ኩረጃ ምንድን ነው?
✅ከዚህ ቀደም ቢቢሲ በሰራው አንድ ዘገባም ተማሪዎች ለኩረጃ ይመቻቸው ዘንድ ከጎበዝ ተማሪዎች ጋር በማመሳሰል ስማቸውን በፍርድ ቤት አስለውጠዋል።
✅ኩረጃ በአንድ የፈተና ክፍል ውስጥ ብቻ የሚካሄድ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚዳብር መሆኑን ጨምረው ያስረዳሉ።
✅የራስ ያልሆነን ስራ እንደራስ አድርጎ ማቅረብ፣ ትክክለኛ ምክንያት ባለመስጠት መምህሩን ማሳሳት እና የማይገባውን ውጤት ለማግኘት የሚደረግ ጥረት፣ ያልተገባ ውጤት ለማግኘት መምህርን ማታለል በአጠቃላይ ኩረጃ ነው ይላሉ ወንድይፍራው (ዶ/ር)።
✅ጓደኛ እንዲኮርጅ መርዳት፣ በግል የተሰጠ ምዘናን ወይንም የቤት ሥራ በቡድን መስራት ሁሉ በኩረጃ ስር እንደሚጠቃለሉ ጨምረው ይገልጻሉ።
✅በትምህርት ቤት ሕይወታቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ በኩረጃ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በርካታ መሆናቸውን በተለያዩ አገራት የተሰሩ ጥናቶች ያሳያሉ።
✅ተማሪዎች የሚኮርጁት ለፈተናው ወይንም ደግሞ ምዘናው በቂ የስነልቦና ዝግጅት ሳይኖራቸው ሲቀር መሆኑን ይናገራሉ።
✅ተማሪዎች በተገቢው መጠን ራሳቸውን ካለመዘጋጀት ውጪ፣ ትምህርትን በአግባቡ አለመከታተል፣ ኩረጃ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሌለው ግንዛቤ መያዝ ወደ ኩረጃ የሚገፉ ሌሎች ምክንያቶች ናቸው ይላሉ።
✅ከዚህም በተጨማሪ ወንድይፍራው (ዶ/ር) እንደሚሉት የወላጆች 'ልጆቼ ተምረው፣ ሕይወቴን ይለውጡኛል' የሚለው ገለጻ ልጆች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል።ይህ ቤተሰብ የሚያደርገው ጫና ተማሪዎችን ለማበረታታት የተደረገ ነገር ቢሆንም ለኩረጃ እንደሚገፋም ያስረዳሉ።
✅በራሱ ጥረት ወላጆቹ ወዳሰቡለት ስኬት መድረስ ያልቻለ ተማሪም የወላጆቹን ጫና ለመሸሽ ጎበዝ የሚባሉ ተማሪዎችን በመደገፍ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ይሞክራል በማለት ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ኩረጃ ከክፍል ክፍል ሲኬድ እያደገ የሚሄድ ብቻ ሳይሆን፣ በሕይወት ውስጥ ዘላቂ የሆነ ተጽዕኖ እንዳለውም ጨምረው ገልፀዋል።
✅"ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በትምህርት ዓለም የነበረን የኩረጃ ሕይወት ወደ ሥራ ዓለም ስንገባም ያንኑ የመተግበር እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ እና ተያያዥነት እንዳለው ነው፤ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በኩረጃ ታግዞ ወደ ከፍተኛ ተቋም ሲገባ፣ እዚያም በኩረጃ ታግዞ ቢመረቅ በስራው ዓለም መደለያ ለመቀበል አያቅማማም።"
✅ተማሪዎች በጓደኞቻቸው ዘንድ ሰነፍ ሆኖ ላለመታየት፣ በውጤት አንሶ ላለመገኘት፣ ወደ ኩረጃ እንደሚገቡም አክለው ተናግረዋል።ተማሪዎቹ ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባታቸው በፊት፣ ለኩረጃ ሲዘጋጁ ኔትወርክ ፈጥረው፣ የመጀመሪያው እቅድ ባይሳካ በሚል ሁለት እና ሶስት እቅዶችን ነድፈው መሆኑንም ጠቅሰዋል።
✅ከዚህ በተጨማሪ የነደፉት ስልት በፈተና የመጀመሪያ ቀን ካልሰራ፣ ለቀጣዩ ፈተና ቀን ሌላ ስልት ነድፈው እንደሚመጡም ይናገራሉ።ከዚህ የሞባይል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በሚያደርጉት ኩረጃም ከትምህርት ቤት ውጪ ያሉ ግለሰቦችን እንደሚያካትቱ ጨምረው ያስረዳሉ።
✔️ለፈተና ራሳችንን እናዘጋጅ
✔️ኩረጃን/ስርቆት እንጠየፍ