የክርስቶስ ሰይፍ.....#share
*የዐፄ ሰይፈ አርዕድ ሰይፍ ሰገባ ዳጋ እስጢፋኖስ መኖሩ አስገራሚ ነገር ነው።ሰይፈ አርዕድ የታላቁ ዐፄ ዓምደ ጽዮን ልጅ ነው።ከ1336-1364 ዓ.ም.ኢትዮጵያን ገዝቷል።እረፍቱ ግንቦት 15 ቀን 1364 ዓ.ም. ነው።
*ሰይፈ አርዕድ ስሙ ንዋየ ማርያም ይባል ነበረ።ሰይፈ አርዕድ የተባለበት ምክንያት በመሪራስ አማን በላይ "የጥንቷ ኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ"በሚለው መጽሐፉ ገጽ 165 መሰረት "ክርስቶስ በግብፅ ምድር ሳለ ለማርሄር "ኃያል ሆይ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ"ብሎ የሰጠው ሰይፍ በተድባበ ማርያም ይገኝ ነበረ።ዐፄ ዓምደ ጽዮን ይኼን ሰይፍ ታጥቀው በተሰለፉበት ከፍተኛ ጦርነት ሁሉ ድል አድርገዋል።አንድም ሽንፈት አልገጠማቸውም።
*እንደ መሪራስ አማን በላይ መረጃ ከሆነ ሰይፉ አለትን ይሰነጥቃል፣ድንጋዩን ይበታትነዋል፣የሰውን ገላ እንደ ጨርቅ ይቀደዋል።ሰይፉን ከአባቱ ዓምደ ጽዮን የተቀበለው ሰይፈ አርዕድ በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ አልፎ ላዕላይ ግብፅ ድረስ በመዝመት የግብፅ ሡልጣኖች መሊክ ኤስ ሳሊህ እና ሞግዚቱ አሚርሼኩም አስዋን ላይ ጦርነት ገጥሞ አሸንፏቸዋል።
*ይኼን አለትን የሚሰነጥቅ፣ድንጋዩን የሚበታትን፣የሰውን ገላ እንደ ጨርቅ የሚቀረድድ ሰይፍ ግብፅ ተሹመው በሚመጡት ጳጳሶች ለማሰረቅ ሞክራ ሳይሳካ ቀርቷል።አስገራሚው ነገር ዐፄ ልብነ ድንግል ሰይፉን ታጥቆ ግራኝን ለመዋጋት ፈልገው ሲሄዱ የፈጣሪ ፈቃድ ባለመሆኑ ከተድባበ ማርያም ወደሌላ ዋሻ በድብቅ እንዲቀመጥ ተደረገ ይላሉ መሪራስ አማን በላይ።
*ስለዚህ ይህ ሰይፍ ከተድባበ ማርያም ወደሌላ ከመሄዱ በፊት ዐፄ ዓምደ ጽዮን ለልጃቸው ንዋየ ማርያም አስታጠቁት ስመ መንግሥቱም ሰይፈ አርዕድ ተባለ።የዚህ አስገራሚ ሰይፍ ሰገባ ደግሞ የሚገኘው ዳጋ እስጢፋኖስ መሆኑን መረጃ ሳገኝ አግራሞት ፈጥሮብኛል።ሰይፉ ግን የት እንደሚገኝ ማወቅ አልቻልኩም።
*አዲሱ የዩቲዩብ ቻናላችን subscribe ያድርጉ ቤተሰብ ይሁኑ።https://www.youtube.com/channel/UC6m-V3zA2xrlwPPWtXLJ33A