ብዙዎቻችን የተረዳነው አይመስልም። ገና ካሁኑ እጃችሁን ታጠቡ መባሉ ሰልችቶናል። ስርጭቱ እንዲገታ የምንችለውን ሁሉ ካላደረግን፣ በመደዳ ያጭደናል። እግዜሩም የሚረዳን እኛ ራሳችንን ስንረዳ ነው።
ምናልባት ኢንተርኔት በመጠቀም ዘመናችን፣ ከዚህ የተሻለ ለህብረተሰብ ጥቅም መረባረብ የምንችልበት ጉዳይ/ጊዜ ገጥሞን አያውቅም። አክቲቪስት ነኝ ብለን ብንራቀቅ፣ ባለስልጣን ነን ብለን ብንመጻደቅ፣ ታዋቂ ነን ወይ ገንዘብ አለን ብለን ብንኮፈስ ሁላችንም ይደቁሰናል።
ወገን፥ አለማወቅ ወይ ቸልተኝነት አያድነንም።
በመረጋጋት ሆነን፣ በባለሞያዎች የሚሰጡ መመሪያዎችን ለመተግበር እንሞክር።
መረጃ በማጋራት እና የምንችለውን ጥንቃቄ በማድረግ፣ ጉዳት መቀነስ እንችላለን፤ ከጸጸት መዳን እንችላለን።