#የሰኞመልዕክት የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመቀነስ ጋዜጠኞች ምን ማድረግ ይችላሉ?
አለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቀን ከቀናት በፊት በተለያዩ መርሐግብሮች ተከብሮ ውሏል። በዕለቱም በአስቸጋሪ የስራ አውድና ከባቢ ውስጥ ሁነው መረጃ የሚደርሱ ጋዜጠኞች ታስበው ውለዋል። ኢትዮጵያ ቼክም ለሙያ እና ለስነምግባር መርሆች ታምነው ማህበረሰባቸውን ያገለገሉ ጋዜጠኞችን ያመሰግናል!
ሆኖም የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶች ስርጭት ከፍተኛ ምስቅልቅል እየፈጠረ ባለበት በዚህ ወቅት የጋዜጠኞች ሚና መረጃን ከመዘገብም በላይ መሆን አለበት ብለን እናምናለን። በዚህ አኳያም ጋዜጠኞች ዘርፈ ብዙ አስተዋጾ ማበርከት ይችላሉ።
ጋዜጠኞች በቅድሚያ ማድረግ የሚችሉት በጎ አስተዋጾ የሙያ እና የስነምግባር መርሆችን በጥብቅ ማክበርና መፈጸም ሲሆን ይህም የሀሠተኛ መረጃን እና የጥላቻ መልዕክቶች ስርጭት በመቀነስ ረገድ የማይተካ ሚና አለው። ጋዜጠኞች ለሙያና ለስነምግባር መርሆችን በከፍተኛ ደረጃ ተገዥ በመሆን ዘገባቸው ትክክለኛ፣ ርዕታዊ፣ ከሀሠተኛ መረጃ የጸዳ፣ አካታችና ከጥላቻ መልዕክት የራቀ መሆኑን ማረጋገጥ የዕለት ስራቸው መሆን ይገበዋል። በተጨማሪም ግልጽነት የተሞላበት የዘገባ ሂደትን ማስፈን፣ ስህተት ሲፈጠር ቀጥተኛና ፈጣን ዕርምት መስጠት ከተከታታዮች ጋር የሚኖረውን የመተማመን ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።
በሌላ በኩል ጋዜጠኞች የመረጃ ማጣራት ስራን በመስራት እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን በማጋላጥ በጎ ተጽኖ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም በሚሰሩባቸው የሚዲያ ተቋማት የመረጃ ማጣሪያ ዴስክ በማቋቋም፣ የአየር ሰዐት ወይም የህትመት ቦታ በመመደብ፣ የግል የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን በመጠቀም እንዲሁም ገለልተኛ ከሆኑ የመረጃ አጣሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት መከወን ይችላሉ።
በተጨማሪም ጋዜጠኞች የሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን መለየት፣ ማጣራት እና ማጋለጥ እንዴት እንደሚቻል የሚያስተምሩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃት ፕሮግራሞችን በመስራትም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። ይህንንም የመረጃ ማጣራት ዘዴዎችና ቴክኖሎጅዎች በመማር እንዲሁም ባለሙያዎችን በመጋበዝ በቀላሉ መስራት የሚቻል ነው።
የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ከአሉታዊ ይዘቶች አንጻር የክትትልና የቁጥጥር ስራቸውን ጠበቅ እንዲያደርጉ በመወትወት እንዲሁም የህግ አውጭና ፈጻሚ አካላት የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕቶች በተመለከተ የሚያወጧቸውን ህጎችና ፖሊሲዎች ጉድለታቸውን በመፈተሽ እንዲሁም በትክክለኛ አግባብ መፈጸማቸውን በመከታተል በጎ ተጽኖ ማሳረፍ ይቻላል።
ጋዜጠኞች እነዚህንና ሌሎች የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭትን የሚቀንሱ ተግባራትን እንደሙያ ግዴታቸው በመቀበል በየዕለቱ መተግበር ከቻሉ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለን እናምናለን።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck