EB Crypto


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Блоги


Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Блоги
Статистика
Фильтр публикаций


Binance account ያላችሁ ልጆች ይሄ ኤርድሮፕ እንዳያመልጣችሁ👇

ሲዝን 1 ተጠናቆ 2 ጀምሯል

ሲዝን 1ን ከባይናንስ ያገናኛ 50ሺ ብቻ ናቸው ዋጋው አሪፍ ይሆናል

አሁኑኑ ጀምሩት👇👇👇 አሰራሩ ያልገባው 👉 @eth_4x

https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_637449690&startapp=ref_637449690&utm_medium=web_share_copy


በ3 ወር 30,000$ ዶላር
Forex Trade መጀመር የምትፈልጉ ብቻ👇

በኢትዮጵያ በForex Trade 1ኛ ደረጃና በቀን ከ300ሺ ዶላር በላይ ከሚሰራው AB marshal ጋር November 4 የሚጀምር፤ ለ3 ወር የሚቆይ 100$ ዶላርን ወደ 30,000$ ዶላር የማሳደግ ቻሌንጅ ይጀምራል።እስካሁንም በየአመቱ 4 ጊዜ ከ100$ ወደ 10,000$ ቻሌንጅ አዘጋጅተው ተሳክቶላቸዋል።የዚህ ዓመት ለ100 ሰዎች ብቻ ለ3 ወር የሚቆይና ተጨማሪ በነፃ ለ3 ወር VIP Channel በ179$ ከፍለው live በቪዲዮ ትሬድ ያስተምራል። ለ1 ሰው 179$ ስለሚከብድ 30 ሰው ሆነን 6$ አዋተን 179$ ከሞላ በኋላ በአንድ ሰው ተመዝግበን የLive Trade ት/ቱን እኛ በዲስኮርድ አማካኝነት 6$ ለከፈሉ ልጆች ብቻ የምናስተላልፍ ይሆናል። ወደ Trade ዓለም መግባት የሚፈልግ ይሄ እድል እንዳያመልጣችሁ። VIP ላይ የሚለቀቁ Signalochinm ሁሉንም እንለቅላቹሃለን። Forex Trade መጀመርና ከላይ የፃፍነውን አይታችሁ መጀመር የምትፈልጉ ብቻ ከስር ባለው ሊንክ አናግሩኝ👇

@eth_4x


Zora Airdrop እየሰራችሁ ያላችሁ ልጆች የመጨረሻ ጊዜው ደርሷል




2 ቀን የቀረው

Fairfun Airdrop ሊጠናቀቅ 2ቀናት ብቻ ቀርተዋል አሁኑኑ participate አድርጉ ።

Join here :
https://fairfun.meme/airdrop?invite=PBRh6t
X ( twitter ) account connect አድርጉ ( ከሌላችሁ መጀመሪያ X  account ክፈቱ ) .

Referral code ይጠይቃል
👉 PBRh6t

Sol Adress አስገቡ any exchanges sol Adress .

Done!


NodePay
Grass ከዚህ በፊት አምልጦዋችኋል ?  Don't worry

ከ Grass ጋር ተመሳሳይነት  ያለው  AI ላይ የሚሰራ  Internet በመጠቀማቹ ብቻ Point እየሰበሰባቹ በሰበሰባቹት መጠን ደግሞ point የምታገኙበት ነው  Grass ላይ ከዚህ  ቀደም የሰሩ  የተሻለ ገቢ ማግኘት ችለው ነበር

Register ለማድረግ Email ብቻ ነው የሚያስፈልጋቹ Register አድርጋቹ ከጨረሳቹ በኋላ እንደአዲስ  ተመለሱና LOGIN አድርጉ

በስልክ የምትሰሩ Mises Browser ተጠቀሙ Desktop ከሆነ ማንኛውም  Browser መሆን  ይችላል

NodePay Extension አውርዱና አገናኙት Connected ካላቹ ጨርሳቿል።

Eligable ለመሆን  በተቻለ መጠን  100 ሰአት ኮኔክት መሆን አለበት 

በተጨማሪም  ኔትወርካቹ ፈጣን ከሆነ  የምትሰበስቡትም POINT ከፍ ያለ ይሆናል

Mumtiple account  እና VPN ባትጠቀሙ መልካም ነው ከሆነም ደግሞ multiple account  በተለያየ Device ስሩት  season 0 ላይ በጣም ብዙ ተጠቃሚዎች ታግደዋል

በዚ ሊንክ ተመዝገቡ👉 https://app.nodepay.ai/register?ref=cWAFqM4wEnAxqsC

ያስቸገራችሁ ነገር ካለ ማንኛዉም አይነት ጥያቄ ጠይቁን'
@eth_4x


ይሄ በብዙ (multi) የዌብሳይት አካውንት ሰርቼ ያገኘውት ገንዘብ ነው መስራት የምትፈልጉ ብቻ ወደዚህ ቻናል ግቡ።

ያልገባችሁ ነገር ካለ 👉 @eth_4x አናግሩኝ


Grass is listed on Bitget pre-market
Price = $1

👇
https://share.bitget.com/u/73JFAGDH


Scroll ነገ በKucoin List ይደረጋል ።

Scroll is the first token listed on binance pre-market.

Pre market price 1.2$+ live
.............................

Scroll ሳታሰሩን እንዳትሉ ከአመት በፊት የተጀመረ project ነበር season 1 ተጠናቋል ፤ ግን Season two አለው ፤ ይህንን Result አይተን ጥሩ ከሆነ የምንሰራ ይሆናል ።

Season 1 - 7%
Season 2 - 8% ነው ከsupply ለAirdrop የሚሰጡት ።

Season 2 አልተጀመረም ሲጀመር እናሳውቃለን ።


እንኳን በደህና መጡ

በዚህ ቻናል የተለያዩ የዌብሳይት ኤርድሮፖችኝ በመስራት ጥሩ ገንዘብ እናገኛለን፤ ምክንያቱም ሰርቼ አጊንቼወለውና። ከእኛ ጋር ለመስራት የምትፈልጉ ምንም ወጪ ሳናወጣ፣ ኢሜል፣ ቲዊተር የመሳሰሉትን ብቻ በመክፈት እንሰራለን፣

ያልገባቹ ነገር ካለ በዚህ👉 @eth_4x አናግሩኝ




Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
የአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች ለ29 ወራት ደሞዝ ስላልተከፈላቸው በረሃብ እየሞቱ ነው ተባለ

በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ የሚገኘው አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች፤ ለ29 ወራት ደሞዝን ጨምሮ ምንም ዓይነት ክፍያ ስላልተከፈልቻቸው በረሃብ እየሞቱ ነው ተብሏል።

የፋብሪካው ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፤ የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ሥራ ጀምሮ በነበረበት ወቅት ብቻ ለአራት ወራት ደሞዝ ተከፍሏቸው የነበረ ሲሆን፣ ከመጋቢት 2013 ጀምሮ እስካሁን ወርሃዊ ደሞዝና ጥቅማጥቅም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦባቸዋል።

በዚህም ከ30 ያላነሱ የፋብሪካው ሠራተኞች በረሃብና በበሽታ መሞታቸውን ጠቅሰው፤ በዚህ ወቅት ሴቶች በልመና፣ ወንዶች ደግሞ አቅም ያላቸው ወደ መሀል አገር ሲሰደዱ ሌሎች ወደ ገጠር ሄደው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በችግር እየኖሩ ነው ብለዋል። 

“ፋብሪካው የክልሉ መንግሥት የልማት ድርጅት በመሆኑ እንደ ሌሎች ሠራተኞች ለእኛም ደሞዝ ይከፈለን ስንል በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ሰሚ አጥተናል።” ነው ያሉት።

“መቀሌ ድረስ ተጉዘን ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ችግራችንን ብንገልጽም፤ “በፋብሪካው ላይ ጉዳት ያደረሰው አካል ካሳ ሲከፍል ነው የእናተም ጥያቄ መልስ የሚያገኘው” የሚል ምላሽ ሰጥቶናል።” ሲሉ ተደምጠዋል።

“ለፌደራል መንግሥት ጥያቄያችንን እናቅርብ አሳልፉን ስንልም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፈቃደኛ አይደለም።” ብለዋል።

በተለይ በክልሉ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቋረጡ ችግሩን ይበልጥ አስከፊ አድርጎታል ያሉት ሠራተኞቹ፤ ከዚያ በፊትም የቀበሌ መታወቂያ ለሌለው ሰው እርዳታ የማያገኝ በመሆኑ፣ እርዳታ ከተሰጣቸው ሰዎች እየለመኑ ይኖሩ እንደነበር ተናግረዋል።

ሠራተኞቹ አክለውም" በ“ኢፈርት” ውስጥ ካሉ የክልሉ መንግሥት 22 የልማት ድርጅቶች ውስጥ የ17ቱ ሠራተኞች ደሞዝ እየተከፈላቸው ነው ካሉ በኋላ፤ ለእኛ የማይከፈልበት ምክንያት ሊኖር አይችልም ሲሉ ተደምጠዋል።

አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከ5 ሺሕ 200 ያላነሱ ቋሚ እና 400 ገደማ ጊዜያዊ ሠራተኞች እንደነበሩት የተገለጸ ሲሆን፤ ብዙዎች የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከፌደራል መንግሥቱ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በጦርነቱ ወቅት ዝርፊያ፣ ውድመት እና የአየር ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለው ፋብሪካው፤ እስካሁን ምንም ዓይነት ጥገና እንዳልተደረገለት እና መቼ ወደ ሥራ እንደሚመለስም እንደማይታወቅ ተመላክቷል።

አዲስ ማለዳ ሠራተኞ ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
ማክሰኞ ጠዋት! ሰኔ 20/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ በራያ አላማጣ አካባቢ ከ1 ሺህ 600 በላይ የመንግሥት ጡረተኞች ለከባድ ችግር መጋለጣቸውን መግለጣቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። የመንግሥት ጡረታ ተከፋዮቹ፣ የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የጡረታ ክፍያቸውን እንዳላገኙና በዚሁ ሳቢያ በተከሰተ የምግብ እጥረት የቤተሰቦቻቸው አባላት ለሕልፈት እንደተዳረጉባቸው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በበኩሉ፣ ያልተከፈሉ የጡረታ ክፍያዎችን ለመፈጸም መረጃዎችን እያጣራና እያመሳከረ መኾኑን እንደገለጠ የጠቀሰው ዘገባው፣ የጡረተኞቹ ተወካዮች የጡረተኞች ማኅደር ከማይጨው ወደ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን እንዲዛወርላቸው ጠይቀዋል ብሏል።

2፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች በክልሉ ሰዎች በርሃብ እየሞቱ ስለመኾኑ መናገራቸውን ዶይቸቨለ ዘግቧል። የሃይማኖት መሪዎቹ፣ ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች በክልሉ ያቋረጡትን የምግብ ዕርዳታ ባስቸኳይ እንዲቀጥሉ መማጸናቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በክልሉ ለተረጅዎች የታሰበውን ዕርዳታ የዘረፉ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡም የክልሉ የሃይማኖት አባቶች ጠይቀዋል ተብሏል።

3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጀት ቋሚ ኮሚቴ ትናንት ባዘጋጀው ሕዝባዊ ውይይት ላይ መንግሥት በቀጣዩ ዓመት በጀት ለመንገድ ፕሮጀክቶች የመደበው በጀት አንስተኛ ስለመኾኑ አስተያየት ሰጪዎች እንዳነሱ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። መንግሥት 300 ያህል ለሚገመቱ ለፌደራል መንገድ ፕሮጀክቶች የመደበው በጀት 68 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ሲኾን፣ ለ100 ያህል የመንገድ ፕሮጀክቶች ከ100 ሚሊዮን ብር ያነሰ በጀት እንደተመደበላቸው ከዝርዝር የበጀት ሰነዱ መመልከቱን ዘገባው ጠቅሷል። ገንዘብ ሚንስቴር አስተያየት ሰጪዎች ላነሷቸው ስጋቶች በሰጠው ምላሽ፣ ጉዳዩ "በበጀት አስተዳደር" ማለትም ለካፒታል ፕሮጀክቶች የተያዙ በጀቶችን በማሸጋሸግ እንደሚታይ ገልጧል ተብሏል።

4፤ ለኢትዮጵያ አዋሳኝ በኾነችው የሱዳኗ ብሉ ናይል ግዛት በሱዳን ጦር ሠራዊትና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው "የሱዳን ሕዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ - ሰሜን" በተሰኘው አማጺ ቡድን መካከል ግጭት ማገርሸቱን መስማቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ተመድ፣ ከግጭቱ የሸሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ የግዛቲቷ ነዋሪ ሱዳናዊያን ወደ ኢትዮጵያው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መግባታቸውን ገልጧል። በሌላ ዜና፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት ባላንጣው ፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ካርቱም የሚገኘውን ግዙፉን የማዕከላዊ ተጠባባቂ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዕሁድ'ለት መቆጣጠሩን አምኗል። ጦር ሠራዊቱ በከተማ የመንገድ ላይ ውጊያ ይሳተፍልኛል ብሎ የጠበቀው እስካፍንጫው የታጠቀውን ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይል ነበር።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም የመምህርነት እና የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "‼️
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

✔- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

✔- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

✔- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

✔- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

✔- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

✔- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

✔- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

✔- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

✔- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

✔- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

✔- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

✔- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

✔- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡ሼር አድርጉ
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
ሰኞ ምሽት! ሰኔ 19/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ለአራት ዓመት ከመንፈቅ በሰብሳቢነት የመሩት ብርቱካን ሚደቅሳ "በጤና ችግር" ከነሃሴ 1 ጀምሮ በፍቃዳቸው ከሥራ እንደሚለቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ማሳወቃቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። ብርቱካን ከሃላፊነት እንደምለቅ ሰኔ 5 ላይ ያሳወቅኹት፣ "ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ ዕርፍት የሚያስፈልገኝ" በመኾኑ ነው ብለዋል። ብርቱካን በኃላፊነት ላይ በሚቆዩባቸው ቀሪ ጊዜያት፣ ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን እንደሚያጠናቅቁና አስተዳደራዊ ሽግግር እንደሚፈጽሙ ገልጸዋል። ብርቱካን ሃላፊነታቸውን "በፍትሃዊነትና ቅንነት" ሲያከናውኑ መቆየታቸውን በመልዕክታቸው ላይ ጠቅሰዋል።

2፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሃንስ አያሌው የባንኩ ያልተመለሰ ወይም መመለሱ አጠራጣሪ የኾነ የብድር ምጣኔ ወደ 9 በመቶ መውረዱን ለዋዜማ ተናግረዋል። ባንኩ "ባልተመለሰ ብድር ምጣኔ ከፍተኛ መሻሻል" ማስመዝገቡን የጠቀሱት ዮሃንስ፣ ይህ ምጣኔ ትግራይ ውስጥ ያለውን የብድር ኹኔታ እንደማያካትት ገልጸዋል። ዮሃንስ የባንኩ ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ በሂደት የተሻሻለው፣ የብድር መክፈያ ጊዜን በማራዘም ሳይኾን ብድርን በመክፈል ብቻ ነው” ብለዋል። ባንኩ ለባለሃብቶች ካበደረው 73 ቢሊየን ብር ውስጥ 19 ቢሊዮኑ ብር ስለመመለሱ አጠራጣሪ የኾነ ብድር ሲኾን፣ ከዚህ ውስጥ 11 ቢሊየኑ ወለድን ሳይጨምር ትግራይ ውስጥ ለተሠሩ ፕሮጀክቶች የተሰጠ ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት የባንኩ ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ 43 በመቶ ደርሶ ነበር። ብሄራዊ ባንክ ለልማት ባንክ ያስቀመጠው ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ ጣሪያ 15 በመቶ ነው።

3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኬሚቴ ዛሬ መንግሥት ባቀረበው የቀጣዩ ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል። ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ በጀቱን ገምግሞ ለምክር ቤቱ የማሻሻያ ሃሳቦችን የማቅርብ ሥልጣን ያለው ሲኾን፣ ምክር ቤቱም በቋሚ ኮሚቴው ምክረ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ በጀቱን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። መንግሥት ለቀጣዩ ዓመት ያቀረበው የ801 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት፣ የ281 ቢሊዮን ብር ጉድለት አለበት።

4፤ ባለፈው ሐሙስና ዓርብ አዲስ አበባ ላይ የመከረው የናይል ተፋሰስ አገሮች ከፍተኛ ስብሰባ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን በቶሎ ቶወደ ተግባር በማስገባት የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭን ቋሚ በኾነና የጋራ የተፋሰስ ልማቶችን በሚያሳልጥ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን እንዲተካ በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል። አገራቱ፣ አፍሪካ ኅብረትና ቀጠናዊ ድርጅቶች ለድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ፍትሃዊ አጠቃቀም ተቋማዊ አሠራሮችን እንዲፈጥሩም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ዙሪያ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት የጀመሩትን ድርድር በመቀጠል ያልተቋጩ ልዩነቶችን እንዲፈቱ የጠየቁት ተሳታፊ አገራት፣ ዓረብ ሊግ በናይል ወንዝ ዙሪያ በሚያወጣቸው "የላይኛው ተፋሰስ አገሮችን ሕጋዊ መብት በሚጋፉ" መግለጫዎች መከፋታቸውንና በተመድ ጸጥታው ምክር ቤትና ሌሎች መድረኮች ላይ የናይል ወንዝን "ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች አፍራሽ መኾናቸውን" ገልጸዋል።

5፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት የአገሪቱን ማዕከላዊ ተጠባባቂ የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መቆጣጠሩን አስታውቋል። የተጠባባቂ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያው ታንኮችን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ክምችት የሚገኝበት ነው። ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት፣ በካርቱምና ኦምዱርማን አብዛኞች ቁልፍ መንግሥታዊ ተቋማትና አብዛኞቹ የኹለቱ ከተሞች ክፍሎች በፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ወድቀዋል።

6፤ የተመድ ድርጅቶች ሩሲያና ዩክሬን በጥቁር ባሕር ወደቦች የዩክሬንን የእህል ምርቶች ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የደረሱበት ስምምነት ካበቃ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ላይ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ቀውስ ያስከትላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የተመድ ረድዔት ድርጅቶች ይህን የገለጹት፣ ጀኔቫ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ነው። ሩሲያ ለውጭ ገበያ በምታቀርበው የእህል እና ማዳበሪያ ምርቷ ላይ ያሉ ዓለማቀፍ ማነቆዎች ካልተወገዱላት፣ ከስምምነቱ እንደምትወጣ ማስጠንቀቋን እንደቀጠለች ነው። በምሥራቅ አፍሪካ ሰባት አገራት፣ 60 ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ እጥረት እንደገጠመው የረድዔት ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ናቸው። በተመድና ቱርክ አደራዳሪነት ከሦስት ወር በፊት የታደሰው ይሄው ስምምነት፣ በሐምሌ አጋማሽ ይጠናቀቃል።

7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ5506 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ6416 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 66 ብር ከ2086 ሳንቲምና መሸጫው 67 ብር ከ5328 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ከ3892 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ5770 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
መቄዶንያ ለክረምቱ ከ500 በላይ አዛውንቶችን ለማንሳት አዳራሾች ማዘጋጀቱን አስታወቀ

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር አዲስ አበባ ላይ በክረምቱ ወገኖችን ጎዳና ላይ በዝናብ እንዳይሰቃዩ ከ500 በላይ አዛውንቶችን ለማንሳት አዳራሾችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፤ “በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአካባቢያችሁ ያሉ እድሜያቸው አዛውንት የሆኑ 60 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው አልጋ ላይ ያሉ እና የሚረዳቸው ልጅ የሌላቸው በ0979797979 ስልክ ቁጥር ቴሌግራም ላይ ምስል አድራሻና የሚያሳይ ሰው ስልክ ቁጥር ቢልኩልን በፍጥነት እናነሳለን!” ሲል ማኅበሩ ጠይቋል፡፡

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በሥሩ ከ7 ሺሕ 500 በላይ የተለያየ ችግር ያለባቸው አረጋውያንን በመደገፍ ላይ የሚገኝ ማኅበር ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ከተማ አያት ፀበል አካባቢ ከመንግሥት ባገኘው 3,600 ካ.ሜ ቦታ ላይ ከ2.3 ቢሊየን ብር በላይ በሚፈጅ ወጪ፣ ባለ 15 ወለል ዘመናዊ ሆስፒታል እና የአረጋውያን መኖሪያ በማስገንባት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

👉መልዕክቱ ለኹሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! ደውለው መጠቆም ለሚፈልጉ 8131 ላይ ይደውሉ፡፡
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራ ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቀዋል፡፡

በጤና ምክንያት የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከነሀሴ 1/2015 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5/2015 አሳውቄያለሁ ብለዋል።

ሰብሳቢዋ ሥራ እሰከሚያቆሙበት ቀን ድረስ ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር ሥራዎችን ለመሥራት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አስታውቀዋል፡፡

በ2011 ታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ከተሾሙበት ቀን ጀምሮ፤ ቦርዱ ራሱን ችሎ ምርጫን ማከናወን የሚችል ተቋም ለማድረግ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደተወጡም ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

ሰብሳቢዋ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ባለፉት አራት ዓመት ከስድስት ወራት ሦስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ኃላፊነቶች ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ” ብለዋል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በትግራይ ክልል መርዶ የተነገራቸው በዚህ መልኩ ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። ይህ የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በአጠቃላይ በአራት ዙር ነው መርዶው የሚነገረው ተብሏል፣ ይህ የሆነው በአንዴ ቢነገር ቀውስ ይፈጥራል በሚል ነው።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የቤት እና የቦታ ግብር እስካሁን ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ

በአዲሱ የቤት እና መሬት ግብር ክፍያ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የአበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብር አወሳሰን እና አሰባሰብ ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክተር ወንድማገኘሁ ካሳዬ አስታውቀዋል፡፡

የቤት እና የመሬት ግብሩ የሚከፈልበት ጊዜ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ብቻ እንደሚቆይ አስታውሰው፤ ከ90 ሺሕ በላይ የሚሆኑት የከተማው ግብር ከፋዮችም ቀደም ብለው ክፍያቸው እንዳጠናቀቁ ገልጸዋል፡፡

አክለውም፤ አሁን የመጀመሪያ ጊዜ እንደመሆኑ መጠን ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት በሚውሉት ላይ የ50 በመቶ ለንግድ ቤቶች ደግሞ የ25 በመቶ የሚሆነውን ክፍያ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን፤ የተሰጠው ቀነ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ ለሚመጡት ግን ተፈፃሚ እንደማይሆን መጠቆማቸውን አሐዱ ራድዮ 94.3 ዘግቧል፡፡
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja


Репост из: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
የ ' ቅጥር ደመወዝ ' አልበቃ ቢላት ፤ ፊቷን ወደ " ሊስትሮነት " ያዞረችው የምህድስና ምሩቋ ምንታምር በለጠ

" ስሜ ምንታምር በለጠ እባላለሁ።

በሊስቶር ስራ ነው የምተዳደረው አዲስ አበባ፤ ቦሌ አካባቢ ።

የተወለድኩት በአማራ ክልል ፣ ዳንግላ ከተማ ነው። ተወልጄ የተማርኩትም እዛው አካባቢ ነው።

እናት አባቶቼ አቅመ ደካማ ነበሩ። አሁን ላይ በህይወት የሉም ሁለቱም። እህቶች እና ወንድሞች አሉኝ።

ዩኒቨርሲቲ የገባሁት በ2007 ዓ/ም ነው በ2011 ዓ/ም በቴክስታይል ኢንጂነሪንግ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቄያለሁ።

ከተመረቅኩ በኃላ ስራ ፍለጋ ነበር የወጣሁት ፤ ስራ ቶሎ ማግኘት ከባድ ስለነበር ወደ ሐዋሳ ነው የሄድኩት።

ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገባሁ፤ በ2500 ብር ደመወዝ ስራ ጀመርኩ የስራ ድርሻዬ የጥራት ደረጃ ማስጠበቅ ቁጥጥር ነበር እሰራበት የነበረው ጨርቃ ጨርቅ ነው፣ ጋርመት ቲሸርቶች ሱሪ ይሰራል እሱ ላይ ጥራት መቆጣጠር ነበር የኔ ስራ።

እዚያ ሁለት ዓመት ሰራሁ ፤ ከዛ በጦርነቱም በ #AGOA / አጎዋ ምክንያት እየቀነሱ ነበር ድርጅቶቹ ሰራተኞችን ፤ ከእሱ ወጥቼ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።

አዲስ አበባ መጥቼ እንደጠበኩት ስራ አላገኘኹም። እየፈለኩኝ ነበር አንዳንድ ቦታዎችም ገብቻለሁ ፤ ደሞዝ የማይሰጥ ድርጅትም አጋጥሞኝ ያውቃል፤ ብዙ ተግዳሮቶችን አሳልፌያለሁ።

ሰው ቤት በተመላላሽነት ምግብ መስራትም ጀምሬ ነበር መጨረሻ ላይ ሊስትሮ / ጫማ ማስዋብ ጀመርኩ።

ዲግሪ ይዣለሁ ፤ ያሳፍራል ዲግሪ ጥቅም የለውም፤ በዲግሪ ስራ ማግኘት አልቻልኩም። ባገኝም ህይወቴን Survive የማያደርግ ፣ የቤት ኪራይ የማይከፍል ፣ ቤተሰብ የማያስተዳድር ፣ ህይወቴን የማይቀይር ደመወዝ ነው ያለው።

ቤተሰብ መርዳት ቀርቶ እራስን መቀየሪያ የለም ፤ እኔ ዩኒቨርሲቲ ስማር የገዛሁትን ልብስ ነው እስካሁን የምለብሰው ፤ ምናልባት ይሄን ሊስትሮ ከሰራሁ በኃላ ልገዛ እችላለሁ።

ከጥዋቱ 11:30 ከቤቴ እወጣለሁ ፤ ታክሲ ይዤ እዚህ ስራ ቦታዬ ላይ 12:30 ደርሳለሁ ፤ ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:40 ድረስ ስራ ቦታዬ ላይ እገኛለሁ።

ደስ ብሎኝ ነው የምሰራው፤ የራሴ መመሪያ አለኝ ፤ በጥዋት ተነስቼ መጥቼ እሰራለሁ፤ ለኔ መስሪያ ቤቴ ድርጅቴ ነው።

ወጣቱ ተስፋ መቁረጥ የለበትም ፤ ያኔ ተስፋ ቆርጬ እራሴን አልጎዳሁም አማራጭ ሳጣ ወደ ሊስትሮ ዝቅ ብዬ መስራት እንዳለብኝ አእምሮዬ ነገረኝ ፤ ይህንን በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ይሄን ወጥሬ ስለምሰራ እራሴን ለመቀየረ፣ ወደዓላማዬ ፣ ወደ መንገዴ ያስገባኛል።

ከዚህ በኃላ የተሻለ ነገር መስራት አስባለሁ። ከዚህ ቀጥሎ ከሞያዬ ጋር ስለሚያያዝ ወደ ፋሽን ፣ ጋርመንት ፣ ስፌት ሞያ ሰልጥኜ ፣ ትንሽዬ ማሽንም ይሁን ገዝቼ ወደዛ የማዘንበል እቅድ አለንኝ። "

BBC AMHARIC
-----------------------
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏


👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇

t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja

Показано 20 последних публикаций.