መርሕ
👉ተንቀሳቃሽ የሆኑ ንብረቶች ባለሀብት ተደርጎ የሚቆጠረው ንብረቱን በእጁ የያዘው ግለሰብ እንደሆነ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1186 ንዑስ አንቀጽ 1 በግልጽ ይደነግጋል።
👉ነገር ግን ይህ ድንጋጌ እንደመኪና ያሉትን ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን የማይጨምር ስለመሆኑ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1186 ንዑስ አንቀጽ 2 “ልዩ የሆኑ አንዳንድ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ የሕጎች ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው።” በማለት እንደመኪና ያሉ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን በመያዝ ብቻ ባለሀብት መሆን እንደማይቻል ልዩ ድንጋጌ አስቀምጦ እናገኛለን።
በውክልና መኪና መሸጥ
👉በተለምዶ መኪናን ስም ዝውውር ሳይፈጸም ሻጭ ለገዢ የመኪናውን ስም ማዞር የተመለከተ ውክልና በመስጠት ሽያጭ ሲደረግ ይስተዋላል።
ምንም እንኳን ሻጩ መኪናውን በሽያጭ ለገዛው ወገን ያስተላለፈው ቢሆንም የመኪናው ስመ ሀብት የሚታወቀው በሻጭ ሆኖ የስም ዝውውር እስካልተፈጸመ ድረስ በሕግ የመኪናው ባለቤት ሻጭ ነው።
👉ይህም ማለት በመኪናው ማንኛውም ዓይነት ጉዳት የተፈጸመ እንደሆነ ለደረሱት ጉዳቶች መኪናው በስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው ሰው ኃላፊ ይሆናል ማለት ነው።
የሻጭ ኃላፊነቶች
👉ስም ዝውውር ያልፈጸመና መኪናው በስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው ግለሰብ በሽያጭ ብቻ ባስተላለፈው መኪና ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ከገዛውና ጉዳት ካደረሰው ሰው ጋር በጋራ ወይም በተናጠል የደረሰውን ጉዳት የመካስ ግዴታ አለበት።
👉ለደረሰው ጉዳት ለብቻ ተጎጂውን የካሰ እንደሆነ ከገዢው ላይ የከፈለውን ክፍያ እንዲተካለት የመጠየቅ መብት ይኖረዋል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም የፌደራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ