ብቁና ንቁ የነበሩ የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል፡፡
➢ በ1997 ዓ.ም የቤት ባለቤት ለመሆን ተመዝግበው የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች በ2005 ዓ.ም በተካሄደው ዳግም ምዝገባ ወቅት ነባር የሚል መለያ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን ዳግም ከተመዘገቡና ውላቸውን ካደሱ ጊዜ ጀምሮ ሳያቋርጡ ሲቆጥቡ የነበሩ ናቸው፡፡
➢ እነዚህ ተመዝጋቢዎች ቀደም ብለው የተመዘገቡ እንደመሆናቸው መጠን በ20/80 የቤት ልማት መርሃ ግብር ተገንብተው ለእጣ ከሚተላለፉት ቤቶች ውስጥ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በወጣው መመርያ ቁጥር 3/2011 መሰረት በነበሩት ዙሮች ቅድሚያ እየተሰጣቸው ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል፡፡
➢ በዚሁ አግባብ በ2005 ዳግም ምዝገባ ያደረጉ ከ140 ሺህ በላይ ተመዝጋቢዎች ሳያቆራርጡ እስከ እጣ ማውጫ ቀን ድረስ እየቆጠቡ ለነበሩት እስከ 13ኛ ዙር በነበረው የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ ሲሰተናገዱ ቆይተዋል፡፡
➢ ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለ14ኛ ዙር በተላለፉት የ20/80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ላይም የ1997 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ተስተናግደዋል፡፡
➢ በዚህም በ14ኛ ዙር እጣ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ንቁና ብቁ የነበሩ ከ43ሺህ ያልበለጡ ቆጣቢዎች ቅድሚያ በመስጠት ሙሉ በሙሉ እንዲሰተናገዱ ተደርጓል፡፡
➢ በእጣ ማውጫ ጊዜ በመረጃ ቋት ውስጥ የቀሩት የ1997 ተመዝጋቢዎች በጊዜው ንቁና ብቁ ያልነበሩ ናቸው፡፡
➢ እነዚህና ሌሎች ቤት ፈላጊዎች በከተማ አስተዳደሩ እየተተገበሩ በሚገኙ የተለያዩ የቤት የልማት አማራጮች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
➢ ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በከተማዋ እየተካሄዱ በሚገኙ የልማት ስራዎች ምክንያት ከመኖርያ አካባቢያቸው ለሚነሱ የልማት ተነሽዎች በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የወጣው በጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ መመርያ ቁጥር 3/2011 አንቀጽ 23 በተገለጸው መሰረት በከተማ መልሶ ማልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት ለመመደብ በተቀመጠው አሰራር መሰረት እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡
➢ እነዚህ በልማት ምክንያት የሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት የሚሰጣቸው ከላይ በተጠቀሰው መመርያ ላይ በሰፈረው መሰረት በከተማ አስተዳደሩ ከሚገነቡ የጋራ መኖርያ ቤቶች ውስጥ ለልማት ተነሺ በሚል በመጠባበቂያ ከተያዙት ቤቶች እንጂ በመደበኛነት ለተመዝጋቢዎች ከሚተላለፉ ቤቶች አይደለም፡፡
➢ የልማት ተነሺ ሆነው የጋራ መኖርያ ቤት ምትክ የወሰዱና በ20/80 ወይም በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ተመዝጋቢ የሆኑ ነዋሪዎች ከምዝገባ ቋት ውስጥ የሚቀነሱ ይሆናል፡፡
Condoaddis.com