በትግራይ ዜጎች ዳግመኛ ግጭት ይቀሰቀሳል በሚል ስጋት ባለፉት ሶስት ቀናት ዉስጥ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሸመታ ላይ ናቸዉ ተባለ
በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ክንፍ የተሾሙ የተባሉ ግለሰብ በሚሊሻዎች ታጅበው ትናንት የመቐለ 104 ነጥብ 4 ኤፍኤም ሬድዮ ጣብያ ለመቆጣጠር መሞከራቸው ተከትሎ በሬድዮ ጣብያው ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ዳጉ ጆርናል መረጃ ማድረሱ አይዘነጋም።
ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደም በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሾሙትን የጣቢያው ሃላፊ አውርደው በሌላ ሰው የመተካት እንቅስቃሴ ማድረጋቸውንና የከተማዋ ፖሊስ ደርሶ ድርጊቱን ማስቆሙን ታውቋል።
የወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ ተከትሎ ደግሞ ግጭት እንዳይነሳ የሰጉ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገንዘባቸው ከባንክ ማውጣት እና ሸቀጦች መግዛት ላይ ተጠምደዋል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዶቼ ቬለ ዘገባ ተመልክቷል።
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቐለ ዲስትሪክት ሰራተኞች እንደሰማነው ከወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ በኃላ በነበሩ ሶስት ቀናት ብቻ ከግማሽ ቢልዮን በላይ ብር ከባንኩ ቅርንጫፎች በደንበኞች ወጪ ተደርጓል።
በገበያዎች በተለይም የምግብ ነክ ሸቀጦች የሚገዛ በዝቷል ፥ የተወሰነ የዋጋ ጭማሪም ይስተዋላል ተብሏል። በሌላ በኩል በበርካታ ነዳጅ ማደያዎች በተለይም ቤንዚን የሌለ ሲሆን በጥቁር ገበያ ከ270 እስከ 300 ብር አካባቢ ይሸጣል።
ይህንኑ ተከትሎ የትራንስፖርት ዋጋም ተወዷል ሲል የዜና ምንጩ ዘግቧል።
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s