የኢትዮጵያ ጦር ‼️
የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ዘልቆ ገብቶ የሞርታር ጥቃት መፈጸሙን የሶማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
👉አልሸባብ ባሳለፍነው አርብ ማታ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሯል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ጦር ጥቃቱን የፈጸምኩት የጦር ካምፔ ላይ ጥቃት ተፈጽሞብኝ ነው ብሏል። ከሶማሊያና ግብጽ ለሚመጡ ድንበር ተሻጋሪ ጥቃቶች በተጠንቀቅ መቆሙ የተገለጸው የኢትዮጵያ ጦር አርብ ምሽቱን ከሶማሊያ ግዛት ወደ ጦር ካምፑ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በሶማሊያ ባኮ ክልል ዋጂድ ወረዳ ላይ የሞርታር ጥቃት መፈጸሙን የአካባቢው ነዋሪዎች መናገራቸውን ጠቅሶ የዜና ገጹ ዘግቧል።
እስካሁን ባለው መረጃ ለ ሰዓታት የዘለቀው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት የተደረገው በግልጽ የሶማሊያን ጦር መለዮ ያላበሱ ትጥቃቸው የአል ሻባብ ሃይል የሚመስሉ ጋር ነው ተብሏል። ግጭቱ በኢትዮጵያ ወታደሮች እና በአልሸባብ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ያለው ዘገባው ሁለቱም ወገኖች ከባድ የጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ይላል።
የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት ከተፈጸመባቸው በኋላ ወዲያው ከፍተኛ የሆነ የቦምብ ድብደባ፣ እና የሞርታር ዶፍ አዝንበዋል ሲሉ ጦርነቱ ሲደረግ በዓይናቸው የተመለከቱ እማኞች አሳውቀዋል። በተደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ምን ያክል ሰዎች ሞቱ የሚለውን የአካባቢው ባለስልጣናት ከማሳወቅ ተቆጥበዋል።
አልሸባብ ባወጣው አጭር መግለጫ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስዶ የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን እና የጦር መሳሪያዎችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መዘረፉን አስታውቋል። ቡድኑ ግን የተጎጂዎችን ቁጥር እና የተያዙትን መሳሪያዎች መጠን አልገለጸም።እንደ እማኞች ገለጻ ግን አል አሻባብ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።
አዩዘሀበሻ
👇👇
👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s