ebstv worldwide📡️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Welcome to EBS TV WORLDWIDE Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates. Don’t forget to share it with your friends.
@ebstvworldwidebot
@EbswhatsnewBot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций










ይህንን ጠቃሚ መረጃ ለመመልከት ወደዚህኛው https://t.me/ebstvnews የዜና ቻናላችን ቢገቡ ያገኙታል።


🔘በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ የተቋቋመው ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መመረቁ ተገለፀ።

🔘አካባቢው በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት የሚታወቅ መሆኑ ሲገለፅ በዚህ ሂደትም ብዙውን ጊዜ ብክነት እንደነበር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

🔘ፋብሪካው በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት እንደሚያስገኝ የገለፀው የጽ/ቤቱ መረጃ በሕገወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ እንደሚሆን ታምኖበታል።

🔘ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ አካል መሆኑ ሲገለፀ በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጣት ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያ መሆኑ ታውቋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የህዳር 11/2017 አበይት የዓለም ዜናዎች

🇷🇺🇺🇦 ሩሲያ በዩክሬን መዲና ኬይቭ ታካሂደዋለች ተብሎ በተሰጋው ግዙፍ የአየር ጥቃት ሳቢያ በመዲናዋ የሚገኙ የአሜሪካ፣ የጣሊያን፣ የግሪክ እና የሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች እየተዘጉ ነው ተባለ።

🇺🇦 የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አሜሪካ የምታደርግልን የጦር መሣሪያ ድጋፍ ከቆመ ከሩሲያ ጋር የገባንበትን ጦርነት ተሸናፊ እንሆናለን ሲሉ ተናገሩ።

🇮🇱🇮🇷 የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የዛሬ ወር ገደማ በኢራን ላይ ባካሄድነው ጥቃት የቴህራን የተወሰኑ የኒውክለር ጣቢያዎች መተናል ሲሉ ለሀገሪቱ ፓርላማ ተናገሩ።

🇿🇦 በቀጣይ የአውሮፓውያኑ 2025 የሚካሄደውን የቡድን 20 ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ እንድታዘጋጅ ደቡብ አፍሪካ ተመረጠች።

🔷 በሥልጣን ላይ ያሉት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሄ በምርጫው አሸናፊ ለሆኑት ተመራጩ ፕሬዝዳንት እንኳን ደስ አለዎት በማለት ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ ቃል ገቡ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews






የህዳር 10/2017 አበይት የዓለም ዜናዎች

🇺🇦🇷🇺 ዩክሬን ከአሜሪካ ያገኘችውን እረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ወደ ሩሲያ መተኮሷን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።

🇺🇦🇷🇺 የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የቀጠለውን የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የተጀመረበትን 1 ሺህኛ ቀን አስመልክቶ ባሰሙት ንግግር አጋር ሀገራት በሩሲያ ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

🇫🇷🇺🇸 የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዩክሬን ከአሜሪካ በተሰጣት ሚሳኤል ሩሲያን እንድትመታ የባይደን አስተዳደር መፍቀዱን አደነቁ።

🇹🇷🇸🇾 ቱርክ በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ በፈፀመችው የአየር ጥቃት ምክንያት በግዛቲቱ የሚኖሩ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ተቋረጠባቸው።

⚠️ የቡድን 20 ሀገራት መሪዎች በተለይ በታዳጊ ሀገራት ለተንሰራፋው የርኃብ አደጋ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲበጅ ጥሪ አቀረቡ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🔸የኢትዮጵያ መንግሥት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ ኢሮ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል፡፡

🔸የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ ዕጩ ሆነው የቀረቡት ተመራጩ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

🔸ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በፕሬዝዳንቱ መመረጥ የተሰማውን ደስታ በኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ ሥም ገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews






የህዳር 9/2017 አበይት የዓለም ዜናዎች

🇧🇷 የቡድን 20 አገራት መሪዎች በብራዚሏ ሪዮ ዲ ጄኔርዮ ከተማ ጉባዔአቸውን እያካሄዱ መሆኑ ተሰምቷል።

🇺🇸🇺🇦🇷🇺 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን ከአሜሪካ ያገኘችውን የረዥም እርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤል በመጠቀም ሩሲያን ማጥቃት እንደምትችል ለመጀመሪያ ጊዜ መፍቀዳቸውን ተከትሎ ሩሲያ የባይደንን ውሳኔ በእሳት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው ስትል ነቀፈችው።

🇺🇦🇺🇸 የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የሩሲያ ግዛቶችን ዘልቀን እንድንመታ በአሜሪካ የተሰጠንን ይሁንታ በደስታ እንቀበላለን ሲሉ ተናግረዋል።

🇹🇷 የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲኘ ታይብ ኤርዶአን የመንግሥታቱ ድርጅት በዓለም ላይ የሚከሰቱ ጦርነቶችን ማስቆም ተስኖታል ሲሉ ወቀሱ።

🇮🇱🇱🇧 እስራኤል በወሰደችው የአየር ጥቃት የሂዝቦላህ የሚዲያ ኃላፊ የነበሩት ሞሐመድ አፊፍን መግደሏን አስታወቀች።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ኢምፓወር አዲስ ለኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪዎች ምን ዕድል ይዟል? ከ55 ግዙፍ የቢዝነስ ኩባንያዎች  ጋር ሰርቻለሁ።


በኢትዮጵያ እስከአሁን የሪል እስቴት ሴክተር የሚመራበት ህግ አልነበረም፡፡በዚህም ምክንያት ኢንደስትው እንዳያድግና የቤት ዋጋ እንዳይቀመስ አድርጎት ቆይቷል፡፡እንዲሁም የህግ ሥርዓት አለመኖሩ በርካቶችን ላልተገባ ኪሳራ ዳርጓል፡፡
አሁን ላይ የሪል እስቴት ኢንዱስትሪው የሚመራበት አዋጅ ተዘጋጅቶ በረቂቅ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡በቅርቡም ጸድቆ ወደሥራ እንደሚገባ የሚጠበቅ ሲሆን በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች በአዋጁ ላይ ስጋትና ተስፋቸውን እየሰጡበት ይገኛሉ፡፡
ህጉ ጥብቅና በርካታ ቤት ገንቢዎችን ከገበያ እንደሚያስወጣ ሲሰጋ በአንጻሩ ለቤት ገዥዎች ዋስትና የሚሰጥ ነው፡፡
ለመሆኑ ይህ አዲሱ የሪል እስቴት አዋጅ ምን ምን ጉዳዮችን ስጋትና ተስፋዎቹ ምንድናቸው?በእነዚህንና ሌሎች ጉዳዮችን ከባለሙያዎች ጋር ቆይታ እድርገናል፡፡









Показано 20 последних публикаций.