Ethio Construction


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


አንድን ጨረታ የሚያሸንፈው ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ ተጫራች ወይስ ከመሐንዲሱ ግምት ተቀራራቢ የሆነ ዋጋ ያስገባ ተጫራች?

💫ጨረታ ለተቋራጮች በሁለት አይነት መንገድ ሊፈጸም ይችላል:-

⭐️አንደኛ[1ኛ:- ግልጽ ጨረታ ሲሆን ማንኛውም ብቁ የሆነ፣ ህጋዊ ፍቃድ ያለው እና ፍላጎት ያለው ተቋራጭ መሳተፍ የሚችልበት በጋዜጣ ወይም በአካባቢው ባሉ የማታወቂያ መንገዶች ወይም በማህበራዊ መገናኛ ድረገጾች (website) ላይ በሚለቀቅ የተጫራችነት ግብዣ ጥሪ (Invitation to Tender) አማካኝነት ተጫራቾች ኩል ዕድል ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ የሚጋበዙበት ሂደት ሲሆን

⭐️ሁለተኛው[2ኛ:- ውስን ጨረታ የሚባል ነው። ውስን ጨረታ አንድ ተጋባዥ ወይም ውስን ቁጥር ያላቸው ልዩ መስፈርት የተሰጣቸው ተጫራቾች ጋር በሚደረግ ድርድር ወይም የመለያ ጨረታ አማካኝነት የሚከናወን የጨረታ አይነት ነው።



📄በግልጽ ጨረታ ሂደት ደግሞ አጫራቹ አካል ሁለት አይነት መንገድን ሊጠቀም ይችላል:-

🏷[አንደኛው] ፖስት ኳሊፊኬሽን (Post Qualification) የሚባል ሲሆን ሥራው ቀለል ያለ እና ማንኛውም ተጫራች ሊያከናውነው የሚችል ከሆነ ቅድሚያ ኢኮኖሚያው (የገንዘብ) መጠናቸውን መመዘን ነው።

በዚህ ሂደት ቅድሚያ ቅንሽ ዋጋ ያስገቡ ተጫራቾች ተለይተው እነዚያ ደግሞ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ነው።

🏷[ሁለተኛው] ፕረ ኳሊፊኬሽን (Pre-Qualification) የሚባለው ደግሞ ማንኛውም ተጫራች ቅድሚያ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው በኋላ በገንዘብ ዝቅተኛ ያስገባው አሸናፊ የሚሆንበት የጨረታ ምዘና መንገድ ነው።

በመሆኑ ይህ ሂደት በፌደራል የግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የወጣው መመሪያ ክፍል አምስት (5) ንዑስ ክፍል (1), (2) እና (3) ላይ በዝርዝር የተብራራ ነው።

🚧በመሆኑም በጨረታ ሰነዶች ምዘና (Bid Response Document Evaluation) ሂደት ላይ ተጫራቾት እንደጨረታ ሰነዱ አወጣጥ ተመስርቶ በቅድሚያ ዝቅተኛ ዋጋ ያስገቡትን በመምረጥ (Post Qualification ሂደትን በመከተል) በቴክኒካል ሰነዳቸው አXእናፊውን የሚለይበትን መንገድ ሊከተል ይችላል።

አልያም ደግሞ Pre-Qualification ሂደትን በመከተል ቅድሚያ የቴክኒካል ሰነዳቸው ታይቶ ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ብቻ ተለይተው ዝቅተኛ ገንዘብ ባስገባ (Lowest bidder) የሚለዩበት መንገድ ነው።


ይህ ሁለቱም መንገድ በግል ፕሮጀክቶችም ይሁን በመንግሥት ፕሮጀችቶች ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉና ህጋዊ እውቅና ያላቸው መንገዶች ናቸው።

ጨረታውን አከፋፈት በተመለከተ በ ክፍል 2 (2.2.1.5) ላይ እንደተብራራው ቃለጉባኤ ተይዞ፣ የጨረታውን አከፋፈት ሂደት ላይ ውይይት ከተካሄደባቸው ጉዳዮች በተጨማሪ ጨረታው ሲከፍተ የተገኙ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው ስለጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚያብራራ ቃለጉባኤ ላይ ስማቸውን እና ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይገባቸዋል።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመሐንዲስን ግምት ያማከለ የጨረታ ሰነዶች ምዘና የሚካሄድበት አጋጣሚ አለ።

ይህም Federation Internationale Des Ingenieurs Conseil – FIDIC አንቀጽ 14 ላይ እንደተገለጸው ተጫራቾች መሐንዲሱ ገምቶ ያስቀመጠውን የግንባታ ዋጋ (Engineering Estimation of Construction Cost) እንደመነሻ በመቁጠር ተጫራቾች ከግምቱ በታች ከ20% በታችን የቀነሰ ዋጋ እንዳያስገቡ ወይም ከግምቱ በላይ ከ20% በላይ እንዳይጨምሩ ገደብ በማስቀመጥ ከዚህ እሳቤ ውጪ የሆኑትን የተጫራቾች ሰነዶች በመጣል በዚህ ክፍተተ (interval) ውስጥ ያሉትን ብቻ የማወዳደር ሥራ የሚሰሩበት መንገድ ነው።

ቢሆንም ግን ይህ አካሄድ ግምቱን ባወጣው መሐንዲስ (ግለሰብ) ጥንቃቄ እና እውቀት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ብዙ ክፍተቶች የሚፈጠሩበት ቢሆንም  የፌደራል መንግስት የግዢ መመሪያ ቀድሞ በነበረው በዚህ አሰራር ላይ ግልጽ ማብራሪያ ሳያስቀምጥ አልፎታል።

መልካም ቀን! 🤚

https://t.me/ethioengineers1


ቀለም እና ህንጻ

💫After Image Effect

🚧በአረንጓዴ አካባቢ የሚሰሩ ሕንፃዎችን በዋናነት ቀይ ቀለም መቀባትን "After image effect" ተብሎ የሚጠራው የቀለም ሳይንስ መርህ ይፈቅዳል።

⭐️ዓይናችን ለረዥም ጊዜ አረንጓዴ ቀለምን ከተመለከተ አንጎላችን ሚዛናዊነትን (የቀለም ዲሞክራሲ እንበለው) ለመጠበቅ ተቃራኒው የሆነውን (Complementary) ቀይ ቀለምን መጠየቅ ይጀምራል።

⏺በዚህም ሂደት ሁሉም መስራች የቀለም ዓይነቶች በ"Color field" ይገኛሉ ማለት ነው፤ አረንጓዴ ውስጥ ቢጫና ሰማያዊ ቀለማት አሉ፤ በዚህ ላይ ቀይ ሲጨመር መሠረታዊ ቀለሞች በሙሉ ተገኙ ማለት ነው።

❇️አንጎላችን ቀለማትን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ነው የሚያስተናግደው።

🔰ከላይ ያለው ምስል የ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ነው።

Via Nita Color Centre


https://t.me/ethioengineers1


ረቂቅ አዋጁ ፀደቀ‼

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ዛሬ በምክር ቤት የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የሪል ስቴት አልሚ ድርጅት ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ እንደማይችል አስቀምጧል።

በተጨማሪ በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር እንደማይችልም አስቀምጧል።

የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

👉 የሪል ስቴት አልሚ የቦታና የተናጠል ይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን በተመለከተ ፦

1) በከተሞች ለሪል ስቴት ልማት የሚውል ቦታ በሚከተለው አግባብ የሚቀርብ ይሆናል፤

ሀ. በአዲስ አበባ ከ5 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፤
ለ. እንደከተሞች ተጨባጭ የቤት ፍላጎትና ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት አካባቢ ባለ ከተሞች ከ1 ሺህ በላይ ቤት የሚገነባና የሚያስተላልፍ ወይም፣
ሐ. ከነዚህ ባነሰ ስፋት ቤት ለሚፈልጉ ከተሞች ደግሞ 500 ቤት በላይ የሚገነባና የሚያስተላልፍ የሪል ስቴት አልሚ መሬት ቅድሚያ ተሰጥቶት በስፋት እንዲቀርብለት ይደረጋል።

2) የሪል ስቴት አልሚው የገነባውን ቤት በተናጠል ለቤት ፈላጊ በሽያጭ ለማስተላለፍ ግንባታው የተፈቀደለትን መስፈርት አሟልቶ 80 በመቶ ሲጠናቀቅ ለየቤቱ የተናጠል የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፤

👉 የሪል ስቴት አልሚ ግዴታዎች ምንድናቸው ?

የሪልስቴት አልሚ በውል ሰነዱ በህንጻ እዋጁ እና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች የተመላከቱ ግዴታዎችን ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪነት የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል ፡-

1) ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡

2) በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል የውሸት ማስታወቂያ ማስነገር አይችልም፡፡

3) ቤቶቹን ለመገንባት የሚያስችለውን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ከመረከቡ በፊት ደንበኞችን መመዝገብና ቅድመ ክፍያዎችን መሰብሰብ አይችልም፡፡

4) በሕጋዊ መንገድ የተረከበው መሬት ሊያስተናግድ ከሚችለዉ የቤት ደንበኛ በላይ መመዝገብ አይችልም።

5) የመኖሪያ ቤት ገዢ ደንበኞች ማኀበር እንዲያቋቋም ያበረታታል ፤ የህንጻ መግለጫ ያስረክባል።

6) ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ፣ የቤቱ የግንባታ ዕቃዎች ዓይነት፣ አርክቴክቸራል፤ ሳኒተሪ ፣ ስትራክቸራል እና ኤሌክትሪካል ዲዛይን፤ የግንባታ ፍቃድና የሪል ስቴት ልማት ፍቃዱን ቅጂዎች ከውል ሰነዱ ጋር አያይዞ ለደንበኛው መስጠት አለበት።

7) ደንበኛው ለከፈለው ገንዘብ ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት አለበት።

👉 ዋስትና ስለመስጠት ፦

የአገር ውስጥ አልሚ ቤቱን ሳይገነባ ለቤት ፈላጊዎች በቅድሚያ በሚሽጥበት ወቅት የሚከተሉትን የዋስትና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

1) የሪል ስቴት አልሚው በቤት ቅድሚያ ሽያጭ ስልት ለመስራት መፈለጉን አግባብ ላለው አካለ አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት፡፡

2) ከቤት ገዥዎች የሚሰበስበውን ገንዘብ አግባብ ካለው አካለ ፈቃድ መሰረት በሚከፈተው የዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማደረግ ወይም ማስያዝ፣

3) የሪል ስቴት አልሚው በቅድሚያ መሽጥ የሚፈልገውን ቤት የመስሪያ ቦታ የይዞታ ማስረጃ ቤቱ ለተጠቃሚዎች ተገንብቶ እስከሚተላለፍ ድረስ በሚመለከተው አካል እንዳይሽጥ እንዳይለወጥ እንዲታገድ ማድረግ፤
📌 በዝግ የባንክ ሂሳብ ገቢ የተደረገው ገንዘብ የሚለቀቅበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡
አዋጁ ከላይ በ PDF ተቀምጧል።


https://t.me/ethioengineers1




የሲሚንቶ ዋጋ‼️

የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ‼️

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ  ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ  እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል፡፡


https://t.me/ethioengineers1


የአርማታ ሙሌታ (Concrete Compaction) ቁጥጥር

1. የግብአት ጥራትን (Materials Quality)፦ በአርማታ ሙሌት ሥራ ሂደት ውስጥ የሚጠቀማቸውን የማምረቻ ግብአቶች ጥራት በተገለጸው መስፈርት መሰረት የሚያሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

ይህ ማለት የቀረበው ሲሚንቶ (Cement) አይነትና የምርጥ ጥራት፣ የአሸዋ (sand or Fine aggregate) እና ጠጠር (Coarse Aggregate)ሳይንሳዊ ምዘናን ማሟላቱን፣ የማቅጠኛ ውሀ (Water) የኮንክሬት ስትራክቸሩን ሊጎዳ የሚችል ኬሚካልና ቆሻሻ የሌለው የጠራ ውሃ መሆኑን እና ሌሎች ተጨማሪ ኬሚካል (Admixture) መለያ አይነት የተሟላ መሆኑን ሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ ተደግፎ የማረጋገጥ ሂደትን መተግበር ማለት ነው።

በዚህ ረገድ የግብአት መሐንዲሱ (Materials Engineer) ለሳይቱ በቀረበው የቤተሙከራ ክፍል ውስጥ በመስራት የማረጋገጥ አልያም በቅርቡ በሚገኝ የቤተሙከራ አገልግሎት ሰጪ ተቋማ በማሰራት የግብአቶችን ጸባይ የመለየትና ማረጋገጫ የመስጠት ግዴታ ይኖርበታል።

2. የግብአቶችን ልኬት (Batching of materials):- በተለይ በሀገራችን የግንባታ ልምድ ኮንክሬት በሚመረትበት ሰዓት ያለው የአሸዋ፣ የጠጠር እና የውሃ ልኬት ለችግር የተጋለጠ ነው።

አንድ 1፡2፡3 ምጥጥንን መሰረት አድርጎ ዲዛይን የተሰራ አርማታ አንድ እጅ ሲሚንቶ፣ ሁለት እጅ አሸዋ፣ ሦስት እጅ ጠጠር መጠቀም አለበት ማለት ቢሆንም የመቀላቀያ ማሽኑ ተቆጣጣሪ (Mixer Operator) ይህንን ምጥጥን ጠብቆ አምራታ የማምረት ልምድ ቸልተኝነት የተሞላበት እንደሆነ ይስተዋላል።

ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በምጥጥን (Proportion) መሰረት እየተመረት መሆኑን መቆጣጠር የግድ ነው።

3. የማሽን እና መሳሪያ ደህንነት (Equipments Security):- የኮንክሬት ድብልቅ ማምረቻ ማሽኖች (mixers) ደህንነታቸው የተረጋገጠ ወይም በአግባቡ የሚሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የኮንክሬት ግብአቶችን መለኪያ ሳጥኖችን (box) ርዝመት ወርድ እና ቀመት (L, W, H) አግባብነት ያለው መሆኑን (ለምሳሌ፦ 18*40*50)፣ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ብሎም የካሳ ሙግትና የሥራ ማቆም መሰናክል እንዳይፈጠር የሰራተኞች ደህንነት መጠበቂያ አልባሳት የተሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

4. በአግባቡ መጠቅጠቁን፦ የሚሞላው አርማታ በተለይ ምሰሶ (column) እና የምሰሶ ጫማ (Footing Pad) በክፍልፋይ ላየሮች  ከፋፍሎ እያንዳንዱ የላየር ክፍል ጫፍ ላይ ሲደርስ በኤሌክትሪክ መንዘሪያ (Vibrator) በደንብ መጠቅጠቅ መቻል አለበት።

የአርማታ መጠቅጠቅ እያንዳንዱ የግንባታ ግብአት በአግባቡ የተሰራጨ እንዲሆን እና የቀጠነው አርማታ ወደታች ወርዶ ጠጠራማው ወደላይ እንዳይቀር በማድረግ የትኛውም የስትራክቸር ክፍል ተመሳሳይ አይነት ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርጋል።

5. የአርማታ ድርቀት እንዳይኖር መቆጣጠር፦ የአርማታ ሙሌት ሂደት ላይ አዲስ የተመረተ አርማታ አላስፈላጊ ደቂቃዎችን ሳይሞላ መቆየት የለበትም።

አርማታ ሳይሞላ ከሚክሰር እንደተገለበጠ የሚቆይ ከሆነ በፎርምወርክ ውስጥ ሆኖ መያዝ ያለበትን የመጀመሪያ ጥንካሬ (Initial Setting) መያዝ ስለሚጀምር ከዚያ በኋላ ሙሌትን ለማከናወን አዳጋች ከመሆኑም በላይ የሚፈለገውን የኮንክሬት ስትራክቸር ጥንካሬ ለማግኘት አዳጋች ይሆናል።

6. የድኅረ ሙሌት ቁጥጥር፦ አርማታ ከተሞላ በኋላ በሳይንስ የተቀመጡ የፎርምወርቅ ማስወገጃ ቀናቶችን (Formwork Removal time) ጠብቆ እንዲፈርስ ማድረግ (በተለይ በቀዝቃዛማ እና ዝናባማ አካባቢዎች)፣ የተሞላው አርማታ በአግባቡ ውሃ እየጠጣ (curing) መሆኑን መከታተል እና የሚቀጥሉ የኮንክሬት ስትራክቸሮች ካሉ የተሞላው አርማታ በቂ ጥንካሬ ካገኘ በኋላ ሥራቸው የሚጀምር መሆኑን መከታተል አለበት።

https://t.me/ethioengineers1


ይህ የ40/60 ህንፃ ቦሌ አያት 2 ብሎክ 38 ይባላል

ዕጣ ከወጣበት ሁለት አመት ሊሞላው ሲሆን ባለ 13 ፎቁ "ህንፃ" በሚያሳፍር እና አደገኛ በሆነ ሁኔታ ተሰርቶ ቆሟል። እስካሁን ከ8ኛ በላይ ያለው የውስጥ ለውስጥ partition የሌለው፣ መወጣጫ ደረጃው ያላለቀ፣ የውስጥ ልስን የሌለው እና ጣራው ያልተመታ ነው።

ህንፃው ውስጥ ሰው ገብቶ አስከፊ አደጋ ሳያደርስ በፍጥነት መፍትሄ ያስፈልገዋል።


Via :- EliasMeseret

https://t.me/ethioengineers1


#ሲሚንቶ

" ከዛሬ ጀምሮ በሚኒስትር መ/ቤቱ በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ሥራ ቀርቷል " - ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል።

በዚህም ወቅት " ከዚህ ቀደም በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ሥራ ከዛሬ ጀምሮ ቀርቷል " ብለዋል።

አምራቾች በራሳቸዉ ኃላፊነት በሚመርጧቸዉ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች በኩል ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

የሲሚንቶ ገበያዉን ለማረጋጋት ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ያሉ ሲሆን የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማያቀርቡ በማናቸዉም የሲሚንቶ አምራች ላይ " የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሚኒስትሩ " አዲሱን ዉሳኔና አቅጣጫ ተከትሎ በግብይት ሰንሰለቱ የደላላ ጣልቃ ገብነት የከሰመ፣ ለመንግስት ፕሮጀክቶችና ለተጠቃሚዉ ህብረተሰብ አስተማማኝ የሲሚንቶ አቅርቦት የተረጋገጠ፣ አምራቾችም ተገቢዉን ትርፍ እያገኙ የከምፓኒዎቻቸዉን ዘላቂ ዕድገት የሚያስቀጥሉበት እንዲሆን " ብለዋል።

የግብይት ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ከካሽ ክፍያ ነጻ ሆኖ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እንዲፈጸም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በውይይት መድረኩ ወቅት አምራቾች የምርት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ተብሏል።

ሲሚንቶ አምራቾች አዲሱን ውሳኔ በማክበር እንደሚተገብሩ ተናግረው ነገር ግን የማምረቻ ግብዓት ፣ የኃይል አቅርቦትና ተያያዥ ችግሮች እንዲፈቱላቸዉ ጠይቀዋል፡፡


https://t.me/ethioengineers1


የግንባታ ቦታን ማስረከብ

⚡️የግንባታ ባለቤት (Client) ለግንባታ ሥራ መሰናክል ከሆኑ ነገሮች (ለምሳሌ፦ የካሳ ጥያቄ ከሚያነሱ ሰዎች ቁጥጥር፣ ከመብራት፣ ከውሃ፣ ከቴሌ ግንባታዎችና መሣሪያዎች) በማጽዳት ወይም ነጻ በማድረግ ዝግጁ የሆነ የግንባታ ቦታን ለሥራ ተቋራጩ (Contractor) የማስረከብ ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት።

⚡️ባለቤቱ የግንባታ ቦታውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ካላስረከበ የግንባታ ማስረከቢያ ጊዜ መራዘም/መዘግየት/ ላይ ለሚያስከትለው ኪሳራ ወይም ወጪ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የሕንጻ ግንባታ ደንቦች (Standard Building Contract with quantities) በአንቀጽ 2.4 እና 2.24 ስር የሰፈረ ድንጋጌ ነው።


https://t.me/ethioengineers1


የሕንፃ አዋጁን መሻር ለምን አስፈለገ?

አዋጅ አይሻርም፤ ይሻሻላል እንጂ። በርግጥ ሊደረግ የታሰበው  ግን ከመሻር ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ረቂቁ የባለሞያውን  ማለትም የአርኪቴክቱን ፡ የኢንጂነሩን ድርሻና ኃላፊነት እንዲቀርፅ ተደርጎ የተዘጋጀን አዋጅ ለድርጅት አሳልፎ ለመስጠት የተቀረፀ ረቂቅ ነው።

አንድ ቀላል ማሳያ እንመልከት። አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ (ቁጥር 624
/2001) አንቀፅ 26 ምን ይላል?

26 የተመዘገቡ ባለሞያዎችን ስለመቅጠር 

ለማንኛዉም ህንፃ ህንፃው ለሚገኝበት ምድብ የሚጠየቁ የዲዛይን አይነቶች ለየስራው በሚመጥኑ የተመዘገቡ ባለሞያዎች መሰራት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡ የሕንፃዉ ግ ንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስም የባለሞያዎቹ ቁጥጥር ሊኖር ይገባል፡፡ የሕንፃ ዲዛይኑን ቴክኒካል ስራ የሚያስተባብረው አርኪቴክቱ ይሆናል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ አዲሱ ማሻሻያ ረቂቅ በለሞያ የሚለውን በቀጥታ በድርጅት በመተካት አንዴት እንደተለወጠ እንመልከት:

19. የተመዘገበ አማካሪ ድርጅት ስለመቅጠር፡ 
ለማንኛውም ህንፃ ህንፃው በሚገኝበት ምድብ የሚጠየቁ የዲዛይን ዓይነቶች ለግንባታው በሚመጥን በተመዘገበ አማካሪ ድርጅት መሠራት አለበት፡፡ የህንፃ ዲዛይኑን ቴክኒካል ሥራ የሚያስተባብረው የዲዛይን ባለሙያ የምስክር ወረቀት ያለው ወይም አርክቴክቱ ነው፡፡ ዝርዝሩ ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡ የህንፃው ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ የቁጥጥር ስራውን የሚያከናውነው አማካሪ ድርጅት የሥራ ተቋራጩን የግንባታ ባለሙያዎችንም ይቆጣጠራል፡፡ የግንባታ ሥራው ሲጠናቀቅ አማካሪ ድርጅት የፈረመበትና መጠናቀቁን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ለተቋሙ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

አማካሪ ድርጅት በባህሪው ተለዋዋጭ የሆነ ፤ ንግድን ማእከል አድርጎ የሚቋቋም ተቋም በመሆኑ ቋሚ በሆነ ህንጻ አዋጅ ውስጥ የሚታቀፍ አይደለም፡፡

ይህ ከባለሞያ ወደ ድርጅት እንዲዞር ተደርጎ የተቀረፀ የሕንፃ አዋጅ አደጋ ምንድን ነዉ? የሕንፃ ሙያ ልክ እንደ ህክምና ፡ እንደ ህግ ባለሞያ በህግ ሊጠበቅ የሚገባ የሙያ ዘርፍ ነው። ይሄ የሚደረገው ደግሞ ባለሞያውን ለመጥቀም አይደለም። በዋነኛነት ማህበረሰቡ ተገቢውን የሙያ አገልግሎት በትክክለኛው ባለሞያ እንዲያገኝ ለማድረግ ነው።

ከተሞቻችን የተሻሉ ከተሞችና ተወዳዳሪ፣ ጤናማና ደህነነታቸው የተጠበቁ ከተሞች እንዲሆኑ ለማድረግ አዋጁ ስራው በቀጥታ ባለሞያው እንዲሰራው መደረጉን ማረጋገጥ አለበት። ዛሬ የህንፃ ፡ የከተማ ጥራት ወድቋል ብለን የምናስብ ከሆነ ይህ አዋጅ ቢፀድቅ ደግሞ ጨርሶ ይሞታል።

አለም አንድ እየሆነች ባለችበት ፤ በስራ እና በንግድ የአለም ትስስር እየጨመረ በመጣበት በዚህ ዘመን ህጎቻችን ከአለማቀፍ ህግጋት ጋር መተሰሳር አለባቸው፡፡ የአለማቀፍ የህንጻ ኮድ ክፍል 107 እንዲሚያሳየው ሃላፊነቱን የሚሰጠው ለተመዘገበ ባለሞያ ነው፡፡በሁሉም የአለም ዙሪያ ብንሄድ የምናገኘው ይህንኑ ነው፡፡  
በመሠረቱ በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ለመቀየር የሚያስፈልግ ምንም ምክንያት የለም። አዋጅ እንደ መዋቅር ነው። ቋሚ የሆነ መርህን ተከትሎ  የሚዘጋጅ ነው። መነካት አያስፈልገውም። መሻሻል የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ በደንቡ ላይ ወይም በመመሪየዎች ላይ  መካተት ይችላሉ። 

ረቂቁ በቅርቡ ለፓርላማ ቀርቦ ለከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ  መመራቱ ይታወሳል፡፡ ቋሚ ኮሚቴውም ከዚያ በኋላ የዘርፉን ባለሞያዎች ጠርቶ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የቀረቡትን ግብአቶች ለማካተት ከፍተኛ ፈቃደኝነት አሳይቷል፡፡

ይህ ማሻሻያ መሠረታዊ የመርህ መዛባት የታየበት በመሆኑ መስተካከል ይኖርበታል፡፡


https://t.me/ethioengineers1


✅🔹Bad Construction🏗

✅️Reasons for slab leaks:
Slab leaks can be caused by poor quality or damaged pipes as well as improper installation. Leaks and bursts can happen when there are bends, kinks, or poor fittings.

✅️Soil Shifts:
Many fac
tors can cause soil to shift, such as earthquakes and under construction the case of soil movement, pipes and connections bend and rub together, damaging them.

✅️Poor Water Quality:
Y
our pipes can be damaged by poor water quality, such as hard water.

https: rel='nofollow'>//t.me/ethioengineers1


✅Set back❗️❗️

አዲሱ የይዞታ አስገዳጅ የ20 ሜትር የመንገድ አዋሳኝ ስፋት እና የአነስተኛው የ500 ካ.ሜ ስፋት የማይተገበርባቸው ቦታዎች


የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች

🏷የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣ በብቃት እና ሀገሪቷ በምትጠቀምባቸው የግንባታ መሪ ሰነዶች (𝔰𝔱𝔞𝔫𝔡𝔞𝔯𝔡𝔰) መሰረት መከናወኑን የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።

ተቆጣጣሪዎች ለግንባታ ባለቤት እና ተቁቅራጭ ዋና ዋና የግንባታ ውስንነቶችን ወይም 𝔠𝔬𝔫𝔰𝔱𝔯𝔞𝔦𝔫𝔱𝔰 ተብለው የሚታወቁትን (ወጪ ገንዘብ፣ ጥራት እና ጊዜ) በአግባቡ ለመጠቀም እና ከማንኛውም ግጭት ወይም ቅሬታ ነጻ ለማድረግ የሚሰየሙ አካላት ናቸው።

⭐️ጠቅላል ሲል የሚከተሉት የሥራ ድርሻዎች አሉባቸው።

[1] የጥራት ቁጥጥር - 𝑸𝒖𝒂𝒍𝒊𝒕𝒚 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒐𝒍፦ የግንባታ ስራዎች የተቀመጡትን ደረጃዎች (𝚜𝚝𝚊𝚗𝚍𝚊𝚛𝚍𝚜) እንዲያሟሉ እና የፕሮጀክቱን የጥራት መስፈርቶች እንዲያከብሩ የስራውን ጥራት መከታተል

[2] የጊዜ አስተዳደር - 𝑻𝒊𝒎𝒆 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፦ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ (መርሐግብር) መሰረት እንዲጠናቀቅ የግንባታ ሂደቱን በየጊዜው መመዘንና መከታተል፣ መዘግየቶችን መለየት እና በፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ

[3] የሀብት አስተዳደር - 𝑹𝒆𝒔𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆 𝑴𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፡ ለተገቢ ተግባራት ተገቢውን ግብአት መመደብ፣ ትክክለኛ ሰውን ለትክክለኛው ስራ በትክክለኛው ጊዜ መመደብ፣ የቁሳቁስ እና የመሳሪያ ሃብቶችን በብቃት ማስተዳደር፣ ለተያያዥ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት

[4] ደህንነትን እና ጤናን ማረጋገጥ - 𝑰𝒏𝒔𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒔𝒂𝒇𝒆𝒕𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒉𝒆𝒂𝒍𝒕𝒉፦ በግንባታው ቦታ ላይ የደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር የደህንነት ፕሮቶኮሎችን በመከተል የመከላከያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና አደጋዎችን እና ጉዳቶችን ለመከላከል እርምጃዎች እንዲተገበሩ ማድረግ

[5] የክፍያ ልኬቶችን ማስተዳደር - 𝑪𝒉𝒆𝒄𝒌𝒊𝒏𝒈 & 𝑨𝒑𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒏𝒈 𝑾𝒐𝒓𝒌𝒔 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅፦ ተቆጣጣሪዎች በኮንትራክተሩ ለክፍያ ጥያቄ የተዘጋጁትን መጠኖች የማረጋገጥ እና ትክክለኛ መጠን ከሆኑ ማሳለፍ ወይም አስተያየት በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ማስደረግ

[6] ተከታታይ ሥራዎች በጊዜው እንዲከናወኑ ማዘዝ/መፍቀድ - 𝑶𝒓𝒅𝒆𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒐𝒓 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒆𝒅𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒂𝒔𝒌፦ በተቋራጩ አስቀድሞ የተፈጸሙ ሥራዎችን በአግባቡ የተከናወኑ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ተከታይ (ቀጣይ) ተግባራት እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት።

[7] ባለድርሻ አካላትና መገናኘት እና የሥራ ቅንጅትን መፍጠር - 𝑪𝒐𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒄𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒐𝒓𝒅𝒊𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፡-  ለፕሮጀክቱ ስኬታማ አፈፃፀም ያግዙ ዘንድ በተለያዩ የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር ግልጽ እና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደ መገናኛ/ድልድይ ማገልገል

[8] የተፈጸሙ ስራዎችን ማረጋገጥ - 𝑪𝒐𝒏𝒇𝒊𝒓𝒎𝒊𝒏𝒈 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒌𝒔፡- የተከናወኑ የሥራ ክፍሎችን ለእያንዳንዱ ሥራ ማረጋገጫ በሆኑ ተያያዥ የፍተሻ ዝርዝሮች (𝚝𝚊𝚜𝚔-𝚛𝚎𝚜𝚙𝚎𝚌𝚝𝚒𝚟𝚎 𝚌𝚑𝚎𝚌𝚔𝚕𝚒𝚜𝚝𝚜) መገምገም እና የተግባር ማረጋገጫ መስጠት /𝚌𝚘𝚗𝚏𝚒𝚛𝚖𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም ውድቅ ማድረግ /𝚛𝚎𝚓𝚎𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም የጥገና ማዘዣ መስጠት /𝚖𝚊𝚒𝚗𝚝𝚎𝚗𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም እንዲፈርሱና እና እንደገና እንዲሰሩ ማዘዝ /𝚍𝚎𝚖𝚘𝚕𝚒𝚜𝚑𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚛𝚎𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም አሳማኝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ማድረግ /𝚖𝚘𝚍𝚒𝚏𝚒𝚌𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ የመሳሰሉትን ውሳኔዎችን /𝚍𝚎𝚌𝚒𝚜𝚒𝚘𝚗𝚜/ ለኮንትራክተሩ መስጠት

[9] ችግር መፍታት - 𝑷𝒓𝒐𝒃𝒍𝒆𝒎 𝑺𝒐𝒍𝒗𝒊𝒏𝒈፦ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶችን መከላከል

[10] መረጃን ሰንዶ ማስቀመጥ -   𝑫𝒐𝒄𝒖𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፦  የእለት ሪፖርቶችን፣ የሂደት ማሻሻያዎችን፣ እና የፕሮጀክት ምእራፎችን ለመከታተል፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ እቅዶች ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦችን ጨምሮ የግንባታ ስራዎችን ትክክለኛ ክስተት ወይም አጋጣሚዎች ወይም ሂደቶች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ

[11] የአካባቢን ሁኔታ ታሳቢ ማድረግ  - 𝑬𝒏𝒗𝒊𝒓𝒐𝒏𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒍 𝑪𝒐𝒏𝒔𝒊𝒅𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒔፦  በግንባታ ተግባራት ላይ የሚኖረውን የአካባቢ ተፅእኖ ለመቀነስ እርምጃዎችን መተግበር፣ የአካባቢ ደንቦችን እና ምርጥ ልምዶችን ማክበር እና ማስከበር::


ለኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የስራ ፍቃድ አሰጣጥ መመሪያን ይመለከታል

 
https://t.me/ethioengineers1


ቤዝ አይሶሌሽን/Base isolation
የመሠረት ማግለል:-

ሕንፃዎችን ከመሬት መንቀጥቀጥ ለመከላከል በግንባታ ላይ የሚውል ዘዴ ነው።

ህንጻውን በተለዋዋጭ ማሰሪያዎች ወይም ማግለያዎች ላይ እንደ ጎማ ወይም ተንሸራታች ቁሶች በመዋቅሩ እና በመሠረቱ መካከል ማስቀመጥን ያካትታል።

እነዚህ ገለልተኞች ህንጻው የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ኃይልን በመሳብ እና በማሰራ ከመሬት ተነጥሎ እንዲንቀሳቀስ ያስችለዋል።

ይህ ዘዴ የህንፃውን የመሬት መንቀጥቀጥ የመቋቋም ችሎታን ያሻሽላል ፣ የነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና መዋቅራዊ ጉዳቶችን ለመቀነስ ፣ የመሠረት ማግለል በሴይስሚክ ክስተቶች ጊዜ ሕንፃዎችን በመጠበቅ ረገድ የተሳካ ነበር፣ ይህም ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ በሆኑ የከተማ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ ጠቃሚ ስትራቴጂ እንዲሆን አድርጎታል።

⭐️ለጠቅላላ ዕውቀት

የመሬት መንቀጥቀጥ ደረጃ ዝቅተኛው በሬክተር ስኬል 0 ሲሆን ከፍተኛው 10 ነው::ስለዚህ ትናንት ማታ ከምሽቱ 5:12 የተከሰተው 4.6 ነው።

አለማቀፍ ጂኦሎጂካል ሰርቬዮቹ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረጃን በሬክተር ስኬል እንዲሁም ሊያስከትል የሚችለውን የጉዳት መጠን እንደሚከተለው አስቀምጠውታል።

1ኛ. መጠን ከ 1.0 እስከ 3.0: ይህን ያህል አይሰማም  ግን ተመዝግቧል.

2ኛ. መጠን ከ 3.0 እስከ 3.9: ብዙ ጊዜ የሚሰማው ነው  ነገር ግን ብዙም ጉዳት የለውም

3ኛ.  ከ 4.0 እስከ 4.9 መጠን: ጉልህ የሆነ የቤት ውስጥ እቃዎች መንቀጥቀጥ;  አነስተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል.

4ኛ ከ 5.0 እስከ 5.9 መጠን: በህንፃዎች እና ሌሎች  ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል.

5ኛ. መጠን ከ 6.0 እስከ 6.9: ጠንካራ መንቀጥቀጥ እና ለከባድ ጉዳት ያስከትላል:

6ኛ. 7.0 እና ከዚያ በላይ መጠን: ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት እና ሰፊ ውድመት ሊያስከትል ይችላል።

 
https://t.me/ethioengineers1


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
✅በርካታ ምክንያቶች በሲቪል ምህንድስና ውስጥ ለጠፍጣፋ ንጣፍ/Flat Slab ውድቀት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋና ምክኒያቶችን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡-

⚡️ከመጠን በላይ መጫን/Overloading፡-
ስላቡ ከዲዛይን አቅም በላይ የሆነ ጭነት ሲገጥመው ለምሳሌ ከባድ ዕቃዎችን ወይም ከባድ ቁሳቁሶችን ላዩ ላይ ማከማቸት።


⚡️ደካማ የግንባታ ልምዶች፡-
በቂ ያልሆነ የኮንክሪት ድብልቅ-mix ወይም ተገቢ ያልሆነ የማጠናከሪያ-Reinforcement አቀማመጥ ያሉ ጉዳዮች ስላቡን ያዳክማሉ።


⚡️የጎደለው ዲዛይን፡-
እንደ በቂ ያልሆነ ውፍረት ወይም ተገቢ ያልሆነ ጭነት ማከፋፈል ያሉ ጉድለቶች የስላቡን ታዐማኒነት ሊነሱት ይችላሉ።


⚡️የቁሳቁስ መበላሸት፡- የማጠናከሪያ-Reinforcement ወይም የኬሚካል ጥቃት ኮንክሪት ላይ መበላሸት በጊዜ ሂደት ስላቡን ሊያዳክም ይችላል።


⚡️የፋውንዴሽን አሰፋፈር፡-
የመሠረቱን እኩል አለመስተካከል ስላቡን ከአቅሙ በላይ ሊያስጨንቀው ወንም Stress ሊፈጥርበት ይችላል።


⚡️የሴይስሚክ እንቅስቃሴ፡-
የመሬት መንቀጥቀጦች ወይም የመሬት መንቀጥቀጦች ተለዋዋጭ-dynamic ሸክሞችን ሊጭኑ ይችላሉ፣የሚከሰተዉን ሸክም ስላቡ በበቂ ሁኔታ ካልተቋቋመ ውድቀት ሊያስከትል ይችላል።


⚡️የሙቀት ውጤቶች
የሙቀት መስፋፋት እና መኮማተር በተለይም ከፍተኛ የሙቀት ልዩነት ባለባቸው ክልሎች በዲዛይኑ ላይ በትክክል ካልተሰራ ወደ መሰባበር-cracks እና ውድቀት ሊመራ ይችላል።

⚡️Collapse/ውድቀትን ለመከላከል እነዚህን ሁኔታዎች በተገቢው ዲዛይን፣ የግንባታ ጥራት እና የጥገና አሰራር መፍታትን ይጠይቃል።

https://t.me/ethioengineers1


Репост из: BeGet Engineering Plc [CENGG]
🔶Advanced Structural Design

ST CHECK LISTS
እነዚህን መመዘኛ መስፈርቶች አሟልተን ነዉ ዲዛይን አሰገብተን  የምናስፈቅደው።
ለ 2 ወሩ Special Structural Design Package ስልጠና መጨረሻ ላይ እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን።

These are the checklists we will finally discuess for our 2months  special structural package course.
🔹Concrete Stru(Ordinary & High rise)
🔹Steel structure
🔸4
Software : Etabs, Sap, Safe, Idea statica

https://t.me/BeGetEngineering


ይህ እስካሁን በሚድያ ምንም ያልተነገረለት የህንፃ ግንባታ መመርያ በአዲስ አበባ የግንባታ ታሪክ ከፍተኛው ተፅእኖ ፈጣሪ ይመስለኛል፣ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ችያለሁ ❗️

መስከረም 3 ተፈርሞ ለሁሉም ክፍለ ከተሞች በተላለፈው በዚህ መመርያ መሰረት ከ15 ሜትር እና በላይ ስፋት ያላቸው መንገዶች የሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት ሴት ባክ (set back) ከተቀነሰ በኋላ ቢያንስ 500 ሜትር ካሬ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፣ ካልሆነ የግንባታ ፈቃድ አይሰጥም ማለት ነው።

በሌላ በኩል በነዚህ መንገዶች ላይ ዝቅተኛው የህንፃ የጎን ስፋት (frontage) ከ20 ሜትር ያላነሰ መሆን አለበት ይላል፣ ይህም ካልተሟላ የግንባታ ፈቃድ አይሰጥም ማለት ነው።

በዚህ ምክንያት በመቶ (ምናልባትም በሺዎች) የሚቆጠሩ ግንባታዎች እንዲቆሙ እየተደረገ ነው።

https://t.me/ethioengineers1


Репост из: BeGet Engineering Plc [CENGG]
Call for Advanced Level Training
1) Building Advanced Structural Design
2) Bridge Design 
3
) Project Planning & Contract Administration .

●Every Sunday Morning 3:00-8:00 LT.
Registration is active
Class starts on October 6/2024

📲
0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering


"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?"
🏷የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው።

💫በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል።

⭐️ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ  የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው  ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ  ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል።  የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ  ውኃ መጠጣት አለበት።

🌟የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል።

🌟(ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል።

⚡️ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው።


https://t.me/ethioengineers1

Показано 20 последних публикаций.