ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


🇪🇹🇪🇹🇪🇹ስለ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀን በቀን የሚወጡ ዜናዎችን እና እንዲሁም አለም አቀፍ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን 🙏ሰላምና ፍቅር ለእናት ሀገራችን ይሁን❤
👉 ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Gebrel or @Wizbeki7 ያናግሩን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


1GB ስንት MB ነዉ?


Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....




"ዩክሬንና ባለስልጣናቱ የእጃቸውን ያገኛሉ"-ሩሲያ

ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ከረዳታቸው ጋር መገደላቸውን ተከትሎ ሩሲያ በዩክሬን አገዛዝ እና ባለስልጣናት ላይ ከባድ የበቀል ዱላ እንደምታሳርፍ ዝታለች፡፡

የአገሪቱ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬድቭ ለጄነራሉ ሞት የዩክሬን ባለስልጣናት በቅርቡ ዋጋቸዉን ያገኛሉ ማለታቸውን የሩሲያው ታስ ዘግቧል፡፡

ዲሚትሪ ሜድቬድቭ የበቀል ጥቃቱ ከፍተኛ የዩክሬን ባለስልጣናትንና ወታደራዊ ኃላፊዎችን ጭምር ኢላማ እንደሚያደርግም ነው የዛቱት፡፡

ጀነራሉ የተገደሉት በዩክሬን ልዩ ዘመቻ ነው የተባለ ሲሆን የዩክሬን የደህንነት ተቋም ኤስቢዩ ጀነራሉ የተገደሉበትን ዘመቻ መምራቱን ሬውተርስ ዘግቧል።

የሩሲያ የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭኢጎር እና ረዳታቸው ከክሬምሊን በስተደቡብ ምስራቅ 7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው በመኖሪያ ቤታቸው መግቢያ ላይ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ በተጠመደና ቤት ውስጥ በተሰራ ቦንብ ዛሬ ማለዳ ላይ መገደላቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡


ወደ ኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች መግባት እንዲችሉ የሚፈቅደው አዋጅ ፀድቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ ዛሬ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።


Репост из: Crypto news
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
📈 Set. Forget. Earn—Even While You Sleep.

💥 maxAPY automates your yield strategy to constantly secure the highest APYs in DeFi. While others move funds manually, you relax.

🚀 Why maxAPY?
✅ Currently at 21% APY—auto-optimized daily.
✅ Zero manual effort: your deposits move where the APY’s best, 24/7.
✅ Trusted by thousands of DeFi users who’ve stopped chasing and started growing.

🌙 Imagine this: While you sleep, while you work, while you do anything else—your money keeps moving and growing.

👇 Start earning now—hands-free.
👉 https://tglink.io/0873c2b7222a

maxAPY: Where automation meets the max returns.


በሕገ-ወጥ መንገድ 6 ሺህ 200 ግራም ወርቅ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሕገ-ወጥ መንገድ 6 ሺህ 200 ግራም (6 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም) ወርቅ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም በሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የውስጥ ክፍል 6 ሺህ 200 ግራም ወርቅ በመደበቅ ለማሳለፍ ሲሞክሩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች ጋር ባደረጉት ክትትል ተጠርጣዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ገብረ ስላሴ ዮሐንስ እና ዓለማየሁ ሰማሞ የተባሉ ሾፌር እና ረዳት ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል::


ጄኔራሉ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ጨምሮ ከአደገኛ ፈንጂዎች ጋር በተዛመደ በሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ውስጥ በተለያዩ ሚናዎች አገልግለዋል። በትላንትናው ዕለት የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ዩክሬን ውስጥ የተከለከለ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ሲል ጄኔራል ኢጎርን ከሶ ነበር፡፡የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት በኪሪሎቭ መሪነት ሩሲያ 5 ሺሕ ያህል የኬሚካላዊ መሳሪያዎችን ተጠቅማለች ሲል ተናግሯል።

ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር "በዩክሬን በሩሲያ ጦርነት ላይ አውዳሚ ኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ተጠቅመዋል" በሚል በብሪታኒያ፣ ካናዳ እንዲሁም በሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ማዕቀብ ተጥሎባቸው ቆይቷል።


በሞስኮ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሩሲያ የኒውክሌር ኃይል አዛዥ ተገደሉ

ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ አንድ አፓርትመንት ሕንፃ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፤ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ከረዳታቸው ጋር መገደላቸው ተገልጿል፡፡

ኢጎር እና ረዳታቸው የተገደሉት ከክሬምሊን በስተደቡብ ምስራቅ 7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው የመኖሪያ አፓርትመንታቸው ውጭ በደረሰ ፍንዳታ ነው ተብሏል።

ጄነራሉ የተገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው መግቢያ ላይ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ በተጠመደና ቤት ውስጥ የተሰራ ቦንብ መሆኑን በሩሲያ መንግሥት የሚተዳደረው ታስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር፤ በኮስትሮማ ከፍተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የኬሚካል መከላከያ ትምህርት ቤት ወታደራዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ከፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 ጀምሮ የጦር ኃይሉን እንዲመሩ ተሹመዋል።


በአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የፀደቀው ሕግ "የዩናይትድ ስቴትስን ብሔራዊ ደኅንነት በውጭ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ካሉ መተግበሪያዎች ለመጠበቅ" የወጣ ነው ይላል። ቲክቶክ ከታገደ ፌስቡክ ይበለፅጋል ይላሉ። ፌስቡክ በ2020 ምርጫ ለመሸነፋቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ ነው ትራምፕ የሚያምኑት።

ኩባንያው ቲክቶክን አሜሪካ ውስጥ ካሉ "እጅግ አስፈላጊ የንግግር መድረኮች" አንዱ ነው ያለው ሲሆን ይህንን ማገድ ለኩባንያውም ሆነ ለተጠቃሚዎቹ "ትልቅ ጉዳት" መሆኑን ተናግሯል።ትራምፕ ሰኞ ዕለት በነበራቸው አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ አስተዳደራቸው "ቲክቶክ እንደሚያጤነው" ተናግረዋል።

"እኔ ለቲክቶክ የተሻለ ቦታ አለኝ። ምክንያቱ 34 በመቶ ወጣቶች ድምፃቸውን ለኔ ሰጥተዋል" ብለዋል። "አንዳንድ ሰዎች [ለማሸነፌ] ቲክቶክ ትልቅ አስተዋፅፆ ነበረው ይላሉ። ቲክቶክ ትልቅ ተፅዕኖ አለው።"

ምንጭ ቢቢሲ


ቲክቶክ በአሜሪካ የሚታገድበት ቀን መቅረቡን ተከትሎ ትራምፕ ዋና ሥራ አስኪያጁን ሊያናግሩት ነው!

የግዙፉ ማኅበራዊ ሚድያ ቲክቶክ ሥራ አስኪያጅ ሹ ዚ ቺው ሰኞ ዕለት ትራምፕን በማራላጎ ያገኛቸዋል ተብሎ ተጠብቆ እንደነበር የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

እየተገባደደ ባለው የአውሮፓውያኑ መባቻ የወጣው ሕግ ቲክቶክ ካልተሸጠ በሚመጣው ጥር አሜሪካ ውስጥ ጥቅም እንዳይውል ይታገዳል ይላል።
የቲክቶክ ባለቤት ቻይናዊው ባይትዳንስ የተባለ ኩባንያ ነው። ኩባንያው ለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባስገባው ይግባኝ ዕገዳው እንዲዘገይ ጠይቋል። አሜሪካ ቲክቶክን ለማገድ የወሰነችው ባይትዳንስ ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት አለው በሚል ምክንያት ነው። ቲክቶክም ሆነ ባይትዳንስ ግን ይህንን ውንጀላ ያስተባብሉታል።


‘" የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው "  ያሉት አባገዳዎቹ ይህም በምክክሩ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡

የምክክሩ ተሳታፊዎች የወከሉት የኦሮሞ ህዝብ ተቆራርጠው የቀሩት ፦
- የመሬት ጥያቄዎች፣
; የወሰን ጥያቄዎች እንዲፈቱ አጀንዳ ሆነው እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

አፋን ኦሮሞ ቋንቋም የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን አባ ገዳዎቹ ለተሳታፊዎቹ " አጀንዳ " አድርጋችሁ አቅርቡ ብለዋቸዋል፡፡

አባ ገዳዎቹ የኦሮሞ ህዝብ መልስ እንዲያገኝ ጠይቁ ባሉበት ወቅት፤ በምክክር ሂደት ላይ ለመሳተፍ በስታዲየም የተገኙት ሰዎች በጭብጨባና በፉጨት ድጋፋቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡

በዛሬ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በተጀመረው የምክክር ምዕራፍ ከ356 ከክልሉ ወረዳዎች የተወከሉ ከ7,000  በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወክለዋል፡፡

መረጃው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ የተወሰደ ነው።


" ኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ የሆኑት የቋንቋ፣ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለ ፤ የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው "  - አባገዳዎቹ

የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ እንዲያገኝለት አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ አባገዳዎች ጠየቁ፡፡

አባ ገዳዎች ይህን የጠየቁት ዛሬ በአዳማ ከተማ የ ሀገራዊ ምክክር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ነው፡፡፡

አባ ገዳዎቹ " የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች አንድም እንዳይዘነጉ " ሲሉ ለምክክሩ ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡

" በምክክሩ የኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ ናቸው የተባሉት ፦
➡️ የቋንቋ፣
➡️ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለን " ብለዋል፡፡


Репост из: ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ትላንት የተደረጉ ጨዋታዎች !

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿በርንማውዝ 1:1 ዌስትሃም 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

🇮🇹በጣልያን ሴሪ ኤ

🇮🇹ላዚዮ 0:6 ኢንተር 🇮🇹

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


ጅማ📍
በጅማ ከተማ የሚካሄደውን የመንገድ ኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባረፉበት አንድ ሆቴል ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ጅማ ከተማ የሚካሄደውን የመንገድ ኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባረፉበት አንድ ሆቴል ላይ ትላንት ወድያ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ የቦምብ ጥቃት እንደተፈጸመ ዋዜማ ባካባቢው ካሉ ምንጮቿ ሰምታለች።

የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው፣ በከተማው በተለምዶ መርካቶ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ወደ ስታዲዮም በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ እንደኾነ ዋዜማ ተረድታለች።

በጥቃቱ በሰዎች እና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር ዋዜማ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻለችም።

የቦምብ ፍንዳታው በተከሰተበት ወቅት ባካባቢው ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች የገለጹ ሲኾን፣ ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው ግን ለጊዜው ማወቅ እንዳልቻሉ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ኾኖም ፖሊስ ከጥቃቱ በኋላ ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን በርካታ ሰዎች ማሠሩን ዋዜማ ሰምታለች።


‘" የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው "  ያሉት አባገዳዎቹ ይህም በምክክሩ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡

የምክክሩ ተሳታፊዎች የወከሉት የኦሮሞ ህዝብ ተቆራርጠው የቀሩት ፦
- የመሬት ጥያቄዎች፣
; የወሰን ጥያቄዎች እንዲፈቱ አጀንዳ ሆነው እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

አፋን ኦሮሞ ቋንቋም የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን አባ ገዳዎቹ ለተሳታፊዎቹ " አጀንዳ " አድርጋችሁ አቅርቡ ብለዋቸዋል፡፡

አባ ገዳዎቹ የኦሮሞ ህዝብ መልስ እንዲያገኝ ጠይቁ ባሉበት ወቅት፤ በምክክር ሂደት ላይ ለመሳተፍ በስታዲየም የተገኙት ሰዎች በጭብጨባና በፉጨት ድጋፋቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡

በዛሬ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በተጀመረው የምክክር ምዕራፍ ከ356 ከክልሉ ወረዳዎች የተወከሉ ከ7,000  በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወክለዋል፡፡

መረጃው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ የተወሰደ ነው።


" ኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ የሆኑት የቋንቋ፣ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለ ፤ የአዲስ አበባ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ነው "  - አባገዳዎቹ

የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ እንዲያገኝለት አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ አባገዳዎች ጠየቁ፡፡

አባ ገዳዎች ይህን የጠየቁት ዛሬ በአዳማ ከተማ የ ሀገራዊ ምክክር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ነው፡፡፡

አባ ገዳዎቹ " የኦሮሞ ህዝብ ለ150 ዓመታት ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች አንድም እንዳይዘነጉ " ሲሉ ለምክክሩ ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡

" በምክክሩ የኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ ናቸው የተባሉት ፦
➡️ የቋንቋ፣
➡️ የወሰን ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለን " ብለዋል፡፡


በምስራቅ ቦረና ዞን የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ ነው

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን የቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የኦነግ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ ነው።

በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦነግ ታጣቂዎች ለቀረበው የሰላም ጥሪ ምላሽ በመስጠት ወደ ካምፕ በመግባት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ታጣቂዎቹ በነጌሌ ቦረና ከተማ አቀባበል እንደተደረገላቸውም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

በኦሮሚያ ክልል መንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡


ጅማ📍
በጅማ ከተማ የሚካሄደውን የመንገድ ኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባረፉበት አንድ ሆቴል ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ጅማ ከተማ የሚካሄደውን የመንገድ ኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባረፉበት አንድ ሆቴል ላይ ትላንት ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ የቦምብ ጥቃት እንደተፈጸመ ዋዜማ ባካባቢው ካሉ ምንጮቿ ሰምታለች።

የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው፣ በከተማው በተለምዶ መርካቶ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ወደ ስታዲዮም በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ እንደኾነ ዋዜማ ተረድታለች።

በጥቃቱ በሰዎች እና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር ዋዜማ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻለችም።

የቦምብ ፍንዳታው በተከሰተበት ወቅት ባካባቢው ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች የገለጹ ሲኾን፣ ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው ግን ለጊዜው ማወቅ እንዳልቻሉ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ኾኖም ፖሊስ ከጥቃቱ በኋላ ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን በርካታ ሰዎች ማሠሩን ዋዜማ ሰምታለች።


ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ ጋር ተወያዩ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ ጀነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ጋር ዛሬ ማለዳ ተገናኝተው መመምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Показано 20 последних публикаций.