TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
አትሮኖስ

5 Apr 2022, 23:11

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

«ልጆችን ይተናኮላል?»
«በተለይ ልጆችን ይጎዳል፡፡»
«ይገድላል?»
«ብዙ ጊዜ አሉ» ወ/ሮ ማርጋሬት::
ፋንቲን ደብዳቤውን እንደገና ለማንበብ ወደ መስኮት ጠጋ አለች፡፡
ማታ በጊዜ ከቤትዋ ወጥታ ሐኪሙ ወደ ነገራት ሆቴል አመራች፡፡
በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ገና ጎሕ ሳይቀድ ወ/ሮ ማርጋሬት ወደ
ፋንቲን ክፍል ሄዱ፡፡ ብዙ ጊዜ አብረው ነበር የሚያመሹት፡፡ በዋዜማው ስላልተገናኙ፣ ሥራም አብረው ስለሆነ የሚሄዱት አሮጊትዋ ከፋንቲን ቤት መጡ፡፡ ፋንቲን ከደረቅ የእንጨት ወንበር ላይ ተቀምጣለች:: ፊትዋ
ገርጥቷል፤ ዓይንዋ እንባ አቅርራል፡፡ ሌሊቱን በሙሉ አልተኛችም:: ሻሽዋ
ጉልበትዋ ላይ ወድቋል፡፡
ወ/ሮ ማርጋሬት ደነገጡ፡፡ «ምነው? ምን ሆንሽ? ሌሊቱን ቁጭ ብለሽ
አደርሽ እንዴ?» ካሉ በኋላ ፋንቲንን አጤንዋት:: ፋንቲን ፊትዋን ቀና
አደረገችው፡፡ በአንድ ቀን ከእድሜዋ አሥር ዓመት የጨመረች መሰለች::
«ምንም አልሆንኩም» አለች ፋንቲን፡፡ «እንዲያውም ደስ ነው ያለኝ፣
ልጄ ላትሞት ነው፤ መንፈሴ ሁሉ የረካ ነው የመሰለኝ::»
ይህን እንደተናገረች ከጥርስዋ ሽያጭ እጅዋ የገባውን አርባ ፍራንክ ለአሮጊትዋ አሳየቻቸው::
«የሥላሴ ያለህ!» አሉ ወ/ሮ ማርጋሬት:: «ይኽ ሁሉ ገንዘብ ከየት ተገኘ? ከሰማይ ነው የወረደው ወይስ ከምድር ፈለቀ?»
«ከየትም ይሁን ብቻ፧ አግኝቻለሁ» አለች ፋንቲን የኩራት ስሜት
አድሮባት ፈገግ እያለች:: ሆኖም ፈገግታዋ ዓይንን የሚያሸሽ እንጂ የሚስብ አልነበረም:: ከንፈርዋ በደረቀ ደም ተበክሎአል:: ወላቃዋም በግልጽ ይታያል፡፡
ሁለቱ የላይኞቹ የፊት ጥርሶችዋ ተነቅለዋል:: ጥርሱ የውበት ቀዳዳ
በቅጡ አልተደፈነም::
አርባውን ፍራንክ፡ ለልጅዋ ኣሳዳጊዎች ላከች:: ሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ ገንዘብ ለማግኘት የፈጠሩት ዘዴ ነበር እንጂ ኮዜት አልታመመችም::

ፋንቲን ፊትዋን ታይበት የነበረውን መስታወት በመስኮት ወደ ውጭ
ወረወረች::

ባለ እዳዎችዋ በጣም እየጨከኑባት ሄዱ፡፡ ያገለገለ እቃ የሚሸጡ ሰውዬ ባገኝዋት ቁጥር «አንቺ እድለቢስ፣ ገንዘቤን አትሰጪኝም?» እያሉ
ሰደብዋት::

ምን አድርጊ ነው የሚልዋት? ፋንቲን እንኳን እዳ ልትከፍል ለሆድዋ ስላልሆነላት ከሰውነት ወጥታለች:: ልጅዋን የሚያሳድጉላት ባልና ሚስት
ሌላ ደብዳቤ ጻፉ::

«ኮዜት ከበሽታዋ ድና በማገገም ላይ ነች:: ነገር ግን እስከ ዛሬ
የተጠራቀመውን መቶ ፍራንክ አሁኑኑ ካልላክሽ ከቤት አስወጥተን መንገድ ነው የምንጥላት» የሚል ነበር፡፡
«መቶ ፍራንክ! አሁን ደግሞ የት ይሆን ይህን ያህል ገንዘብ የማገኘው? ይሁና!» አለች:: «የቀረውን ጥርሴን እሸጣለኋ!»
እድለቢስዋ ፋንቲን የሰው መዘባበቻ ሆነች::..

💫ይቀጥላል💫
🩸Share 🩸

5.9k 0 11 18
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Наш блог Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot