ኢትዮ መረጃ - NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@B_promotor

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ሕብረተሰቡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎቹን እንዲያቀርብ ጥሪ ቀረበ

ሕብረተሰቡ በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚ ጉዳዮችና አምራች ዘርፎች ላይ ጥያቄዎቹንና ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን እንዲያቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

በዚሁ መሠረት ሕብረተሰቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች አማካኝነት ጥያቄዎቹን መላክ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡበት ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አረጋግጧል፡፡

ጥያቄያችሁን አቅርቡ ………


"በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል"
- ሌተናንት ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ

ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል "በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል" በማለት አስጠነቀቁ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በግልጽ የሚታይ መቃቃር አለ። የእኔ ስጋት ይህ ከቃላት አልፎ ወደ ጦርነት እንዳያድግ ነው" ብለዋል።

ጦርነቱ ለቀጠናውም ዳፋ እንደሚሆንም ጄኔራል ፃድቃን በእንግሊዘኛ ባስነበቡት ጽሑፍ አስታውቀዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረግ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች እንደሚባለው "አጭርና ወሳኝ" እንደማይሆን የገለጹት ጄኔራል ፃድቃን ለቀጠናው አውዳሚ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

"ጦርነቱ ሲያከትም አሁን የምናውቀው የአገራቱ ጂኦግራፊ ይለወጣል። በአፍሪካ ቀንድና ከቀይ ባሕር አሻግሮም ጉልህ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጥ ያስከትላል" ብለዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ የሆኑት ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሚቀሰቀሰው ጦርነት "የሱዳንና የቀይ ባሕር ደኅንነት ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ያሳድራል" ብለዋል።

"በጦርነቱ ማዕከላዊ የምትሆነው በደንብ የሠለጠነና ልምድ ያካበተ ከፍተኛ የወታደር ቁጥር ያላት ትግራይ ናት" ሲሉም አክለዋል።
(BBC)

@sheger_press
@sheger_press


መቀሌ ውጥረት ነግሷል‼️

ዛሬ ለሊቱን ጀምሮ ብዛት ያለው  ሰራዊትና መትረየስ የጫኑ ፓትሮል መኪኖች በመቀሌ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ  እንቅስቃሴ እያደሩጉ እንደሚገኙ ታውቋል

በደብረፂዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ህዝባዊ ሰራዊታችን በከሃዲ ቡድን ሴራ አይፈርስም ብሏል።

ህወሓት በመግለጫው የግዚአዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ብሄራዊ ክህደት የፈጸሙ እና እየሰሩ ያሉ አመራሮችን በማባረር በጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያላቸውን ውክልና አንስቻለሁ ያለ ሲሆን ነገር ግን ጊዚያዊ ፕሬዝዳንቱ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት ከህግና ስርዓት ውጪ ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።

የህዝባችንን አንድነት በማደፍረስ የትግራይን ሁለንተናዊ አቅም በማዳከም ብሄራዊ ክህደት እየፈፀመ ያለው የቀድሞ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ለመፋለም የተደራጀውን የትግራይ ሰራዊት ለመበተን ድርጊቱን አጠናክሮ ቀጥሏል"ብሏል።

የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከስልጣናቸው እና ከኃላፊነታቸው ውጪ የትግራይ ጦር ግንባር አመራሮችን እና ጄኔራሎችን  አግደዋል ያለው ህወሃት፣ይህ ማዕቀብ መሠረተ ቢስ እና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ቢሆንም ህዝባዊ ትግሉን ከህግ እና ከስርዓት ውጭ ለማድረግ ቡድኑ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን ያሳያል ማለቱን።

@sheger_press
@sheger_press


በባለሀብቶች የታሪፍ ፍራቻ የተነሳ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ነው ተባለ

ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታሪፍ በአለም ኢኮኖሚ እድገት እና በነዳጅ ፍላጎት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ፣ እንዲሁም ከኦፔክ የነዳጅ አምራች ሀገራት የነዳጅ ምርት እየጨመረ በመምጣቱ፣ ባለሃብቶች ላይ ስጋትን አሳድራል። ያልተጣራው ድፍድፍ ነዳጅ አርብ እለት 90 ሳንቲም በ6 ሳንቲም ቀንሶ ወደ 70.30 ዶላር ዝቅ ብሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ዌስት ቴክሳስ ገበያ ድፍድፍ በ ነዳጅ በ66.96 ዶላር በበርሚል የተሸጠ ሲሆን በስምንት ሳንቲን ቀንሷል።

ለሰባተኛ ተከታታይ ሳምንት ነዳጅ ቀንሷል፣ ይህም ከህዳር 2023 ወዲህ ረጅሙ የኪሳራ ጉዞ ተደርጎ ተወስዷል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ ግብር መጣላቸው እንዲሁን በዋና ዘይት አቅራቢዎቻቸው ላይ ካናዳ እና ሜክሲኮ የዘገየ ታሪፍ ከጣሉ በኋላ ድፍድፍ ነዳጅ ለሶስተኛ ተከታታይ ሳምንት ቀንሷል። ቻይና በአሜሪካ እና ካናዳ የግብርና ምርቶች ላይ የአፀፋ ታሪፍ መጣሏ ይታወሳል።

ትራምፕ ሞስኮ ከዩክሬን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻለች ዩናይትድ ስቴትስ በሩስያ ላይ የምትጥለውን ማዕቀብ እንደምትጨምር ከተናገረች በኋላ አርብ እለት የነዳጅ ዋጋ ቀንሷል። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ለማቆም ከተስማማች ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ የኃይል ማመንጫ ዘርፍ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለማርገብ የሚያስችል መንገድ እያጠናች ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚያውቁ ሁለት ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦፔክ ፕላስ በመባል የሚታወቀው ሩሲያን ጨምሮ የነዳጅ ላኪ ሀገራት ድርጅት እና አጋሮቹ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በዘይት ምርት ጭማሪ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ እንዳሉት ኦፔክ ፕላስ የገበያ ሚዛን በሚኖርበት ጊዜ ውሳኔውን ሊቀይር ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።


ወቅታዊ እና እውነተኛ የመረጃ እጦት ለጋጠማችሁ፣ የቱን ልመን? ብላችሁ ለተወዛገባችሁ ፣  እነሆ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ መረጃዎችን ካሉበት አጣርቶና ፈልፍሎ ልምድ ባላቸው ጋዜጠኞች የሚያቀርብ  ቻናል ልጠቁማችሁ።

መረጃዎቹ ለየት ያሉ ፈጣን እና እውነተኛ ናቸው።👌""በዚህ ሊንክ ግቡ
👇👇👇
ሊንክ👇
https://t.me/Addisinsider_ETH
https://t.me/Addisinsider_ETH


የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

ኢትዮጵያ ብዝሃ ሀይማኖት የሆነች ሀገር እንደ መሆኗ የተለያየ እምነት ተከታዬች ለዘመናት ተፈቃቅደውና ተከባብረው ኖረውባታል። እየኖሩባትም ይገኛሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ይህንን በጎ እሴት በመሸርሸር ውዝግብና ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡

በተለይም የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተረድቷል።

ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ም/ቤቱ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ በመሆኑ የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የጥላቻ ንግግር በየትኛውም ወገን ቢሰነዘር ጠቅላይ ም/ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንደሚሰራም ማወቅ ይገባል፡፡

በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብርየሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ ያሳስባል።

በመሆኑም፡-
1. የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ከመክረሩ በፊት የጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስን።

2. ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤

3. የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤ እንዲሁም

4. ወቅቱ በሙስሊሞች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የፆም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ጠቅላይ ም/ቤቱ የእስልምና አንኳር እሴቶችን በተለይም የፈጣሪያችንን አሏህ፣ የነቢያትን፣ የመለኮታዊ መፃህፍትንና የደጋግ ተከታዮችን ክብር የሚያጎድፉ ማንኛውም አይነት የጥላቻ ትንኮሳና ድርጊት በህግ አግባብ እንዲታረሙ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚወጣም ይሆናል፡፡

ለእውነተኛ ሰላምና አብሮነት የሚቆረቆሩ አካላት ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዙና ለፍትህ እንዲሰሩም ጠቅላይ ም/ቤቱ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

@sheger_press
@sheger_press


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በጥላቻ ንግግር ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

ኢትዮጵያ ብዝሃ ሀይማኖት የሆነች ሀገር እንደ መሆኗ የተለያየ እምነት ተከታዬች ለዘመናት ተፈቃቅደውና ተከባብረው ኖረውባታል። እየኖሩባትም ይገኛሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ይህንን በጎ እሴት በመሸርሸር ውዝግብና ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡

በተለይም የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተረድቷል።

ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ም/ቤቱ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ በመሆኑ የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የጥላቻ ንግግር በየትኛውም ወገን ቢሰነዘር ጠቅላይ ም/ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንደሚሰራም ማወቅ ይገባል፡፡

በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብርየሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ ያሳስባል።

በመሆኑም፡-
1. የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ከመክረሩ በፊት የጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስን።

2. ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤

3. የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤ እንዲሁም

4. ወቅቱ በሙስሊሞች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የፆም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ጠቅላይ ም/ቤቱ የእስልምና አንኳር እሴቶችን በተለይም የፈጣሪያችንን አሏህ፣ የነቢያትን፣ የመለኮታዊ መፃህፍትንና የደጋግ ተከታዮችን ክብር የሚያጎድፉ ማንኛውም አይነት የጥላቻ ትንኮሳና ድርጊት በህግ አግባብ እንዲታረሙ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚወጣም ይሆናል፡፡

ለእውነተኛ ሰላምና አብሮነት የሚቆረቆሩ አካላት ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዙና ለፍትህ እንዲሰሩም ጠቅላይ ም/ቤቱ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ


ባለው የፀጥታ ሁኔታ ለምዕራብ ትግራይ ዞን መድኃኒት ማሰራጨት አልተቻለም ተባለ።

ለምዕራብ ትግራይ ዞን በተለይ ለማይፀብሪ ወረዳ መድኃኒት ለማሰራጨት መቸገሩን በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሽሬ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለጣቢያችን አስታውቋል።

የፅ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ሙሌ አብርሃ ፤ መድኃኒቶችን ለሶስት ዞኖች የምናሰራጭ ቢሆንም ለምዕራብ ትግራይ ግን ማድረስ አልቻልንም ብለውናል።

በተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢመጡም በእኛ በኩል የሚቻል ባለመሆኑ በጎንደር ቅርንጫፍ በኩል እንዲደርሳቸው ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ከወረዳው ሁለት ጊዜ መድኃኒት እንድንሰጥ ተጠይቀን ነበር የሚሉት ሃላፊው፤ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ጥያቄያቸውን መመለስ አልተቻለም ነው ያሉት።

የወባም ሆነ የኤችአይቪ መድኃኒቶች አሁን ላይ ችግር የለብንም ያሉት ሃላፊው፤የብድር ሁኔታ ግን አስቸጋሪ ሆኖ ቀጥሏል ብለውናል።

በብድር መድኃኒቶችን ወስደው ፤ ብድራቸውን ያልጨረሱ ስለመኖራቸውም አንስተዋል።

Ethio Fm

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ለሕወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሆነ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ

አንዳንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ረገብ እያለ የቀጠለው የሕወሓት አመራሮች ሽኩቻ መነሻው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የተሳተፈው የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ምን መፈጸምና አለመፈጸም እንዳለበት በተገቢው ሁኔታ ሳይደራደር ትዕዛዝ ተቀብሎ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን፣ የሕወሓት አንደኛው ክንፍ ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።
ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ዘ ኒው ሂዩማኒታሪያን ከተሰኘ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት አሁን በትግራይ ፖለቲካ ልሂቃን መካከል ለሚታየው መቆራቆስ ዋነኛ ምክንያት ነው፤›› በማለት ስምምነቱን ‹‹የክፍፍሉ መነሻ›› ብለውታል።
አቶ ጌታቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይዘውት የተጓዙት ተደራዳሪ ቡድን በጦርነት ለደቀቀችው ትግራይ፣ ‹‹ጦርነቱን ብቻ እንዲያስቆምና ከዚያ ያለፈም ያነሰም ነገር እንዳይፈጽም ነበር ተልዕኮ የተሰጠው፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ የክልሉን መንግሥት የሚያፈርስ ትዕዛዝ ጭምር ይዘው መጥተዋል...

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


#መምህሩን በሃይማኖት የመሰለው አብሪ ኮከብ 

ቅዱሱ ታላቅ የሃይማኖት ጠበቃ ሲሆን የተወለደው ግብጽ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው፡፡ ሲሆን በምግባሩ፣ በትምሕርቱ ለምዕመናን ጥቅም ሆኗቸዋል፡፡ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ገና ልጅ ሳለ ምሥጢረ ክርስትናን ይማር ዘንድ ወደ ተፍጻሜተ_ሰማዕት ቅዱስ_ዼጥሮስ ሔዷል፡፡ ቅዱስ ዼጥሮስ የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክና ሊቅ ሲሆን በታሪክ የዘመነ ሰማዕታት መጨረሻ ተብሎ ይታወቃል፡፡ እርሱ ያስተማራቸው ብዙ አርድእት ቢኖሩም 3ቱ ግን ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ አኪላስ ውዳሴ ከንቱ ወዳጅ፣ ሆዱ ዘመዱ፣ አርዮስ ደግሞ ወልድ ፍጡር ያለ የቤተ ክርስቲያን ጠላት ሆኑ፡፡ አኪላስ ስለ ምንም የማይጨንቀው ሰው ነበር፡፡ ደጉ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በሃይማኖት በመመሰል በጾምና በጸሎት እየተጋ መምሕሩን ቅዱስ ዼጥሮስን ለመተካት ለመምሰል ይጥር ነበር::

ወቅቱ ዘመነ ሰማዕታት እንደ መሆኑ ቅዱሱ ከመምሕሩ ጋር ብዙ ነገሮችን አሳልፏል፡፡ አርዮስ ክዶ ቅዱስ ዼጥሮስ ካወገዘው በሁዋላ እንደ ባልንጀራ ገስጾ ሊመልሰውም ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን የአርዮስን ክፋት ከጌታ ዘንድ የተረዳው ቅዱስ ዼጥሮስ ደቀ መዝሙሩን እለእስክንድሮስን ጠርቶ መከረው፡፡ "እኔ ከሞትኩ በሁዋላ አኪላስ ይተካል:: ከአርዮስ ጋር ስለሚወዳጅ በ6 ወሩ ይቀሠፋል:: አንተ ግን ከአርዮስ መርዝ ተጠበቅ" አለው:: ይህንን ካለው በሁዋላ ወታደሮች የቅዱስ ዼጥሮስን አንገት ቆረጡ:: ይህ የተደረገውም እ.ኤ.አ በ311 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም አኪላስ ተሾመ:: እንደ ተባለውም ከአርዮስ ጋር ስለተወዳጀ በ6 ወሩ ተቀሰፈ:: በዚያው ዓመትም ቅዱስ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ ወይም ግብጽ 19ኛ ፓትርያርክ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ::

ሊቁ ሲሾም መልካም አጋጣሚ የነበረው ያ የመከራ ዘመን ማለፉ ሲሆን በጣም ከባዱ ግን የአርዮስ ተከታዮች ከተገመተው በላይ መበብዛታቸው ነው፡፡ ቅዱሱ በዽዽስ መንበሩ ለ17 ዓመታት ሲቆይ ዕንቅልፍና ዕረፍትን ትቶ እየጾመ፣ እየጸለየ፣ ምዕመናንን ከአርዮስ የኑፋቄ መርዝ ለመታደግ በቃልም በደብዳቤም መሸ ነጋ ሳይል ሕዝቡን እያስተማረ ታግሏል፡፡ በመጨረሻም በ325 ዓ.ም በንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አዋጅ በተዘጋጀው የኒቂያ ጉባኤ ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ካሳለፉ ከ318 ሊቃውንት ጋር አውግዞታል ለይቶታል፡፡ በጉባኤው መጨረሻም ጸሎተ ሃይማኖትን ሠርተው፣ መጽሐፈ ቅዳሴ ደርሰው፣ 20 ቀኖናወችን አውጥተው፣ አሥራው መጻሕፍትን ወስነው፣ ቤተ ክርስቲያንን በዓለት ላይ አጽንተው ተለያይተዋል:: የዚህ ሁሉ መሪ ደግሞ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ነው::

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልድ ዋሕድ፣ አምላክ ወልደ አምላክ፣ የባሕርይአምላክ፣ መሆኑን መስክሮ ክብርን አግኝቷል፡፡ የእምነታችንም መሠረቱ ይሔው ነው፡፡ ክርስቶስን ከአባቱ ጋር በመለኮቱ የሚተካከል ብለው ካላመኑ እንኩዋን ድኅነት ክርስትናም አይኖርም፡፡ ከጉባኤ ኒቅያ በሁዋላ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመልካሙ ጐዳና ሲጋደል ምዕመናንንም ሲያጸና ኑሯል፡፡ ዘወትር ወንጌልን በፍቅር ያነብ ነበርና ሲጸልይ የብርሃን ምሰሶ ይወርድለት ነበር፡፡ ስለ ውለታውም ቤተ ክርስቲያን በግብጽ ካበሩ 5ቱ ከዋክብት ሊቃውንት እንደ አንዱ ታከብረዋለች፡፡ ቅዱሱ ሊቅ በ328 ዓ.ም ዐርፎ በክብር ተቀብሯል፡፡


ገዳማዊያን በዓለም ላለነው ለኛና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገራችንም ይጸልያሉ፡፡ ገዳማቸውን በመርዳት፣ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡ 


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብርና ታክስ በተጨማሪ በሌሎች ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ ተገለፀ

የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ፎረም በከተማው ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ከባድ ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን ገልጿል። ፎረሙ የባለሀብቶችን ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

የባለአብቶች ፕሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ለካፒታል እንደገለጹት፣ ባለሀብቶቹ ያላግባብ ድርጅቶቻቸው መታሸግ፣ መፍረስ፣ መነጠቅ (መቀማት)፣ ሥራ እንዲያቆሙ መደረግ፣ ያላመኑበትን ከፍተኛ ግብርና ታክስ ለማስከፈል ማስገደድ፣ የባንክ አካውንታቸው መታገድ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ወይም እንዳይገቡ እየተደረጉ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በስልክ ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረስ፣ የማያምኑበትን አሰልቺና ተደጋጋሚ መዋጮዎች መጠየቅ፣ እንዲሁም ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳይከውኑ ማዋከብ፣ የብድር አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ያለማግኘት እና የመሳሰሉት ችግሮች እየደረሱባቸው መሆኑን ሰምተናል ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ፎረሙ ከመጋቢት 01 እስከ 27 ቀን 2024 ዓ.ም ድረስ የከተማውን ባለሀብቶች ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል መዘጋጀቱንና ባለሀብቶችም መረጃቸውን በሰነድ በማቅረብ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።

የባለሀብቶቹ ቅሬታ ከተሰበሰበ በኋላ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ችግሮቹ እንዲፈቱ ፎረሙ እንደሚሰራ አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ተናግረዋል
@ethio_mereja_news


ከነፍሳችን በላይ አብልጠን በምንወዳቸው ውዱ ነብያችን ክብር የማንደራደር መሆኑን ሁሉም ሊያውቅ ይገባል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ከሰሞኑ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ድምበር የሚያልፉ ግለሰቦችን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የዳዕዋ መድረክ በርካታ ሙስሊሞች በተገኙበት መልዕክት ያስተላለፉት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ "ከነፍሳችን በላይ አብልጠን በምንወዳቸው ውዱ ነብያችን ክብር የማንደራደር መሆኑን ሁሉም ሊያውቅ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።

"እኛ እምነታችን በምናስተምርበት ወቅት ፈፅሞ የሰዎች እምነት ላይ ድንበር አናልፍም እስልምናም ያንን አያዘንም ያሉ ሲሆን ሌሎች የእምነት ተቋማትም ድንበር የሚያልፍ ግለሰቦችን ተው ሊሉ ይገባል" ብለዋል።

"እንደ ተቋም በህግ መሄድ እስካለብን ጥግ ድረስ እንሄዳለን ያሉ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በተለይ ወጣቱ በሰላማዊ መንገድ እምነቱን ማስከበር አለበት" ሲሉ ገልፀዋል።

©️ ሀሩን ሚዲያ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ጥቆማ‼️

በሀገራችን ታማኝ የዜና ምንጮችን የሚያገኙበት የቴሌግራም ቻናል ነው!

ሊንክ👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግስት ማሻሻያ ላይ አቤቱታ ያቀረቡ የክልል ምክር ቤት አባል ታሰሩ 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ተመራጭ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ተሰማ ዛሬ እሁድ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ተኩል ገደማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለቤታቸው እና የፓርቲው ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። አቶ ዮሐንስ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው አስቀድሞ፤ “የጉዞ እግድ እንደተጣለባቸው” ተነግሯቸው ከአሶሳ አየር ማረፊያ እንዲመለሱ መደረጋቸውንም ምንጮቹ ተናግረዋል።

አቶ ዮሐንስ ዛሬ ጠዋት በአሶሳ አየር ማረፊያ የተገኙት፤ ጽህፈት ቤቱ በአዲስ አበባ ለሆነው ለፌደራል የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ያስገቡትን አቤቱታ በአካል እንዲያስረዱ በመጠራታቸው እንደሆነ ምንጮቹ አስረድተዋል። ለአጣሪ ጉባኤው የቀረበው አቤቱታ፤ ከአቶ ዮሐንስ በተጨማሪ አቶ አመንቴ ገሺ እና አቶ ተስፋሁን ኪሉ የተባሉ የቦዴፓ የክልል ምክር ቤት ተመራጮችን ስም የያዘ ነው።

አቤቱታው ከሁለት ሳምንት በፊት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ የጸደቀውን የክልሉ ህገ መንግስት ማሻሻያ የተመለከተ ነው። የህገ መንግስት ማሻሻያው “የኢፌዲሪን ህገ መንግስት የሚቃረን ነው” ሲሉ በአቤቱታቸው የጠቀሱት፤ ሶስቱ የክልል ምክር ቤት አባላት አጣሪ ጉባኤው የህገ መንግስት ትርጓሜ በመስጠት “ተፈጻሚ እንዳይሆን” እንዲያደርግ ጠይቀው ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


በእነ ጆን ዳንኤል የክስ መዝገብ በተከሰሱ ተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ጉዳይ ላይ ዉሳኔ ሊሰጥ ነዉ ፡፡

አንደኛዋ ተከሳሺ ነፍሰጡር ስለሆነች እና የመዉለጀዋ ጊዜዋ ስለተቃረበ ፍርድቤቱ በልዩ መዝገብ እንዲመለከተዉ ተጠይቆል ፡፡


መረጃ ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ የሚካሄዱ መደበኛ ያልኾኑ ንግዶችን በሥርዓት ለማስተዳደር የሚያስችለውን ረቂቅ ደንብ ዛሬ ተወያይቶ ማጽደቁን አስታውቋል።

የከተማዋ አስተዳደር የደንቡን ዝርዝር ይዘት ለጊዜው አልገለጠም። ኾኖም የአስተዳደሩ ጸጥታ አካላት በከተማዋ የፈጣን ምግብ ሽያጭን ጨምሮ በጎዳና ላይ የተለያዩ ንግዶችን በሚያካሂዱ በአነስተኛ ገቢ በሚተዳደሩ ዜጎች ላይ የኃይል ርምጃ ይወስዳሉ የሚል ቅሬታ ሲቀርብባቸው ቆይቷል።

የአስተዳደሩ ካቢኔ በዛሬው ስብሰባው፣ በከተማዋ የምሽት የንግድ ቤቶችንና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫዎችን የአገልግሎት ሰዓት ለማራዘም የተዘጋጀውን ረቂቅ ደንብ ማጽደቁንም ገልጧል።


#ምኩራብ፣ የቤትህ ቅናት በላኝ

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዐቢይ ጾም ሶስተኛ ሣምንት ምኩራብ ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምኩራብ የገባበትና ያስተማረበት ነው፡፡ ምኩራብ ማለትም ቀጥተኛ ፍቺው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 2÷12-ፍጻሜው ይነበባል፡፡ “የአይሁድም የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን÷ ርግቦችንም የሚሸጡትን፣ ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፡፡ የገመድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎችንና በሬዎችን፣ ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣ፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፡፡ ርግብ ሻጮችንም÷ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ” አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም÷ “የቤትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል በመዝ. 68÷9 ተጽፎ እንዳለ ዐሰቡ፡፡”

ጌታችን ከጥምቀቱ በፊት ወደ ቤተመቅደስ የመጣባቸው በርካታ አጋጣሚዎች ቢኖሩም ሁለቱ ግን ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ የመጀመሪያው ሉቃስ 2÷22-40 በሥርዓተ ኦሪት መሰረት በተወለደ በአርባኛው ቀን ወደ ቤተመቅደስ መምጣቱ፣  ሁለተኛ በሉቃ 2÷41-47 እንደምናገኘው ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲሆነው ከዮሴፍና ከእመቤታችን ጋር ለበዓል ወደ ኢየሩሳሌም በሄዱ ጊዜ ከእነርሱ ተለይቶ በቤተመቅደስ በመቅረት የኦሪት ሊቃውንትን ሲጠይቃቸውና ሲሰማቸው የነበረበት አጋጣሚ ናቸው፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ አገልጋዮቹ በሥጋዊ ፍላጎታቸው ምክንያት በቤተመቅደሱ የማይገባ ሥራ እየሰሩ ቢያይም አምላክነቱን ገልጦ የሚያስተምርበት፣ የሚገስጽበት ጊዜ አልደረሰምና በዝምታ አልፏቸው ነበር፡፡

ከጥምቀቱ በኋላ ግን በሁለት አጋጣሚዎች ቤተ መቅደሱን አጽድቷል፡፡ ቀዳሚው በመጀመሪያው ፋሲካ አገልግሎቱን ሲጀምር ያደረገውና ከላይ በዮሐንስ ወንጌል የገለጽነው በምኩራብ ሣምንት የሚነበበው፣ የሚተረጎመው ነው፡፡ ጌታችን ለሁለተኛ ጊዜ ቤተመቅደሱን ሊያነፃ የሄደው ለመከራና ለሞት ተላልፎ ከመሰጠቱ አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና፣ በማቴ 21÷12-17 የሚገኘው ነው፡፡ በዚህም ወቅት በተመሳሳይ ገዥዎችንና ለዋጮችን፣ እንዲሁም የቤተመቅደስ አለቆችን “ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፣ እናንተ ግን የሌቦችና የወንበዴዎች፣ ቀማኞች ዋሻ አደረጋችኋት” በማለት የገሰጸበት ነው፡፡ ስለሆነም ትንቢተ ነቢያትን የፈጸመ ጌታ በአገልግሎቱ መጀመሪያና ፍፃሜ ላይ ወደ ቤተመቅደስ የመጣው ቤተመቅደሱን ለማንፃት ነበር፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተመቅደስ ሲመጣ በቤተመቅደሱ እንስሳት የሚሸጡ የሚለውጡ ሰዎች እንደ ብሉይ ኪዳን ሥርዓት ለኃጢአት ማስተስረያ መስዋእትነት የሚቀርቡ ነበሩ፡፡ የካህናት አለቆችና ግብር አበሮቻቸውም በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እንስሳት ለመስዋእት ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ በመስጠት በምትኩ ገንዘብ እየተቀበሉ አገልግሎቱ መልኩን ቀይሮ ንግድ ሆኖ ነበር፡፡ እንስሳቱን የሚሸጡት ሰዎችም ስለሚያገኙት ትርፍ እንጂ ስለ መስዋእቱ ንጽህና አይጠነቀቁም ነበር፤ ከጌታ የሚገኝ ሰማያዊ ጸጋን በመሸጥና በመለወጥ በሚያገኙት ትርፍ የቀየሩ ነበሩ፡፡

ታዲያ ወደ ቤተመቅደስ የመጣው ለፍርድ ሳይሆን ለማንፃት ነበርና ሻጮችና ለዋጮችን ሰዎች ሳይሆን የሚሸጡትንና የሚለወጡትን ርግቦችን፣ በጎችን፣ በሬዎችን፣ የሰዎቹን የሚለወጥ ገንዘብ ከቤተ መቅደስ አስወጣ፡፡ የቤተ መቅደሱ ባለቤት ዳግም ይመጣል፡፡ የሚመጣው ግን እንደቀደመው ለማንፃት ሳይሆን ለፍርድ ነውና በምግባር በሃይማኖት ጸንተን፣ በጸሎትና በምጽዋት ተግተን እንጠብቀው፡፡


ገዳማዊያን በዓለም ላለነው ለኛና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገራችንም ይጸልያሉ፡፡ ገዳማቸውን በመርዳት፣ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡ 


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




ኢትዮጵያ ድሮን ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ገንብቻለሁ አለች!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) የሚያመርተውን የስካይ ዊን ኢንዱስትሪን መርቀው በከፈቱበት እንዳስታወቁት ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ ያሳድጋል ፡፡

ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ የሚያሳድጉ ናቸው ተብሏል፡፡ድሮኖቹ በከፍተኛ መልካዓ-ምድር ላይ በብቃት አገልግሎት የሚሰጡና ጸረ-ድሮን ጭምር የታጠቁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡ኢንዱስትሪው ድሮኖችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም አለው ብለዋል ፡፡

@ethio_mereja_news

8.4k 0 6 21 113
Показано 20 последних публикаций.