Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ይቅርብህ!
~
ስለ ትግራይ ፖለቲካ ቢነሳ ትግሬ ወንድሜ ሊከፋህ ይችላል። ስለ አማራ ፖለቲካ ቢወራ አማራው ወንድሜ ሊከፋህ ይችላል። ስለ ኦሮሞ ፖለቲካ ቢወራ ኦሮሞው ወንድሜ ሊከፋህ ይችላል።
ወንድሜ ሆይ! የፖለቲከኛ ድስኩር ተከትለህ ጥላቻ አትዝራ። በኣኺራ ታምን የለ? ለነሱ በስባሳ ፖለቲካ ብለህ ኣኺራህን አታጨልም። ዘረኝነት ውስጥ አትግባ።
ወንድሜ የነሱ ፖለቲካ ለድሃው ህዝብ ጠብ የሚያደርገው ላይኖር ህይወትን ያክል ውድ ነገር አትገብር። የኢኮኖሚውን ኪሳራ፣ ማህበራዊ ውጥንቅጡን፣ የህሊና ጠባሳውን ትተነው ይሄው ሚሊዮን የሚገመት ወጣት ረገፈ። እስኪ ከዚህ ሁሉ መአት በኋላ ዛሬ ላይ እንደ ህዝብ ያተረፍነውን ንገረኝ። እንዲሁ ካንድ መከራ ወደ ሌላ መከራ መገላበጥ ብቻ። የፈተና አዙሪት።
አሁንም በዱር በገደሉ ያለህ፣ "በለው ውገረው" የምትል ሁሉ እቅጩውን እወቀው! በሞትህ አትፀድቅም። ባንተ ሞት እናትህ ቤት ሃዘን እንጂ ደስታ አይገባም። ሌላው ቀርቶ የትግል አጋሮችህ ሳይቀሩ የፖለቲካው አሰላለፍ ሲቀየር "ቅዱስ" ሞትህን "አላማ ቢስ እልቂት" ብለው ያራክሱታል። እናትህ ያለ ልጅ፣ ልጆችህ ያለ አባት ቀርተው ሜዳ ላይ ሲወድቁ አታጋዮችህ በትልልቅ ሆቴሎች ውስኪ ይራጫሉ። እና ለማን ነው የምትሞተው?! እኮ ለምን?
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor