አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የመላኩ የቅዱስ ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው::
በዛሬው ቀን በያለንበት ቤተ ክርስቲያን አምላከ ቅዱስ ገብርኤል ማረን ይቅር በለን ከተቃጣብን ከመጣብን እሳት አድነን የምንልበት ቀን ነው።
እርሱም በባቢሎን አገር ከነደደ እሳት ውስጥ በጨመሩአቸው ጊዜ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳናቸው ተራዳኤ መልአክ ነው::
"ለገብርኤል መልአክኪ ዘፍሡሕ ገፁ" ፊቱን ደስ ያለው የተላላከልሽ የገብርኤል ድምፁን በመስማት ያለ አባት ፀነስሽው። በዚህም አብሳሬ ትብስኅት የተባለው ቅዱስ ገብርኤል ነው።
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማፅናናት የምስራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡
ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታት ገድላቸውን እንዲፈፅሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላዕክትን ወርሃዊና ዓመታዊ በዓላቸውን በፀሎትና በምስጋና ታከብራለች፤ በተለይ ታኅሣሥ ዐሥራ ዘጠኝ ቀን የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
በጣዖት ፍቅር እጅግ ያለመጠን ልቡ ተቃጥሎ የነበረው የባቢሎን መሪ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል አሰርቶ መኳንንቱን ሰብስቦ ሕዝቡ በሙሉ ለጣዖቱ እንዲሰግድ አዋጅ አወጀ፡፡
ያ ዘመን ለእግዚአብሔር ወዳጆች የፈተና ዘመን ነበር፡፡ አስመሳዮች ለጣዖት ሰገዱ፤ ተረበረቡ፡፡ እውነተኛ አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ‹‹ ንጉስ የወደደው፣ ጊዜ የወለደው›› በሚል አስተሳስብ አይለወጥም፡፡ በዚያ ፈታኝ ዘመን ነበር ሶስት ታማኝ የእግዚአብሔር ባለሟሎች የተገኙት፡፡
ንጉሱ ላቆመው ጣኦት ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ውሳኔው መሆኑን ወጣቶቹ በሚገባ ያውቁታል ግን ይህንን አልፈሩም፡፡
ንጉስ ሆይ አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣዖት አንሰግድም አሉት፡፡
ሶስቱ ወጣቶች የወሰዱት ይህ አቋም ለንጉሱ ታላቅ ራስ ምታትን ፈጠረ፤ ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
እሳቱም ሰባት እጥፍ ነደደ፡፡ ወዲያውኑ የንጉሱ አገልጋዮች አናንያ ፣ አዛርያን እና ሚሳኤልን እያንከበከቡ አንጠልጥለው ወደ ዕቶን እሳቱ ወረወሯቸው፡፡
በእሳቱ ኃይል የተነሳ አገልጋዮቹም በእሳቱ እየተጠለፉ እንደ ማገዶ ነደዱ፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን ከየት እንደመጣ ከማይታወቅ እንግዳ ጋር በመሆን በዕቶን እሳት ውስት ይንሸራሸሩ ጀመር፡፡ ይህ ተዓማራት ንጉሡንና መኳንንቱን አስገረመ፡፡ ንጉሡም በዚህ ወቅት፦
‹‹ እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ እሳቱ ምንም አላቆሰላቸውም አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል ፡፡ ›› አለ፡፡
ንጉሥ ናብከደነፆር በግልፅ ተመልክቶ እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠልስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
በግዕዙ ‹‹ ወገፁ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብኤር ይመስል›› አራተኛውም ፊቱ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል ይላል፡፡
አዎን፤ ከዚህ በላይ እንደተገለፀው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉትን ወጣቶች የነደደውን እሳት አብርዶ በሃይማኖታቸው እንደ አፀናቸው ተመልክተናል፡፡
የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት እኮ ጥንት የነበረ ብቻ ሳይሆን እስከ አለንብት ዘመን ደርሶ የመልአኩን አማላጅነት በዓይን የተመለከትነው ተጨባጭ ድርጊት ነው፡፡
የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ስጋ እና ነፍስ ድነው እውነተኛ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡
በመልአኩ ስም በፈለቀው ፀበል ተጠምቀው ደዌ የራቀላቸው በምልጃው የተቋረጠው ሕይወታቸው የተቀጠለላቸው እጅግ በርካታ ናቸው፡፡
በየዓመቱ በተለያዩ በቅዱስ ገብርኤል ስም በታነፁ አብያተ ክርስቲያናት የሚሰባሰበው ምዕመን ስዕለቱ የሰመረለት ልመናው የተሰማለት ተምኔቱ የተፈፀመለት ብዙ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡
ስለዚህ ለመላዕክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ፀጋ ተረድተን መልአኩን ልናከብረውና ልናመሰግነው ይገባል፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም መላኩ ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ በፊታችን ቆሞ ይጠብቀን ያድነን ለዘላለሙ አሜን::
🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️