Big Habesha Tech


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Технологии


This is my user name @bighabesha
በተመሳሳይ ሰምና profile እንደትጭበርበሩ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций


PC Game ወዳጆች መቼም ይህን Game ታውቁታላችሁ።
Call of duty
በጣም ተወዳጅና ብዙ ሪከርዶችን የሰባበረ Game series ነው።
ከ2003 እስከ 2023 ድረስ ከ20 በላይ የCOD ሲሪየሶች ተለቀዋል።

በActivision Blizzard ባለቤትነት ይተዳደር የነበረው ይህ game ከ2023 ጀምሮ Microsoft ጠቅልሎ ስለገዛው አሁን ባለቤትነቱ የMicrosoft ሆኗል።
በጣም ተወዳጅ  የCOD ሲሪየሲች መካከል
⚫Call of Duty 4: Modern Warfare
⚫Call of Duty: Black Ops
⚫Call of Duty: Ghosts
⚫Call of Duty: Infinite Warfare
⚫Call of Duty: Vanguard
እነዚህም በስራቸው ከ2 በላይ ሲሪየሶች አሏቸው ።

ከPC በተጨማሪ Call of duty Mobile ያለው ሲሆን በአሁኑ ሰአት እጅግ ተወዳጅ እየሆኑ ካሉት የሞባይል fps ጌሞች መካከል አንዱ ነው።

👉ሁሉንም የCOD ጌሞች ከዚህ ቻናል ላይ ማውረድ ትችላላችሁ።
@CallOfDutyGamesPC

እስኪ የተጫወታችሁትን የCOD franchise comment ላይ ፃፉልን።


ሰላም ቤተሰቦች 👋
በቃ እናንተ ሰው የት ጠፋ አትሉማ?

ለማንኛውም ተመልሻለሁ በአሪፍ አሪፍ መረጃዎች እክሳችኋለሁ።


IOS 18.3

Apple ከጥቂት ቀናት በፊት ለ i-phone ተጠቃሚዎቹ Ios 18.3ን ለቆ ነበር። ታዲያ ይህም update ካካተታቸው features መካከል፦

⚫የnotification summarization feature እጅግ ተሻሽሎ ቀርቧል።
⚫performance ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።
⚫ለiPhone 16 models visual intelegence ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።
⚫Calculator app ላይ የ "=" ምልክት እየደጋገምን ስንነካ መጨረሻ ላይ ያለው የሂሳብ ኦፕሬሽን ይደጋገማል። ለምሳሌ በፊት ላይ 2×2 ብለን "=" ስንነካ 4 ይሰጠናል በድጋሜም "=" ስንነካ ለውጥ አያመጣም 4ን ያሳየናል አሁን ግን የ"=" ምልክት ስንነካ ×2 አድርጎ 8 እያለ ይቀጥላል። random scientific calculator እና አንድሮይድ ስልኮች ላይ የተለመደ ነው።
⚫በተጨማሪም ሌሎች ጥቃቅን ችግሮች ተቀርፈውበታል።

ይህንን IOS 18.3 update የሚያገኙ ስልኮች ዝርዝር፦
iPhone SE (2nd generation )
iPhone SE (3rd generation )
iPhone XR
iPhone XS
iPhone XS Max
iPhone 11
iPhone 11 Pro
iPhone 11 Pro Max
iPhone 12 mini
iPhone 12
iPhone 12 Pro
iPhone 12 Pro Max
iPhone 13 mini
iPhone 13
iPhone 13 Pro
iPhone 13 Pro Max
iPhone 14
iPhone 14 Plus
iPhone 14 Pro
iPhone 14 Pro Max
iPhone 15
iPhone 15 Plus
iPhone 15 Pro
iPhone 15 Pro Max
iPhone 16
iPhone 16 Plus
iPhone 16 Pro

©bighabesha_softwares


እኛ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች crypto እንዴት እንደሚጠቀሙ እና እንደሚመለከቱ የምንመረምር የሳይንስ ተመራማሪዎች ቡድን ነን። አሁን በ30 ቋንቋዎች የሚገኘውን 2ኛውን የCrypto Survey እያካሄድን ነው። በተለይ የአፍሪካ/ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎችን አስተያየት እንፈልጋለን፣ ለዚህም የዳሰሳ ጥናቱን በ አማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ተርጉመናል።
https://survey.stateofcrypto.net/

ሁሉም ውጤቶች ይፋዊ እና ለሳይንሳዊ እውቀት አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።
ከኢትዮጲያ ብዙ ሰዎች እንደሚቀላቀሉ ተስፋ እናደርጋለን!
ማንኛቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት በ info@stateofcrypto.net ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በኩል ለመገናኘት አያመንቱ።


Software ወይም website በምናበለፅግበት ጊዜ ስራችንን ለማቀላጠፍ አንዳንድ frameworksን መጠቀም ግድ ይላል። ታዲያ አንዳንድ frameworks እና የምትማሩባቸውን ድረገፆች እንደሚከተለው አሰናድተንላችኋል።

React 👉 react.dev
Vue 👉 learnvue.com
Ruby on Rails 👉 railstutorial.org
Next.js 👉 nextjs.org
Angular 👉 angular.io
Django 👉 djangoproject.com
Flask 👉 flask.palletsprojects.com
Laravel 👉 laravel.com
Spring Boot 👉 spring.io
Flutter 👉 flutter.dev
Bootstrap 👉 getbootstrap.com
Tailwind CSS 👉 tailwindcss.com

በቀጣይ ስለ framework ሙሉ ማብራሪያ እናቀርባለን።
©bighabesha_softwares


#ጥንቃቄ

ሰሞኑን በቴሌግራም እና WhatsApp ላይ እየተሰራጨ ያለ መተግበሪያ አለ። ስሙም ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ሲሆን ቀላል ያልተባለ ጉዳት ያደርሳል።

ከሚያደርሳቸውም በርካታ ጉዳቶች መካከል፦ password ማየት፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን ማንበብ፣ ስክሪን ማየት ይጠቀሱበታል። ከዚህም በላይ አሳሳቢው #የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ እንዳጋራው መረጃ ይህ መተግበሪያ ካለኛ ፍቃድ ገንዘባችንን ሊመነትፍ እነሰደሚችል አስታውቋል።

ከPlay store, App store አልያም ከምታምኗቸው ምንጮች ብቻ መተግበሪያ/APP ማውረድ፤ ከሰዎች የሚላክላችሁን link ሳታጣሩ አለመክፈት፤ ለመተግበሪያዎች አላስፈላጊ permission አለመስጠት ማለትም የcamera መተግበሪያ ሆኖ ከካሜራ በተጨማሪ የስልክ permission የሚጠይቃችሁ ከሆነ መጠርጠር እና ሳታጣሩ ፍቃድ አለመስጠት የመሳሰሉት ቅድመ ጥንቃቄዎች ከዚህ መተግበሪያ ጉዳት ሊያድኑን ይችላሉ።

pharma+ በብራዚል ፣ፓኪስታንና South Africa ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

Source: Tikvah_ethiopia

©bighabesha_softwares


⚡️⚡️⚡️⚡️
DeepSeek የሳይበር ጥቃት ደረሰበት።

በጥቂት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘውና አለምን እያናወጠ የሚገኘው የቻይናው AI DeepSeek የሳይበር ጥቃት ደረሰበት።

ከፍተኛ የmalicious attack ስለገጠመውም ለጊዜው አዲስ አካውንት registration እንዳቋረጠ ተገልጿል።

ይህን ጥቃት ማን እንደፈፀመው በግልፅ ባይታወቅም የሌሎች ተፎካካሪ generative AI ድርጅቶች እጅ ሊኖሩበት እንደሚችል The Hacker News ዘግቧል።


@bighabesha_softwares


ቻይና ሰራሹ chat bot

በ2023 ማለትም የዛሬ አመት ገደማ Liang Wenfeng በተባለ ግለሰብ የተሰራ AI ነው። ይሁንን እንጂ ባለፈው ሳምንት በመተግበሪያ መልክ ቀርቧል።

ይህ AI እስካሁን ድረስ 3 ጊዜ version አሻሽሏል። እነርሱም DeepSeek LLM, V2 እና አሁን ላይ ያለው V3 ናቸው።

መተግበሪያውም ከUI/user interface ጀምሮ በበርካታ ነገሮች ከChat Gpt ጋር ተመሳሳይነት አለው።

ነፃ መሆኑ በsoftware አበልፃጊዎ እና በተለያዩ የchat bot ተጠቃሚዎች ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ አድርጎታል።

ወጪ ቆጣቢ ከመሆኑም በተጨማሪ open-source መሆኑ ከበርካታ Chat bots የበለጠ ተደራሽነት እንዲኖረው ያደርጋል።

አሁን ላይም Play store ላይ ከ1 million በላይ downloads እና 4.7 rating ማግኘት ችሏል።

ይህ ነገር በዚሁ ከቀጠለ China ወደፊት የAI ኢንዱስትሪውን የምትቆጣጠረው ይመስላል ሀሳባችሁን አጋሩን።

©bighabesha_softwares

19k 0 0 25 194

China ከchatGPT ጋር የሚፎካከር አዲስ ነጻ generative AI አስተዋወቀች።

DeepSeek ስትል የሰየመችው ይህ AI በPlaystore በAppstore እና በድረገፅ ተለቋል።

በተለቀቀ በቀናት ልዩነት ውስጥ የtechnology stock market በከፍተኛ ደረጃ እንዲዋዥቅ አድርጓል።

ሞክሩት
Play store link
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.deepseek.chat

Website
https://www.deepseek.com/

ℹ️Login ስታደርጉ በemail login አድርጉ።

ዝርዝር መረጃ ይጠብቁን።

@bighabesha_softwares


ስማርት ትራስ

careld ይሰኛል። ዘመናዊ እና በርካታ features ያለው ትራስ ነው። ስሙን ትራስ እንበለው እንጂ በርካታ ትራስ ላይ ያልተለመዱ ነገሮችን አካቷል ከነዚህም መካከል።

ላተነፋፈስ ስርዓት የሚሆነንን ከፍታ በመመጠን እንዳናንኮራፋ ያደርገናል።
የተሰራበት ጥሬቃ ለመተኛት በጣም ምቹ አድርጎታል።
እንደሚመቸን አድርገን በፈለግነው ከፍታ እና position መተኛት እንችላለን።
ስለ ልብ ምታችን እና አተነፋፈስ ስርዓታችን አንዳንድ መረጃዎች በስልካችን ይልክልናል።

በMarch 2025 በይፋ ለገበያ የሚወጣ ሲሆን በበርካቶች ዘንድም አድናቆትን ማግኘት ችሏል።

©bighabesha_softwares


OpenAI Operator የተሰኘ አዲስ AI አስተዋወቀ።

ይህ AI agent ሰዎችን በመተካት የተለያዩ የኢንተርኔት ስራዎችን ይሰራል ተብሏል። የራሱን browser በመጠቀም የተለያዩ ድረገፆችን ይጎበኛል type ያደርጋል። click ያደርጋል። scroll ያደርጋል።

ኢንተርኔት ላይ ያሉ ታስኮችን በመውሰድ ባጭር ጊዜ ይከውናል። ለምሳሌ አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ሆቴሎችን የዋጋ ዝርዝር አጥንቶ የተሻለው ላይ አልጋ book እንዲያደርግ ማዘዝ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ፎርሞችን መሙላት፣ ከግሮሰሪ order ማድረግ እንዲሁም meme create ማድረግ ይችላል።

Computer-Using-Agent(CUA) የተሰኘ ሞዴል የሚጠቀም ሲሆን ማንኛውንም graphical user interface በቀላሉ እንዲረዳ ተደርጎ ነው የተሰራው። አንድ ሰው የኮምፒውተሩ screen ላይ የሚያያቸውን buttons, menus, textና የተለያዩ ፎቶዎችን በቀላሉ ይረዳል ተብሏል።

የሰውን involvement የሚጠይቁ እንደ login, payment detailsና CAPTCHA ሲኖር ተጠቃሚው እንዲያስገባ እንደሚጠይቀው በድረገፃቸው ላይ አስፈረዋል።

በአሁኑ ጊዜ በሙከራ ላይ ቢሆንም አሜሪካ ውስጥ Pro ተጠቃሚዎች operator.chatgpt.com ላይ ገብተው መሞከር ይችላሉ ሲል OpenAI አስታውቋል። ወደፊትም ለPlus, Teamና Enterprise ተጠቃሚዎች እንደሚለቀቅ አስታውቋል።

OpenAI ወደፊት ምን ያስተዋውቅ ይሆን?


የ ጃፓኑ Sony ታሪካዊ የሆነዉን Blu-ray Disk ማምራት ማቋረጡን አስታወቀ።

ብዙዎቻችን የ90ዎቹ ትውልዶች የተለያዩ ፊልሞችንና ሙዚቃዎችን በCD, DVD እና Blu-ray እያስጫን አይተናል።

ከዋጋ ርካሽነትና ቀላልነት አንጻር ብዙ ሰዉ CDና DVD ቢመርጥም ከዘመናዊነትና ብዙ መረጃ በመያዝ ግን Blu-ray Disk ይሻላል።

ያም ሆኖ የሚሞሪ ካርድና ፍላሽ ካርዶች መምጣት ምክንያት እነዚህ እቃዎች በከፍተኛ ፍጥነት ከገበያው እየወጡ ይገኛሉ።

ለዚህም ነው ትልቁ የቴክኖሎጂ እቃዎች አምራች ድርጅት SONY ከየካቲት ወር ጀምሮ እነዚህን Blu-ray Disk ማምረት እንደሚያቆም ያስታወቀው።


✍️እስኪ በDVD ያያችሁት የማትረሱት ፊልም ምንድን ነው? Comment

@bighabesha_softwares


የአንዳንድ Programming Languagesን ዕውቀት የምንቀስምባቸው ድረገጾች፦

ለHTML 👉 w3schools.com

ለCSS 👉 css-tricks.com

ለJavaScript 👉 javascript.info

ለPython 👉 realpython.com

ለTypeScript 👉 codecademy.com

ለJava 👉 javatpoint.com

ለRuby 👉 rubyguides.com

ለC 👉 tutorialspoint.com

ለC++ 👉 learncpp.com

ለC# 👉 csharp.net

ለPHP 👉 php.net

ለSwift 👉 hackingwithswift.com

ለKotlin 👉 kotlinlang.org

ለRust 👉 rust-lang.org

ለDart 👉 dart.dev

ለR 👉 r-project.org

ለPerl 👉 perl.org

ለScala 👉 scala-lang.org

ለHaskell 👉 haskell.org

ለJulia 👉 julialang.org

ለElixir 👉 elixir-lang.org

©bighabesha_softwares


SAMSUNG በትናንትናው  ዕለት S25 series ስልኮችን launch አድርጓል።

ሙሉ የLaunching ፕሮግራሙን ለመከታተል ሞክሬ ነበር ከS24 የበለጠ ያን ያክል wow የሚያስብል feature አላየሁም።

ከS24 ultra የሚለየው ነገር
1. Processor: S25 አዲሱ Snapdragon 8 Elite ፕሮሰሰር የተገጠመለት ሲሆን S24 Ultra Snapdragon 8 Gen 3 ተገጥሞለታል።
2. Camera: አብዛኛው የcamera spec ተመሳሳይ ሲሆን ያላቸው ብቸኛ ልዩነት  S25 50MP ultrawide የተገጠመለት ሲሆን S24 Ultra 12MP ultrawide camera አለው።

3. Design: S24 Ultra ሹል አራት መዓዘን ቅርፅ ሲኖረው S25 ደግሞ በአራቱም አቅጣጫ rounded ጠርዝ አለው። በክብደት S24 ትንሽ ከበድ ይላል። S24 ultra 233g ሲመዝን  S25 Ultra ደግሞ 218g ይመዝናል።

ዋጋ
SAMSUNG በዚህ ስልኩ ላይ የዋጋ ጭማሪ አላደረገም። S24 ultra ሲወጣ ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ S25ም ይሸጣል።

Pricing Details:
1. Galaxy S25 Ultra:
• Starts at $1,299.99
• Storage options: 256GB, 512GB, and 1TB
• Online-Exclusive Colors: Titanium Pinkgold, Titanium Jetblack, Titanium Jadegreen
2. Galaxy S25+:
• Starts at $999.99
• Storage options: 256GB and 512GB
• Online-Exclusive Colors: Blueblack, Coralred, Pinkgold
3. Galaxy S25:
• Starts at $799.99
• Storage options: 128GB and 256GB
• Online-Exclusive Colors: Blueblack, Coralred, Pinkgold




ብዙ ነገሮችን በአንድ ላይ የያዘ ካርድ ስራ ላይ ሊውል ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዜጎች 3 እና 4 ካርድ እንዳይዙ የሚያደርግ ካርድ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው።

ይህም ካርድ መንጃ ፍቃድ፣ ኤቲኤም፣ ፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የሚይዝ ስማርት ካርድ ሲሆን በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ስራ እንዲገባ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።

ካርዱ ወደ ስራ ሲገባም ከባንኮች እና ከሌሎች ተቋማት ጋር ትስስር ፈጥሮም እንደሚሰራ ተገልጿል።

Source: #Tikvah_ethiopia

በዚህ ካርድ ዙሪያ ሀሳባችሁን አካፍሉን።
©bighabesha_softwares

24k 0 0 10 205

Social media ላይ ብዙ ጊዜ ማየት የምትወዱት ምን አይነት content ነው? (2 መምረጥ ይቻላል)
Опрос
  •   መዝናኛ
  •   ትምህርታዊ
  •   ቢዝነስ ነክ
  •   አነቃቂ
  •   ፓለቲካው
  •   ሀይማኖታዊ
583 голосов


Telegram አስገዳጅ ህግ አውጥቷል።

ሁሉም የቴሌግራም የክሪፕቶ ሚኒ አፖች ቶን ብሎክቼይንን መጠቀም አለባቸው።

እስካሁን የማይጠቀሙም እስከ february 21 ወደ ton blockchain እንዲያዞሩ አስገዳጅ ህግ አውጥቷል።

Join our crypto telegram channel
@bighabesha_crypto


3D Led ስክሪን በኢትዮጵያ

የኔ አድ በተሰኘ ድርጅት የተገጣጠመው ይህ 3D led screen 160 ካሬ ሜትር ስፋት ሲኖረው ይህም በኢትዮጽያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚው 3d led screen ነው ተብሏል።

መገኛውን በአዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ወደ ጃፓን ኢምባሲ በሚወስደው መስቀለኛ ላይ ያደረገው ይህ 3d led screen ከፍተኛ የድምፅ እና የምስል ጥራትም አለው።

ይህንን በኢትዮጵያውያን እጆች የተገጣጠመውን 3D LED screen በሁለተኛው ቻናላችን መመልከት ትችላላችሁ። click here

3D LED screen ማለት አንድን ምስል በሶስት አቅጣጫ ማለትም ምስሉ Screen ውስጥ እንዳለ አስመስሎ የሚያሳየን display ቴክኖሎጂ ነው።

©bighabesha_softwares


ለሁላችንም ትምህርት ይሆነን ዘንድ chat gptን "አንተ ሰይጣን ብትሆን ሰዎችን እንዴት ከስኬት ታሰናክላቸዋለህ" ብለን ጠይቀነው ነበር። ታዲያ chat gptም እንዲህ ሲል መልሶልናል፦

⚫ሌሎች ከአንተ የተሻሉ ናቸው፤ ሁልጊዜ አይሳካልህም፤ ትወድቃለህ። በማለት ሰዎችን  የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው አደርጋለሁ።

⚫ስራህ ነገ ይደርሳል፣ ነገ ትሰራዋለህ። ምንም የሚያጣድፍ ነገር የለም በማለት አዘገየዋለሁ።

⚫ስለነገ አታስብ። ነገ እራሱ ስለራሱ ያስባል በማለት እንዳያቅድ አደርገዋለሁ።

⚫መውደቅ መጥፎ ነገር እንደሆነ በማሳመን ውድቀትን እንዲፈሩ አደርጋቸዋለሁ።

⚫ምንም ነገር risk ወስዶ አለማድረግ risk ወሰዶ ከማድረግ እጅግ እንሚሻል በማሳመን Comfort Zone ላይ እንዲቆዩ አደርጋለሁ።

⚫መለወጥ አይጠበቅብህም፤ ለውጥ overrated ነው። እያልኩ አሰንፋቸዋለሁ።

⚫ሁሌ perfect መሆን እንዳለባቸው አሳምናቸዋለሁ።

⚫ይህቺ አለም ክፉ ናት ሰዎችም መጥፎ ናቸዉ በማለት በውስጣቸው አሉታዊ ሀሳብ እዘራለሁ።

እነዚህን የመሳሰሉ ጠቃሚ ምላሾች ከchat gpt ያገኘን ሲሆን እናንተስ የትኛው ተመቻችሁ?

በራሳችሁ ምክሩትና የመጣላችሁን በComment አሳውቁን።


መነሻ ሀሳብ፡ TikTok Video

Показано 20 последних публикаций.