የአዲስ አበባዉ የዐሊ መስጊድ ጉዳይ በሽምግልና ተይዞ ስለነበር ሂደቱ በዚያዉ አቅጣጫ ይፈታል የሚል እምነት ነበረኝ። መጅሊሱ የሽምግልናውን ውጤት ተከትሎ የአንድን መስጊድ ችግር መፍታት አለመቻሉ ያለንበትን አሳዛኝ ሁኔታ ያሳያል፡፡ ሲፈጸሙ የከረሙ ነዉሮችና ትላንት በማህበራዊ ሜዲያ ሲሰራጩ ያደሩ ምስሎች እጅግ የሚያሙ ከመሆናቸዉ የተነሳ ሀላፊነት እንደሚሰማዉ አንድ ዜጋና ሙስሊም የበኩሌን ማለት እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ በዚህ የተከበረ ወር በድ*ብደ*ባ ዓይኑ የጠፋ፣ አናቱ የተ*ፈ*ነከተ፣ በስ*ለ*ት ተ*ወ*ግ*ቶ የሚያቃስት ወዘተ ወንድሞችን ማየት፣ የእናቶችን ለቅሶ መስማት እጅግ ሲበዛ ያሳዝናል፤ ይሰቀጥጣል፡፡
ዐሊ መስጊድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች የገጠመዉን ፈታኝ ሁኔታ ለማየት የሚያስችል አንድ ናሙና ነዉ፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ተመሳሳይ ወይም የባሱ ፈተናዎችን ማስተናገዱን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ምንድን ነዉ የተፈጠረዉ? አሁን ካለንበት ሁኔታ ዉስጥ እንዴት ልንገባ ቻልን? ወደፊትስ ምን ዓይነት ሁኔታ ይጠብቀናል? እንዴትስ መዉጣት ይቻለናል? የሚሉ ጥያቄዎች እያንዳንዱን ሙስሊም ዜጋ ሊያሳስቡ የሚገቡ ናቸዉ፡፡ ስለሆነም አጠቃላይ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያመላክት የምክክር መድረክ ይዘጋጅ ዘንድ የሀገር ሠላምና የዜጎች ደህንነት ለሚያሳስባቸዉ የሁሉም ወገን የእስልምና ሊቃዉንት (ዑለሞች)፣ መምህራን (ዳዒዎች)፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት የሚጠበቅባቸዉን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡
በሀገሪቱ ትርጉም ያለዉ አሀዝ ያላቸዉ ዜጎች ሰቆቃና ዋይታ ከጫፍ ጫፍ በሚሰማበት በዚህ ወቅት በየትኛዉም ግላዊም ሆነ ቡድናዊ ስሌት ተሸብቦ ዝምታን መምረጥ ከአላህ ፊት ተጠያቂ፣ በታሪክም ተወቃሽ የሚያደርግ ነዉር መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ።
https://t.me/hassentaju