነብይ የተነገረው ይፈፀም ዘንድ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ። ማቴ 2፤13_15
ድንግል ሆይ! ስደትሽን እያሰብሽ ከልጅሽ ዘንድ ምህረትና ይቅርታን አሰጭን! በበርሃው በደረሰብሽ ራሃብና የውሃ ጥሙን አሳሰቢልን፤ ልጄን ይገሉብኛል እያልሽ ስታለቅሽ ከአይኖችሽ የፈሰሰው መሪር እምባ አሳስቢልን! ድንግ ሆይ! በአካላዊ ስጋችን ከመልካም ምግባር ወደ ክፉ ምግባር የተሰደዱትን ስለ ስደትሽ ብለሽ እነሱን መልሻቸው !ድንግል ሆይ ከልጅሽ ጋር ተሰደሽ ስደትን የቀመሽ ስደተኛ ልጆችሽንም መልሻቸው ።ስለኢትዮጲያም አብዝተሽ አሳስቢ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
@aleroe
@alerobot