እስራዔል በፈጸመችው የአየር ጥቃት የናባቲዬ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ 6 ሰዎች ተገደሉ
የናባቲዬ ከተማ ከንቲባ የተገደለው ከሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ቡድን ጋር በማዘጋጃ ቤት ህንጻ ውስጥ ውይይት በማድረግ ላይ እያሉ እንደሆነ ተገልጿል።
የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነጂብ አዝሚ ሚካቲ እስራኤል ሆነ ብላ በማዘጋጃ ቤቱ ላይ እርምጃ መውሰዷን ጠቅሰው ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡
እስራኤል በበኩሏ ጥቃቱን የፈጸመችው ሂዝቦላህ በምድር ስር ያከማቻቸው የጦር መሳሪያዎችን ኢላማ በማድረግ እንደሆነ ገልጻለች።
በሌላ በኩል አሜሪካ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ እስራኤል እንድትፈቅድ በመጠየቅ የምታደርገው ወታደራዊ ድጋፎችም ይህንኑ ቅድመ ሁኔታ ያማከለ እንደሆነ ጠቁማለች፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ፤ ከዮርዳኖስ መንግስት የተላኩ 50 የጭነት መኪናዎች ምግብ፣ ውሃ፣ የህክምና ቁሳቁሶች እና ጊዜያዊ መጠለያን በመያዝ ሰሜን ጋዛ መድረሳቸውን አስታውቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡