በሞስኮ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሩሲያ የኒውክሌር ኃይል አዛዥ ተገደሉ
ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ አንድ አፓርትመንት ሕንፃ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፤ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ከረዳታቸው ጋር መገደላቸው ተገልጿል፡፡
ኢጎር እና ረዳታቸው የተገደሉት ከክሬምሊን በስተደቡብ ምስራቅ 7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው የመኖሪያ አፓርትመንታቸው ውጭ በደረሰ ፍንዳታ ነው ተብሏል።
ጄነራሉ የተገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው መግቢያ ላይ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ በተጠመደና ቤት ውስጥ የተሰራ ቦንብ መሆኑን በሩሲያ መንግሥት የሚተዳደረው ታስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር፤ በኮስትሮማ ከፍተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የኬሚካል መከላከያ ትምህርት ቤት ወታደራዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ከፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 ጀምሮ የጦር ኃይሉን እንዲመሩ ተሹመዋል።