ሰው መጽናናት ይፈልጋል። ወደመዝናናት የሚያደርሰውን መንገድ ይመርጣል። እውነታን በመገንዘብ የነገን እውነታ መልክ ማሳመር ሲችል፣ እውነታን በመካድ የነገን እውነታ መልክ ማበላሸት ይመርጣል። ይህን ያስባለኝ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ፣ ከመከላከያ እና ጥንቃቄ መልእክቶች ይልቅ፣ የሚያጽናኑ ወሬዎች የሚሰራጩበት ፍጥነትና ስፋት ቢደንቀኝ ነው። መሸበር አያስፈልግም። መጠንቀቅ ግን ያስፈልጋል።
(ላምሳሌ: በሽታው ወጣት አይገልም የሚል ሙሉ ለሚሉ እውነት ያልሆነ ወሬ፤ ከሚሞተው የሚድነው ይበልጣል፤ መድኃኒት አገኘን የሚሉ ጠንቋዮች እና የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ውዥንብር፤ የተመራማሪዊቹን ልፋት አፈር የሚያበላ የሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ፤ conspiracy theory)
ማነው ቤቱ ውስጥ ጣሪያው ተሸንቁሮ፣ "አይ አብዛኛው ደህና ነው" ብሎ የሚተኛ?
ማነው "ቤቱ በብዛት ግድግዳ ስለሆነ በሩ ባይቆለፍም ችግር የለውም" ብሎ ክፍቱን ትቶት የተኛ
ማንስ ነው "ዐይኔ ውስጥ የለው ጉድፍ ከዐይኔ ስፋት መጠን ጋር ሲነጻጸር ብዙም አይደለም" ብሎ የተወው?
ወገን፥ በዓለም ላይ ይሄ ሁሉ መንግስት እና የጤና ባለሙያ ጅል ሆኖ አይደለም ሌት ተቀን የሚጮኸው እና ለመከላከል ሥራ አስቁሞ የሚጨነቀው።
በተለይ እንደ እኛ ላለ አገር፣ ከመከላከል አንጻር ሲታይ ህክምና በጣም ውድ ነው!! አቅሙ የለንም! እንኳን ለወረርሽኝ ለተራ ሆድ ህመም እንኳን መከላከል ነው ርካሽ።