ለፈገግታ😅😅
(ሶስት ሁነን ተጎልተን እየደሰኮርን ነዉ ያዉ ሴትም አይደለን😂 እኔ ሜሪ ና ቤቲ ሁነን ( ቤቲ ብዙ አታወራም የኛ ወሬ ስለወንድ ነዋ እሷ ለታማኝ ባሏ ታማኝ ሚስት ናታ😅) ተቀላቀሉን)
" ሜሪዬ ያንን ተስፋዬን ትናንት አግኝቼዉ እኮ"
"አትይኝም! ያጅብ አገጭ የት ጉድጓድ ገብቶ አገኘሽዉ ነዉ?"
" ታክሲ ዉስጥ ነዋ ይሄ ከረፈፍ ሌላ ሴት መስዬዉ ሲለፋደድብኝ ቆዬ"
"መች ይሁን እንደ ወንድ ቆፍጠን የሚለዉ ሁሌም ሴት ስር ኤዲያ ! "
"ወንድ ብሎ ፍጥረት ተይዉ እስኪ ሜሪዬ ባሌ አትበይ ባላችን ነዉ ሚባለዉ ብላለች ወይንዬ "
( ቤቲ ቱግ አለች ባሏን ስለምትወደዉ ወንድ ስሳደብ ደሟ ነዉ ሚፈላዉ)
" ምን መሆናችሁ ነዉ ? አሁን የኔን ባል ማን ጋ አያችሁት እድሜ ልኩን ታምኖልኛል እኮ በባለጌ አትመስሉ ወንድን ብትታመኑ ታማኝ ታገኙ ነበር እሽ እጭ እጭ! "
( ሜሪ ሳቀች በጣምና..)" ስሚማ ቤቲዬ አዲስ ሲም አዉጥቻለሁ የኤልሳ ፎቶ ልኬ ላዉራዉ እስኪ ታማኙን 😂😂 ከዋለለ ኩሪፍቱ በራስሽ ወጭ ትጋብዠናለሽ ከታመነ የአምስተኛ አመት በአላችሁን በኛ ወጪ it that ok? "
"(ቤቲ በድፍረት እሺ)"
ኦን ላይን ነበር ......
" ሰላም ቆንጆ"
"ሰላም ቆንጂት"
"እንዴት ነክልኝ የኔ መለሎ በፎቶ ብቻ ሰዋከኝ እኮ"
"አፍሽ ሲጣፍጥ"( ቤቲ ዘ አይን ዘ መጉረጥረጥ😂)
"ፍቅረኛ አለክ ዉዴ?"
"ኧረ ሴት ሳወራ እንኳን የመጀመሪያዬ ነዉ ጣፋጭ"
(ቤቲ ዘ እንባ ዘ ዱብ ዱብ)
( ፎቶ ላከችለት የኤልሳን ኤልሳ ቂጦዬ😍)
"ስታምሪ የኔ መልአክ ና በይኝ ልምጣ"
(ሜሪ ተበሳጨች ማሸነፍ ብትፈልግም ይሄን ያህል እንዝላል ነዉ ብላ አላሰበችም ፃፈችለት...)
" አንተ ቅሌታም ባለጌ ሜሮን ነኝ የሚስትህ ጓደኛ ዘልዛላ ነገር ቀሽም"
አየዉ.....ዝም .........ጭጭ.........ጭጭ
ቤቲን ማባበል ጀመርን....የሜሪ ስልክ ጮኸ ምና አባቱ ሊል ይሁን እያለች አነሳችዉ.....
"ወዬ ሜሪዬ ጫጫታ ስለነበር አልተነበበኝም ምንድን ነበር ያልሽኝ?"
😂😂😂😂😂😂😂😂ሜሪዬ ሳቅ ፍርስ ቤቲዬ መንታዉን እልቅስ እኔ ከሁሉም እንዳልሆን ወደቤቴ ቆስ😂😂😂😂
✍ፋኢዛ
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
For any comment
@mornin_bot