▫️▫️💥ትክክለኛው መረጃ💥
💥የትላንቱ የቤተ-መንግስት ስብሰባ💥
ወሃቢዮቹ ትላንት በሶሻል ሚዲያ መንጋቸውን ለማጃጃልና በመንጋቸው አዕምሮ ላይ እንደለመዱት ለመሳለቅ ሲያራግቡት የነበረው ነገር በሙሉ ሐሰት ነው፡፡ ሰው ተሳስቶ እንኳ 1 ዕውነት አያወራም እንዴ?! ለናሙና አንድ ዕውነት እንኳ አላገኘሁበትም፡፡
ለምሳሌ፡👇
1️⃣. ተቀዳሚ ሙፍቲ እና ‹ኢብኑ ቱፋ› ፌደራል መጅሊስን በጋራ ይምሩ ተብሏል ብለው ወሃቢዮቹ ትላንት ሲያራግቡት የነበረው ፍፁም ሐሰት ነው፡፡
2️⃣. በቀጣዩ የዒድ አል-አድሓ ሶላት ላይ በአ.አ. እስታዲየም ሙፍቲ በንግግር ከፍተው ‹ኢብኑ ቱፋ› በዱዓ ይዘጉታል ብለው ወሃቢዮቹ ሚያናፍሱትም ውሸት ነው፡፡
3️⃣. አቶ ሱልጣን አማን የታሸገው የአዲስ አበባ መጅሊስ ቢሮ እንዲከፈትላቸው ጠይቀው በቅርቡ እንደሚከፈትላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል ብለው ወሃቢዮቹ ሚያናፍሱትም ፍፁም ቅጥፈት ነው፡፡
4️⃣. ሙፍቲን በየቀኑ አውርጃለሁ ብሎ ሲሰበሰብ የነበረው 25 “ዑለሞችን” የያዘው “ጠቅላላ ጉባኤ” እንዲመለስ ተወስኗል ብለው ወሃቢዮቹ ሚያራግቡትም ከዕውነት የራቀ ሐሰት ነው፡፡
5️⃣. ከዛሬ 3 ዓመት በፊት የ479 ሑጃጅ 40 ሚሊየን ብር የሚጠጋን ገንዘብ ቁርጥም-አድርጎ የበላው የወሃቢያ አካል የሆነው ቦርድ ወደ ስራው እንዲመለስ ተወስኗል ብለው ወሃቢዮቹ የሚፈበርኩት ፊልምም ምናልባት በሕንዱ Bollywood ካልሆነ በስተቀር በአሜሪካው Hollywood ሊሰራ የማይችል ቅዠት ነው፡፡
6️⃣. ጠ/ሚ. ዐብይ የአንዋር መስጂዱን ኢማም ሰዪድ ሸኽ ጧሃን እንዲህ አሉ፤ እከሌን እንዲህ አሉ .. ወዘተ … እያሉ ወሃቢዮቹ መንጋቸውን የሚያስጨፍሩበትም ምኞት ቢሆን ያስጨበጨበ ተረት-ተረት ነው፡፡
💥ትክክለኛውስ መረጃ የቱ ነው?💥
ከላይ እንደገለፅኩላችሁ ወሃቢዮች የትላንቱን የቤተ-መንግስት ስብሰባን በተመለከተ የሚያራግቡት በሙሉ ሐሰት ነው፡፡ እንዲያውም እራሳቸው ከፍተኛ ውርደትን እና ቅሌትን የተከናነቡበት ስብሰባ ነበር፡፡ ለዚህም ነው መንጋቸው እንዳያፈነግጥባቸው እንደለመዱት ሐሰት ከመፈብረክ ውጪ ሌላ አማራጭ ያላገኙት፡፡
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ወሃቢዮች ከመጅሊስ ተገንጥለው መውጣታቸውን እና ሌሎችንም እስከዛሬ ሲፈፅሙት የነበረውን ወንጀል በሙሉ ህገ-ወጥ እንደሆነ በግልፅ ቋንቋ ነው የነገሯቸው፡፡
ጠ/ሚ ዐብይ እንዲህ ነበር ያሏቸው፡👇
👉 ‹‹ይህን ሁሉ ሕገ-ወጥ ተግባር ስትፈፅሙ እኛ አውቀን ነው አይተን እንዳላየ ዝም ያልናችሁ፡፡ ሴራው ሳይገባን ቀርቶ አይደለም፡፡ ደሞ በየጓዳው ተደብቃችሁ መንግስት ህግ አያስከብርም ብላችሁ ታሙናላችሁ፡፡ እኛ እርምጃ መውሰድ እና ህግ ማስከበር ጠፍቶን ወይም አቅቶን አይደለም ዝም ያልነው፡፡ እናንተ የሃይማኖት አባቶች ናችሁ ብለን ነው እስኪ ትንሽ እንያቸው በሚል ዝም ያልናችሁ፡፡ ከአሁን በኋላ እኛ በምንላችሁ መስመር ካልሄዳችሁ ግን ህግ እንዴት እንደምናስከብር እናሳያችኋለን››
በዚህ መልኩ በአብዛኛው የወሃቢዮቹን ትዕቢት የሚያጋልጥ፣ ወሃቢዮቹን አፍ የሚያስይዝ እና አንገት የሚያስደፋ ንግግር በውይይቱ ላይ ከተናገሩ በኋላ እና ተሳታፊዎችን ጨምሮ ሐሳቦችን ካንሸራሸሩ በኋላ የሚከተሉት ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡ 👇
1️⃣. በሙፍቲ የሚመራው ህጋዊው መጅሊስ (በሙፍቲ መሪነት ብቻ) አሁን ባለበት ይቀጥል፡፡
2️⃣. አቶ ሱልጣን በበኩላቸው .. ‹‹እንደምታዩት አሁን በዓል ደርሷል ነገር ግን የአ.አ. መጅሊስ በመታሸጉ የተነሳ ለመጅሊሱ ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አልቻልንም›› .. የሚል ቅሬታ ሲያቀርቡ፤ ቢሮው ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ብቻ ለሰራተኞች ደሞዝ ለመክፈል እንዲከፈት እና ከ10 ቀን በኋላ ዳግም እንዲታሸግ ተወስኗል፡፡ ደግሞ 10 ቀኑንም ቢሆን ልክ በፊት እንደነበረው አቶ ሱልጣን ዋና ፕሬዝደንት እና ሸኽ ዓሊ ሙሐመድም ም/ፕሬዝደንት ሆነው የወሃቢያውም የሱፊያውም አባላት ሁሉም የቀድሞ ቦታቸውን ይዘው እኩል ቢሮ ገብተው በጋራ ደሞዝ ከፍለው ከ10 ቀን በኋላ እንዲታሸግ ነው የተወሰነው፡፡
3️⃣. ከ4 ዓመት በፊት የአሁኑን መጅሊስ ያዋቀሩት ከ300 እስከ 400 የሚጠጉ ዑለሞች ከዐረፋ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ በሙፍቲ የበላይነት ከየገጠሩ ተጠርተው መጥተው (የወሃቢያው ቡድን አልወያይበትም ብሎ ወርውሮት የወጣውን) የመጅሊሱን ረቂቅ ህገ-ደንብ ዑለሞቹ እና መሻኢኾቹ በጥልቀት እንዲወያዩበትና እንዲመረምሩት ተወስኗል፡፡
4️⃣. ከዚያም እነዚህ ዑለሞች በተወያዩት መሰረትና መርምረውት የተስማሙበትን ውጤት መሰረት አድርገው የፌደራል መጅሊስን ፕሬዝደንት እና ዋና ፀሐፊውን እንዲሰይሙ ተወስኗል፡፡
5️⃣. በዚህ በትላንቱ በቤተ-መንግስት ስብሰባ ላይ የተገኙትን የመንግስት ባለሥልጣናትን እና የፖሊስ እና የፀጥታ ኃላፊዎችን.. ‹‹እከሌ ከእንገዲህ ይህን ታስፈፅማለህ›› .. እያሉ ዶ/ር ዐብይ አፅንኦት ለመስጠት የያንዳንዳቸውን ባለሥልጣናት ስም በየተራ እየጠሩ ይህን ውሳኔ እንዲያስፈፅሙ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
6️⃣. የፊታችንን የዒደል-አድሓ የዒድ ሶላትን በተመለከተ ክቡር ተቀዳሚ ሙፍቲ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ሙፍቲ ግን .. ‹‹በጭራሽ አላደርግም›› .. ብለው እንቢ አሉ፡፡ ጠ/ሚ ዐብይ ለሙፍቲ .. ‹‹እሺ ዱዓ እንኳ አድርጉ›› .. ሲሏቸው ሙፍቲ ደግሞ .. ‹‹በጭራሽ ዱዓም ሆነ ንግግር አላደርግም›› .. አሉ፡፡ በዚህ የተነሳ በዒድ ዕለት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝደንት አቶ አደም ፋራሕን ጨምሮ ሁለት ከመንግስት የተወከሉ ሰዎች ብቻ በወቅታዊ የሀገሪቷ ጉዳይ ዙሪያ ንግግር እንዲያደርጉ እና ሌላ ማንም ሰው ንግግር እንዳያደርግ ተወስኗል፡፡
7️⃣. በመጨረሻም ጠ/ሚ ዐብይ እንዲህ አሉ፡👇
👉 ‹‹በእነዚህ በተወሰኑት ውሳኔዎች መሰረት የማትስማሙ ከሆነና መፍትሔ ላይ የማትደርሱ ከሆነ ግን የመጅሊሱን ቁልፍ ከ4 ዓመት በፊት የነበረው የቀድሞው መጅሊስ ፕሬዝደንት ለነበሩት ለሸኽ ሙሐመድ አሚን ጀማል ቁልፉን አስረክባቸው እና የቀድሞው መጅሊስ ይመለሳል›› .. በማለት ኮስተር ብለው ይህን ተናግረው ብድግ ብለው ተነስተው ሄዱ፡፡
ስብሰባውም በዚህ ተቋጨ፡፡ ዕውነታው እንግዲህ ይህ ነው።