Ethiopian Electric Utility


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Карьера


EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Карьера
Статистика
Фильтр публикаций


የስማርት ሜትር መሰረተ ልማት ዝርጋታ ለማከናወን የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመካከለኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ወደ ስማርት ሜትር ለመቀየር የሚያስችል የስማርት ሜትር መሰረተ ልማት ዝርጋታ የውል ስምምነት ዛሬ ተፈርሟል፡፡

የውል ስምምነቱ የተፈረመው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እና ፓዎርኮም ኤልቲዲ ከተባላ የኤስራኤል በኩባንያ ተወካይ ያቆብ ዳር መካከል ነው፡፡

የስማርት ሜትር መሰረተ ልማት ዝርጋታው ሁሉንም የመካከለኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን የሚያካትት ሲሆን 29 ሚለዮን 808 ሺህ 525 ዶላር እና 10 ሚሊዮን 242 ሺህ 075 ብር ተመድቦለታል፡፡

የመካከለኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ስማርት ሜትር መሰረተ ልማት ዝርጋታ ለማከናወን አንድ አመት ከስድስት ወር ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

የመካከለኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ስማርት ሜትር መሰረተ-ልማት ዝርጋታ የቅድመ ክፍያ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሙላት የሚያስችል ነው ፡፡

ተቋሙ በመጀመሪያ ምዕራፍ የከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቆጣሪ ወደ ስማርት የመቀየር ስራ ሙሉ በሙሉ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በቀጣይም ዛሬ ውል ከተገባው የመካከለኛ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞች በተጨማሪ የመኖሪያ ተጠቃሚ ደንበኞች ቆጣሪ በስማርት ለመቀየር በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

ተግባራዊ የሚደረገው ስማርት ሜትር መሰረተ ልማት ዝርጋታ ፕሮጀክት የሃይል ብክነትን ለማስቀረትና የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ለሁሉም መገናኛ ብዙኃን (የማዕድ ማጋራት መርሃ -ግብር የሚካሄድበት ቀን የተቀየር መሆኑን ስለማሳወቅ)

1446ኛውን ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል ፈጥር ምክንያት በማድረግ ነገ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ፒያሳ በሚገኘው የቀድሞ የተቋማችን ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር እንደምናከናውን በመግለፅ የዜና ሽፋን እንድትሰጡ ዛሬ ጠዋት በዚሁ ገፃችን ላይ መጠየቃችን ይታወሳል፡፡

ሆኖም መርሃ-ግብሩ ለሌላ ቀን የተዛወረ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር እየገለፅን፤ በቀጣይ ፕሮግራሙ የምናካሂድበት ቀንና ሰዓት የምንገልፅ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል

ከጋምቤላ - ደንቢዶሎ 66 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በብልሽት ምክንያት በቄለም ወለጋ ዞን በደንቢዶሎ ከተማ፣ ሳዮ ወረዳ፣ አንፊሎ ወረዳ፣ ሃዋ ጋላን፣ ሮቢ ገበያ ከተማ፣ መቻራ ከተማ፣ ጫንቃ ከተማ፣ ቃቄ ከተማ፣ ቄቤ ከተማ እና አካባቢዎቻቸው ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ተመልሷል።

የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁን ክቡራን ደንበኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን ።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ለሁሉም መገናኛ ብዙኃን

ተቋማችን በመደበኛነት ከሚሰጠው አገልግሎት ጎን ለጎን የተለያዩ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻቸን ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

በዚህም 1446ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል ፈጥር ምክንያት በማድረግ ነገ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ፒያሳ በሚገኘው የቀድሞ የተቋማችን ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ማዕድ የማጋራት መርሃ -ግብር ያከናውናል፡፡

ስለሆነምበተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በቦታው ተገኝታችሁ የዜና ሽፋን እንድትሰጡን የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ሪጅኑ 7ሺ 9 መቶ 75 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አደረገ

በኢትዮጵያ ኤሌክትክ አገልግሎት የጎንደር ሪጅን ባለፉት 8 ወራት 7ሺህ 9መቶ 75 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉ ተገለፀ፡፡

ሪጅኑ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራው ስራ 54.06 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር 158.4 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እንዲሁም 69 የተለያየ አቅም ያላቸው የትራንስፎርመር ተከላ ስራ ተከናውኗል፡፡

በተጨማሪም በሪጅኑ የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ በተሰራ የመልሶ ግንባታ ስራ 89.69 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር 59.41 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር 23 አጋዥ ትራንስፎርመሮችን የማስቀመጥ እና 27 የትራንስፎርመርአቅም ማሳደግ ተችሏል፡፡

የውሃ እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

የጎንደር ሪጅን 23 የአገልግሎት ማዕከል 228 የሳተላይት ጣቢያዎች ያሉት ሲሆን ለ136 ሺህ 800 ደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ከዚህም ውጥ 131 ሺህ 620 ደንበኞች የድህረ ክፍያ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ 5ሺህ 180 ደንበኞች ደግሞ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/@EthiopianElectricUtility
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/@ethiopian.electri
[Whatsapp] https://web.whatsapp.com/


በአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውንቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/power-interruption?lang=am


በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በከምባ 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመር ላይ በደረሰ ጉዳት በኮንሶ ዞን እና በአሊ ዞን ከቀን 24 /2017 ዓ.ም ጀምሮ የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክብሯን ደንበኞቻችን በወጪ መስመሩ ላይ ያጋጠመው ችግር ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን እንጠይቃለን።

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/@EthiopianElectricUtility
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/@ethiopian.electri
[Whatsapp] https://web.whatsapp.com/

5k 0 3 19 10

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የስራ እንቅስቃሴ እና የደንበኞች አስተያየት !!


ሃይል መቆራረጥ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው

በቃሊቲና አካባቢው የሚስተዋለውን ሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ቁጥር 9 አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤሊያስ ሻኙ ገለፁ፡፡

ማዕከሉ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች የሚስተዋለውን ሃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ያረጁ ምሰሶዎችን የመቀየር፣ የረገቡ መስመሮችን የማስተካከል፣ የትራነስፎረመሮችን አቅም ማሳደግ እና የሃይል ማመጣጠን ስራዎችን በማከናወን አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም 450 ያረጁ የእንጨት ምሰሶችን፣7 ትራንስፎርመር አቅም ለማሳደግ ተጠንቶ 2 ባለ 315 ኪ.ቮ.አ የተቀሩ ሲሆን ሌሎች በሂደት ላይ መሆናቸውን ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

ማዕከሉ ደንበኞች ለሚያቀርቡት የኃይል ጥያቄ መልስ መስጠት እና አዲስ ኃይል ፈላጊ ደንበኞችን በስታንዳርዱ መሰረት እያስተናገዱ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡

ስራ አስኪያጁ አክለውም በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስን ስርቆትና ጉዳት መከላከል የሁሉም ሃላፊነተ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እንደራሱ ንብረት ሊጠብቅ ይገባል ሲሉ መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡

የቁጥር 9 አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለ42 ሺ ደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን 22 ሺ ድህረ-ክፍያ 20 ሺ ቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ናቸው፡፡ በዚህም ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት የማዕከሉ ደንበኞች በዘመናዊ የክፍያ አማራጮች እየፈፀሙ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ከስነ-ምግባር ጥሰቶች ጋር የሚገናኙ ችግሮችን ለመጠቆም ይፋ የተደረገውን መተግበሪያ ይጠቀሙ!!


በአዲስ አበባ፣ ሸገር፣ ጅማ እና ድሬዳዋ ከተሞች የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውንቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/power-interruption?lang=am


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በኦ.ቢ.ኤን ይጠብቁን

ውድ ደንበኞቻችን ከ ነገ ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 3፡20-3፡40 በየሁለት ሳምንቱ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ /ኦ.ቢ.ኤን/ ቴሌቪዥን በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሚተላለፈውን ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

Kabajamtoota maamiltoota keenya guyyaa boruu kamisa Gurraandhala 25/2017 A.L.I. galgala 3፡20 hanga 3፡40-tti Oromiyaa Biroodkaastiing Neetwork(OBN) irratti walitti aansuun turban lama gidduutti altokko Sagantaan Afaan Oromoo kan tamsa’u ta’uu isiniif ibsaa saganticha akka hordoftan kabajaan isin affeerra.

TAJAAJILA ELEKTIRIKII ITIYOOPHIYAA


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከፍተኛ አመራሮች የመስክ ምልከታ አካሄዱ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከፍተኛ አመራሮች ኮተቤ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የልህቀት ማዕከል፣ የስካዳ ሲስተም፣ የብሄራዊ ሃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

በግንባታ ላይ የሚገኘውን የዲስትረቡሽን መቆጣጠሪያ ማዕከል (ስካዳ ሲስተም) ወቅቱን የጠበቀ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ እና አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ በመስክ ምልከታው ተጠቁሟል፡፡

የልህቀት ማዕከሉ ሁለገብ የሰው ኃይል ማሰልጠኛ፣ የምርምርና የልህቀት ማበልፀጊያ፣ ብሄራዊ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ስካዳ መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ አዳራሽ፣ የሰልጣኞችና እንግዶች ማረፊያ ቤቶች እና ክሊኒክን የያዘ ነው፡፡

በተጨማሪም የልህቀት ማዕከሉ የዲስትሪቡዩሽን ዕቃዎች ጥራት ፍተሻ እና ላብራቶሪ ፋሲሊቲዎችን የሚያሟላ ሲሆን አጠቃላይ ሲቪል ግንባታ ስራዎች ዘጠኝ የተለያዩ ስፋትና ከፍታ ያላቸው ህንፃዎች እንዲሁም ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ያካተተ ነው፡፡

በመስክ ምልከታው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እና የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ሪጅኑ 6 የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አደረገ

የሶማሌ ሪጅን በበጀት ዓመቱ 8 ወራት 6 የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን የሪጅኑ አገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረሚካኤል ገብሬ ገለፁ፡፡

ሃላፊው አክለውም ሪጅኑ ባለፉት በ8 ወራት በክልሉ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙት ወልጀኖ፣ ገላዲድ፣ አቡኩደን፣ ኦባታሌ፣ ኦማር እና በቆልማዮ የተሰኙ 6 የገጠር ቀበሌዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ቀበሌዎቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግም 110 ኪ.ሜ መካከለኛና 86 ኪ.ሜ ዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ፤1190 መካከለኛ እና 1903 ዝቅተኛ መስመር ኮንክሪት ምሰሶ ተከላ እንዲሁም 20 ትራንስፎርመር ተከላ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

ሪጀርኑ በቀጣይ አራት የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊ ግብዓት እንዲቀርብ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ተጠቃሚ ከሚሆኑት መካከል የነጎብ ዞን ከተማ የሆነው የኤለወይን እና የያሁፕ ወረዳ ይገኙበታል ብለዋል።

አያይዘውም ሪጅኑ የፀኃይ ኃይል ማመንጫዎችን በስፋት እየገነባ መሆኑን ጠቅሰው የበቆሎማዩ የገጠር ቀበሌን የፀኃይ ኃይል ማመንጫ በመገንባት ተጠቃሚ ተደርጓል፡፡

ለበቆልማዮ 23 ኪ.ሜ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 5 ትራንስፎርመሮች ተከላ መከናወኑን የገለፁት የ10 ቀበሌዎች የፀሀይ ኃይል ማመንጫዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ኃላፊው የሶማሌ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በእቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦ http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1323?lang=am



Показано 16 последних публикаций.