ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


በዚህ ቻላል እግዚአብሔር እንደፈቀደ ሰዎች ጥያቄ የፈጠረባቸውን መልሱን ፈልገው እንድያገኙበት ይርዳ ዘንድ የተመለሱ ጥያቄዎችን በቤቱ ያሉትም ከቤቱ ውጭ ያሉትም ፈልገው ያገኙበታል ሼር በማድረግ የድርሻውን ይወጡ እንድመልስላቹ የምትፈልጉትን ጥያቄ ይላኩልን https://www.youtube.com/channel/UCALs0oI8MNndUaK9l-vkGwA?sub_confirmation=1. ለአስተያዬት @Semagnd

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜


🍀ሥራ በመንፈሳዊም በዚህ ዓለምም ያስከብራል

መንፈሣዊውንም ዓለማዊውንም ሥራ ሳትደክሙ ለምትሠሩ ለእናንተ ትልቅ አክብሮት አለኝ ምክንያቱም ሁሉም እንደ እናንተ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልመና ይቀር ነበር  እነዚህ ጥቅሶች ለእናንተ ነው።

“አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ (ዮሐ 5:16)” ብሎ እንዳስተማረን እግዚአብሔር ድንቅ ነገርን ሲሠራ ይኖራል። በሥራ አንቀፅ የጀመረው መጽሐፍ ቅዱስ “እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ (ራዕ 22:12)”“ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን:- ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና:- ሥራ ከቶ ሳይሠሩ፥ በሰው ነገር እየገቡ፥ ያለ ሥርዓት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና (ተሰሎ 3:10)”“ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት (ገላ 6:9)”“ “ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ (ሮሜ 12:11)”“ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም። የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል (2 ጢሞ 2:6-7)”ራሱም በሰው ላይ ላለመክበድ እየሠራና እየደከመ ይኖር እንደነበር ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች “በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፥ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፥ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን (1 ቆሮ 4:12-13)”ሌሎችንም ማስቸገር እንደሌለበት ሲናገር “ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም” ( 2ኛ ተሰሎ 3፡8)
“አንተ ታካች፥ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ? ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂት ታንቀላፋለህ፥ ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅህን ታጥፋለህ፤ እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል (ምሳሌ 6:7-11)”
“የትጉ እጅ ትገዛለች፤ የታካች እጅ ግን ትገብራለች (ምሳሌ 12:24)” ይልና  “የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች። በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፤ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል (ምሳሌ 10:4-5)”
“ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና (ምሳሌ 21:25)”
“የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፤ አንዳችም አታገኝም፤ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች (ምሳሌ 13:4)” “በሥራው ታካች የሚሆን የሀብት አጥፊ ወንድም ነው (ምሳሌ 18:9-10)”ክርስቲያን በሥራ መትጋትን በምንም ሊተካው አይችልም፡፡ ምድራዊ ሀብትም ይሁን ሰማያዊ ጽድቅ በመትጋት እንጂ በመታከትና በመተኛት አይገኝም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፤ ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ (ምሳሌ 14:23-24)” በማለት ልምላሜ (ትርፍ) በድካም (በመሥራት) እንጂ በከንፈር (በማውራት) እንደማይገኝ አስገንዝቦናል፡፡ በተጨማሪም “ምድሩን የሚያርስ እንጀራ ይጠግባል፤ ምናምንቴዎችን የሚከተል ግን ድህነት ይሞላበታል። የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም (ምሳሌ 28: 19-20)” ብሎ መትጋትን ገንዘብ እንድናደርግ አስተምሮናል፡፡ እንቅልፍን መውደድም እንዲሁ ለድህነት እንደሚዳርግ ሲናገር “ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ (ምሳሌ 20:13)” ብሏል፡፡

@felgehaggnew


ሁሉ ተፈቅዷል የሚል የተጨፈለቀ ንግግር እኔ አይመቸኝም ሁሉ ተፈቅዷል በሚል ሰው ሰውን አርዶ እንዳይበላ አትግደል የሚለውን ሕግ ፈርቶ ቢተው እንኳን ሰው የገደለውን ሰው ሊበላ ነው ማለት ነው ያው ሁሉ ከተፈቀደ ጫትም ሲጋራም መስከርም ተፈቅዷል? ሁሉ ተፈቅዷል ሲባል እስከምን የሚል መጨመር አለበት። ትውልድ ገዳይ ትምህርት እንዳሆን


🔴ቃዴስ በገና ተቋም🟢
🔹የበገና የክራር የከበሮ ትምህርት እንሰጣለን
🔹በፈለጉት ሰዓት በማመቻቸት መማር ይችላሉ
🔹 ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከስራ ሰዓት በኋላም መማር ይችላሉ(ከእሁድ እስከ እሁድ)
🔹  በህብረት ውይም በግል መማር ይችላሉ                                                            👉🏻👉🏻🟣 ከሁለት በላይ ሆናችሁ ከመጣችሁ ዋጋ በጣም እንቀንሳል
🔹ጥራት ያላቸው በገና ክራር መሰንቆ ዋሽንት ከበሮ በተመጣጣኝ ዋጋ እንሸጣለን
🔹ልዩ የሆነ ስልጠና ለህጻናትም እንሰጣለን  online ይቻላል
🟣አድራሻ ፡ ቦሌ ቡልቡላ ከማሪያም ማዞሪያ 100ሜ ገባ ብሎ ቬሮኒካ ህንጻ ዳሽን ባንክ ወይም ከገበረው ድርጅት ያለብት ሁለተኛ ፎቅ ላይ
ለበለጠ መረጃ 📞 0933703002
                      📞 0991314522                                                                              

telegram JOIN👇👇👇👇

https://t.me/kades123beg

share share


🔴ቃዴስ በገና ተቋም🟢
🔹የበገና የክራር የከበሮ ትምህርት እንሰጣለን
🔹በፈለጉት ሰዓት በማመቻቸት መማር ይችላሉ
🔹 ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከስራ ሰዓት በኋላም መማር ይችላሉ(ከእሁድ እስከ እሁድ)
🔹  በህብረት ውይም በግል መማር ይችላሉ 👉🏻👉🏻🟣 ከሁለት በላይ ሆናችሁ ከመጣችሁ ዋጋ በጣም እንቀንሳል
🔹ጥራት ያላቸው በገና ክራር መሰንቆ ዋሽንት ከበሮ በተመጣጣኝ ዋጋ እንሸጣለን
🔹ልዩ የሆነ ስልጠና ለህጻናትም እንሰጣለን 
🟣አድራሻ ፡ ቦሌ ቡልቡላ ከማሪያም ማዞሪያ 100ሜ ገባ ብሎ ቬሮኒካ ህንጻ ዳሽን ባንክ ወይም ከገበረው ድርጅት ያለብት ሁለተኛ ፎቅ ላይ
ለበለጠ መረጃ 📞 0933703002
                  📞 0991314522

telegram JOIN👇👇👇👇

https://t.me/kades123beg

share share


እንኳን አደረሳችሁ ከስንት ዓመት በፊት የተጻፈች አስታወስኩና forward አደረኩላችሁ😁


Репост из: ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው
እግዚአብሔር ልጅ አንተ ነህ፣በመስቀልና በትንሣኤ ተስፋን የሰጠኽን የእግዚአብሔርና የሰው ልጅ አንተ ነህ።

እኔስ ከሊቁ ከቅዱስ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ ጋር ሁኜ እንድህ እላለሁ
በአምላኩ ደም የተቀደሰ ከፈጣሪው ጎን በወጣ ውኃ የተጠመቀ ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
ለገነት ዛፎች አክሊል ለገዳም ዛፎችም ክብር የሆናቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
ለአሸናፊ እግዚአብሔር በግ መሠዊያ የሆነው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ለእሥራኤል አምላክ የፋሲካው መሠዊያ የሆነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
የጎልጎታዊው የምሥጢር ወይን ማፍለቂያ የሆን ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ከእርሱ ምእመናንን ለማተም የሚሆን የሕግና የሥርዓት ደምን ያንጠባጠበ ዕፅ ምን ዓይነት ነው!
ብሩካን በጎችን ለማጠቢያ የሚሆን ምንጭን ያወጣ ዕፅ ምን ዓይነት ነው !
ምድርን የቀደሳት ሰማይንም ያማተበበት ዓለምንም ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በረከት የባረከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ሰማያውያንን ከምድራውያን ያስተባበራቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
አዳምን ከስሕተት ያዳነው ሔዋንን ከሞት ጻዕረኛነት ነጻ ያወጣት ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
ስለእርሱ አስቀድሞ በኦሪትና በነቢያት የተነገረየሰበሰባቸው በሐዋርያትም በገሐድ የተሰበከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
የተከተሉትን የበተናቸው ያመኑትንም ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ቤቴ ክርስቲያንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ላይ የመሠረታት ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
አልጫውን ያጣፈጠ ርኩሱንም ያነጻ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ድኻውን ከፍ ከፍ ያደረገ በደለኛውን ያጸደቀ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ደካማን ያበረታ ሕመምተኛውንም ያዳነ ዕፅ እንደምን ያለ ነው !
ጥቂቱን ያበዛ ሰነፉንም ጥበበኛ ያደረገ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
መካኗን ወላድ ያደረገ ጨለማውን ያበራ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
@felgehaggnew
@felgehaggnew


Репост из: ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው
🌺🌺🌺መስቀል🌺🌺🌺

አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እስኪ ከክርስቶስ ደም እና ከኤልያስ ማን ይበልጣል ?

መቼም ሁላችሁም የክርስቶስ ደም እንደምትሉኝ እርግጥ ነው ነገር ግን አንዳንዶች ይሄን በአፍ ብቻ የሚያደርጉት አሉ ግን ደግሜ ልጠይቃችሁ ከኤልያስ ጨርቅ እና ከክርስቶስ መስቀል የትኛው ይበልጣል?

ይሄን ለእናንተ ልተወው እና ኤልያስ እና ኤልሳዕ በኤልያስ ጨርቅ የዮርዳኖስን ባሕር ባንድ ሳሉ ኤልያስ በጨርቆ ባሕር ከፍሎ ተሻግረውበታል ከዚያን በኃላ ኤልያስ በእሳት ሰረገና ሲወሰድ ከኤልያስ የወደቀ ልብስ ነበር ኤልሳዕም የኤልያስን ጨርቅ እንደተራ ጨርቅ አላየውም ይልቁልስ መለኮታዊ ኃይል እንዳለው ተረዳ እንጅ በሥጋዊ አይን የኤልያስ ጨርቅ ተራ ጨርቅ ነው ሥጋዊ የሆነ ሰው ያን ጨርቅ ባሕር ይከፍልልኛል ብሎ አያስበውም ከተራ ጨርቅነት ውጭ ለሱ ትርጉም አይኖረውም ምክንያቱም መንፈሣዊ ሰው ሳይሆን ሥጋዊ ሰው ነው እንጅ ኤልሳዕ ግን በሥጋዊ አይኑ አልተወሰነም ይልቁንስ በመንፈሳዊ ዓይን ያ ጨርቅ ተራ ጨርቅ እንዳልሆነ ተመለከተ እንጅ መልኮታዊ ኃይል እንዳለው አየ እንጅ ጨርቁንም ወስዶ ባሕር ከፈለበት ታድያ ኤልያስ ጨርቅ ይሄን ታምር ካደረገ የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልማ ምን አይነት ታምር ያደርግ ይሆን የክርስቶስ ደም የፈሰሰበት ክርስቶስ ተሰቅሎ ዓለም ያዳነበት መስቀል ምን ዓይነት ይሆን
እኛስ ኤልያስ ባሕር የከፈለበትን ጨርቅ ይዞ ባሕር እንደከፈለበት ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ ጠላት ድል እንዳደረገልን እኛም የሱን መስቀል ይዘን ጠላትን ድል እንነሳው አለን
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ተራራ ከሙሴ እና ከኤልያስ ጋር ደቀ መዝሙርቱን ይዞ የታየበትን ተራራ ቅድሱ ተራራ ይለዋል ታድያ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ደሙ የፈሰሰበትን መስቀል ምን ይኃል ቅዱስ ይሆን እኛስ ጴጥሮስ ያን ተራራ ቅዱስ ብሎ ከጠራው መስቀሉንም አብልጠን ለምን ቅዱስ አንለውም
እስኪ ልንጽጽር ትንሽ አንስተን በመስቀሉ ላይ እና በደብረ ታቦር ማን እንደሆነ እንይ
🌺በደብረ ታቦር ተራራ የኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ
🌺በመስቀል ላይ ከክርስቶስ ጐን፡በጦር፡ሲወጋው፤ወዲያውም፡ደምና፡ውሃ፡ወጣ።ከሞተ ሰው ደም አይወጣም ነገር ግን ክርስቶስ ሙቷልም ሕያውም ነው ብለን እንድንናገር አደረግን እንደሞተም ሕያውም እንደሆነ ነገረን
🌺በደብረ ታቦር ሙሴ እና ኤልያስ ታዪ
🌺በመስቀል ላይ ቀኑ ጨለመ ፀሐይም ብርሃኗን ነሳች
🌺በደብረ ታቦር የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ተሰማ
🌺በመስቀል ላይ ሆኖ የቤተ፡መቅደስ፡መጋረጃ፡ከላይ፡እስከ፡ታች፡ከኹለት፡ተቀደደ፥ምድርም፡
ተናወጠች፥አለቶችም፡ተሰነጠቁ
በመስቀል ላይ የሆነውን ዘርዝረን አንጨርስም የእኛ መዳን የተፈጸመበት ትንቅ ታምር የታየበት ነው እና
ታድያ ይሄን ተራራ ቅዱስ ብሎ ጴጥሮስ ሲጠራው እናይ አለን
2ኛ ጴጥ 1:18፤እኛም፡በቅዱሱ፡ተራራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ሳለን፡ይህን፡ድምፅ፡ከሰማይ፡ሲወርድ፡ሰማን።
ጴጥሮስ ይሄን ተራራ ቅዱስ ብሎ ከጠራ የክርስቶስ ደም የፈሰሰበት መስቀልማ እንዴ ቅዱስ አይሆን? ።
ነብያትም ሐዋሪያትም ስለመስቀሉ ተናገሩ
መዝ 22:4፤በሞት፡ጥላ፡መካከል፡እንኳ፡ብኼድ፡አንተ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነኽና፥ክፉን፡አልፈራም፤በትርኽና፡ምርኵዝኽ፡እነርሱ፡ያጸናኑኛል።
በትር የተባለው የሃይማኖት በትር ነው ምርኩዝህም ሲል መስቀልን ማለቱ ነው
ምእመናን ከመናፍቃን ጋር እንዳይተባበሩ በእርሱ ይገሠጻሉና
ማቴ 5:15፤መብራትንም፡አብርተው፡ከእንቅብ፡በታች፡አይደለም፡እንጂ፡በመቅረዙ፡ላይ፡ያኖሩታል፡በቤት፡ላሉት፡
ዅሉም፡ያበራል። መቅረዝ የተባለውም መስቀል ነው ፤ መብራትም የተባለውም አማኑኤል ነው በእርሱ የሚያምን ሁሉም ወደ ብርሃን ይሔዳል ጨለማ አያገኘውምና
መዝ 59:4፤ከቀስት፡ፊት፡ያመልጡ፡ዘንድ፥ለሚፈሩኽ፡ምልክትን፡ሰጠኻቸው።
ምልክት የተባለው መስቀል ነው
መዝ 85:17፤ምልክትንም፡ለመልካም፡ከእኔ፡ጋራ፡አድርግ፤የሚጠሉኝ፡ይዩ፡ይፈሩም፥አቤቱ፥አንተ፡
ረድተኸኛልና፥አጽንተኸኛልምና።ብሎ ቅዱስ ዳዊት የተናገረለት ነው።
ነቢያት የመስቀሉን ምልክት አሳዩ ሙሴ የመስቀልን ምልክት በራፊድ ምድረ በዳ ሠራ ኢያሱን አማሌቃውያንን እንዲዋጋቸው አዝዞ እርሱ ወደ ተራራ ወጣ ሁለት እጆቹንም ዘርግቶ በመስቀል አምሳል ከፍ አድርጎ ከጠዋት እስከ ማታ ቆየ እጆቹንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ያሸንፋል እሥራኤልም ይሸነፋል እጆቹን በዘረጋ ጊዜ ግን አማሌቅ ይሸሻል እሥራኤልም ያሸንፋል አሮንና ሖርም እጆቹን ተሸክመው ዋሉ የሙሴም እጆች ከባዶች ነበሩ ስለዚህም እጆቹን እንዳያወርድ ታላላቅ ድንጋዮችን በወዲህና በወዲያ አደረጉ
በመስቀል አምሳል በተዘረጉት እጆቹ አማሌቅ ድል ሆኑ (ዘጸ 17:8-13)።
ሙሴ በመስቀል ምልክት ጠላቶቻቸውን ድል እንዳደረጉ እኛም በመስቀሉ ጠላትን ድን እናደርግ አለን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል
1ኛ ቆሮ 1:18፤የመስቀሉ፡ቃል፡ለሚጠፉት፡ሞኝነት፥ለእኛ፡ለምንድን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ኀይል፡ነውና።
እግዚአብሔር ሙሴን እንድህ ይለዋል
5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በሕዝቡ፡ፊት፡ዕለፍ፥ከእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤ወንዙንም፡ የመታኽባትን፡በትር፡በእጅኽ፡ይዘኻት፡ኺድ።
እግዚአብሔር ለሙሴ ለምን ወንዙን የመታኽባትን በትር በእጅኽ ይዘኻት ሂድ አለው ለምን ያለዚያች በትር ቢሄድስ ወይስ ሌላ በትር ይዞ ቢሄድስ ይሄ የሚያሳየው እግዚአብሔር ያችን በትር መለኮታዊ ኃይል እንድኖራት አድርጓል ማለት ነው
ምክንያቱም ያች በትር እግዚአብሔር በዚያች በትር ሁኖ እስራኤልን ከግብጽ ያሻገረባት እና ልዩ ታምራት ያደረገባት ስለሆነች ነው
እኛም ብርሃን ዓለም ጳውሎስ እንዳለ
ገላ 6:14፤ነገር፡ግን፥ዓለም፡ለእኔ፡የተሰቀለበት፡እኔም፡ለዓለም፡የተሰቀልኹበት፡ከጌታችን፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡መስቀል፡በቀር፡ሌላ፡ትምክሕት፡ከእኔ፡ይራቅ።
እራሱ ጌታ ኢየሱስም የሚወደኝ ቢኖር መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ እንዳለ መስቀሉን ይዙን ሙሴ ያችን በትር ይዞ ብዙ ታምራት እንዳደረግ እኛም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ጠላትን ድል እናደርገው አለን ሙሴ ያችን በትር የእግዚአብሔር በትር ይላታል
ዘጸ 17:9፤ሙሴም፡ኢያሱን፦ጕልማሳዎችን፡ምረጥልን፥ወጥተኽም፡ከዐማሌቅ፡ጋራ፡ተዋጋ፤እኔ፡ነገ፡የእግዚአብሔርን፡ በትር፡በእጄ፡ይዤ፡በኰረብታው፡ራስ፡ላይ፡እቆማለኹ፡አለው።

ሙሴ ያችን በትር የእግዚአብሔር በትር ካላት እኛማ እንዴት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክሕት ከእኔ ይራቅ አንል መስቀሉን ይዘን
ያዕቆብም ኤፍሬምና ምናሴን በባረከ ጊዜ የመስቀልን ምልክት አሳየ ዮሴፍ ምናሴን በግራው በእሥራኤል በቀኙ አቆመው ኤፍሬምንም በቀኙ በእሥራኤል ግራ አቆመው እሥራኤልም እጆቹን አስተላለፈና ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ግራ እጁንም በምናሴ ራስ ላይ አደረገ ዮሴፍም እሥራኤልን የሚበልጠው ይህ ነውና ቀኝ እጅህን በእርሱ ላፕ አድርግ አለው እሥራኤልም ልጄ ሆይ ዐውቃለሁ ይህ ደግሞ ታላቅ ሕዝብ ይሆናል አለው። (ዘፍ 48:3-14)።

ስለ መስቀልህ አንተ የአባቶቻችን አምላክ በወዳጅህ በሙሴ አንደበት ለእሥራኤል ልጆች እንዲህ አልካቸው እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያድርጉ ዘንድ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ ይህም ምልክት ይሁናችሁ( ዘኁ 15:38)። እኛም የተጠመቅን ዕፅ መስቀልህን ምልክት አደረግን ካልተጠመቁት የተለየን እንሆን ዘንድ።
ማኅየዊ በሚሆን በሕማማተ መስቀልህ ዓለምን ትቤዥ ዘንድ ወንድ ከማታውቅ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆንክየ


🌼🌻እንኳን አደረሳችሁ🌼🌻

ይህንን ዓመት በእግዚአብሔር ምሕረት እና ፍቅር በአዲስ ተስፋ እንጀምር።ትናንት ሄዷል ነገ ገና አልመጣም, ዛሬ ብቻ ነው ያለን
እያንዳንዱ አዲስ ዓመት ለእኛ የሚከፍትልን የተስፋ ጉዞ ነው ።አዲሱ ዓመት ያለፈውን ትተን የወደፊቱን በእምነት የምንጠባበቅበት ጊዜ ነው እያንዳንዱ ሰው በምድር ላይ በሚኖረው እያንዳንዱ ቅጽበት እና እያንዳንዱ ክስተት በነፍሱ ውስጥ አንድ ነገር ይተክላል።

መልካም በዓል ለሁላችሁ ።

@felgehaggnew


St. Cyril of Jerusalem (c. 313 – 386)
Key Work: Catechetical Lectures
Quote: "The Church is called Catholic, then, because it extends over all the world, from one end of the earth to the other; and because it teaches universally and completely one and all the doctrines which ought to come to men’s knowledge, concerning things visible and invisible, heavenly and earthly."


ከደጅህ_ስደርስ_ልቤ_ይመታል_ወደ_ማደሪያህ_እግሬ_ተነስቷልኦ_ጌታዬ_ሆይ3_ልቤ_አንተን_ይመኛል https://t.me/felgehaggnew




Репост из: ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው
Melito the Philosopher, bishop of Sardis
If therefore it might come to pass by the power of your grace, it has appeared right to us your servants that, as you, having overcome death, do reign in glory, so you should raise up the body of your Mother and take her with you, rejoicing, into heaven. Then said the Savior [Jesus]: "Be it done according to your will" (The Passing of the Virgin 16:2-17 [A.D. 300]).
Timothy of Jerusalem
Therefore the Virgin is immortal to this day, seeing that he who had dwelt in her transported her to the regions of her assumption (Homily on Simeon and Anna [A.D. 400]).
Epiphanius, Panarion
“If the Holy Virgin had died and was buried, her falling asleep would have been surrounded with honour, death would have found her pure, and her crown would have been a virginal one...Had she been martyred according to what is written: 'Thine own soul a sword shall pierce', then she would shine gloriously among the martyrs, and her holy body would have been declared blessed; for by her, did light come to the world." 78:23 (A.D. 377)
John the Theologian
The Lord said to his Mother, "Let your heart rejoice and be glad. For every favor and every gift has been given to you from my Father in heaven and from me and from the Holy Spirit. Every soul that calls upon your name shall not be ashamed, but shall find mercy and comfort and support and confidence, both in the world that now is and in that which is to come, in the presence of my Father in the heavens". . . And from that time forth all knew that the spotless and precious body had been transferred to paradise (Falling Asleep of the Holy Mother of God)


💦ክርስቶስ የሰው ማንነት ከሌለው የሰው ልጅ አልዳነም ማለት ነው ምክንያቱም የሰው ማንነት ከአምላክ ጋር አንድ አልሆነምና የሰው ልጅ ደግም ማንነት ያለው ነው ማንነት ከሌለው ሰው አይደለም ማለት ነው ወይም ደግም የሰው ተፈጥሮ የሚቀነስ የሚጨመር ነው ማለት ነው ክርስቶስ የሰው ማንነት የለውም ከሚል ከአውጣኪ ምንፍቅና አራቁ 😁 ቅዱስ Gregory of Nazianzus እንዳለው የሰው ልጅ ድኅነትን ጎዶሎ የሚያደርግ ምንፍቅና ነው ሰው የዳነው ሥጋው ነው እንጂ ነፍሱ አልዳነችም ያስብላል

"Gregory of Nazianzus (c. 329–390)
Letter 101 to Cledonius: " ያላሰበውን አላዳነውምና። ነገር ግን ከአምላኩ ጋር አንድ የሆነው ደግሞ ይድናል. አዳም ግማሹ ብቻ ቢወድቅ፣ ክርስቶስ ወስዶ ያዳነው ደግሞ ግማሹ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ተፈጥሮው ሁሉ ቢወድቅ ከተፈጠረው ከባሕርይው ሁሉ ጋር አንድ መሆንና በአጠቃላይ ሊድን ይገባዋል።"

Oration 29 (The Third Theological Oration) "“በእግዚአብሔር መልክ የነበረው የባሪያን መልክ ያዘ፤ ባለ ጠጋውም ሀብቱን ለእኛ ያካፍል ዘንድ የኛን ሁሉ ወደ እርሱ ሰጠ ድሀ ሆነ። ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር መታሰብና መዳን እንዲያገኝ አስፈላጊ ነበርና። ትስጉት ማለት ይህ ነው፡ የሰው ተፈጥሮ ከፍ ከፍ ማለቱ ነው እንጂ የመለኮት ተፈጥሮ ተቀንሷል ማለት አይደለም።"


አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለ ታቦሩ ምሥጢር

"ጴጥሮስ ሆይ! የእግዚአብሔርን ልጅ ፤ እንደምን አልኽው? ፤ ለአንተስ የቀደመውን የአዳምን ደም ግባት አይተህ ከአዳም ሴት ልጅ ፣ በሥጋ በተወለደው ፣ 'በፊቱ ብርሃን' እየተደሰትህ በዚያ ትኖር ዘንድ በተሻለህ ነበር።

+ እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን የፊቱ መልክ በታቦር ተራራ ብርሃን በሆነው በእርሱ በጉንጮቹ በጥፊ መመታት ካልሆነ በቀር ፣ ቤተ ክርስቲያን በማን ፊት ትድን ነበር?

+ እናንተ በዚያ ከኖራችሁ በቀራንዮ ተራራ በመስቀል ላይ ለዓለም መዳን ማን እጁን ይቸነከር ነበር? ከማንስ ጎን የሕይወት ውኃ ወደ አዳም መቃብር ይፈስስ ነበር?

+ እናንተ በዚያ ከኖራችሁ ለሙታን ሕይወት ይሆን ዘንድ ማን በሥጋ ሞትን ይቀምስ ነበር? ማንስ የጻድቃንን ነፍሳት ከአንጦርጦስ ሊያወጣቸው ይችል ነበር?

+ እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን ጦርነትን ያደርግ ዘንድ ማን ከጨለማ ሠራዊት ጋር ለመዋጋት ይዘጋጅ ነበር? አሕዛብን ከጣዖት አምልኮ ይታደጋቸው ዘንድ በቤልሆር ሠራዊት ላይ ማን ጦረኛ ያስነሣ ነበር?

+ እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን ማን ቤተ ክርስቲያንን በአንተ ላይ ይሠራት ነበር? ምሰሶዎቿ ሐዋርያትን ፣ በሮቿ ነቢያትን ፣ ግድግዳዎቿ ሰማእታትንስ ማን ያቆም ነበር?

+ እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን ማን ሂዱና በዓለም ዳርቻዎች ሁሉ የመንግሥትን ወንጌል አስተምሩ ፤ ስታጠምቁአቸውም "በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ስም በሉ'  ብሎ ይልካችሁ ነበር?
                      
"ጌታችን በደብረ ታቦር የለበሰው ብርሃን ፣ የመለኮት ብርሃን አይደለም። የመለኮት ብርሃን የታየስ ቢሆን ምድርን ባነዋወጣት ፣ ባሕርን ባናወጻት ፣ ዓለምም እርሱን መቻል በተሳነው ነበር። ጌታ የለበሳት የብርሃን ጸዳል ግን አዳም ከኤዶም ገነት ውስጥ በነበረ ጊዜ የነበረችው ብርሃን ናት።"

         አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
(መጽሐፈ ምሥጢር ምዕ 30፥36 -


🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫

       ደብረ ታቦር በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


“እንግዲህስ ወደ ታቦር ተራራ ስለመውጣት ወደተናገሩ ወደ ወንጌላውያን ዜና ነገር እንመለስ፡፡ ማቴዎስ እንዲህ አለ፡- ከስድስት ቀን በኋላ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዟቸው ብቻቸውን ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደመብረቅ ብርሃን ነጭ ሆነ ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዮአቸው፡፡ (ማቴ 17፡1-8) ማርቆስ በስድስተኛው ቀን ጌታ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ወሰዳቸው ብቻቸውንም ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደመብረቅ አብለጨለጨ በምድር ላይ ሳሙና እንደዚያ አድርጎ ማንጻት እንደማይቻለው እንደበረዶ  ነጭ ሆነ፡፡ ሙሴና ኤልያስም ከጌታ ኢየሱስ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው አለ፡፡ (ማር 9፡2-8) ሉቃስም ከዚህም ነገር በኋላ በስምንተኛው ቀን ጌታ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዩሐንስንም ይዟቸው ሊጸልይ ወደተራራ ወጣ ሲጸልይም መልኩ ተለወጠ ልብሱም እንደመብረቅ ሆነ ከእነርሱም በክብር ተገልጠው በኢየሩሳሌም ይሆን ዘንድ ያለውን ክብሩን የተናገሩ ሙሴና ኤልያስ ናቸው፡፡ (ሉቃ 9፡28-31)

ማቴዎስና ማርቆስ አንድ ቃል ተናገሩ፡፡ በስድስተኛው ቀን ማለትም በአንድ በኩል በስድስተኛው ቀን ተብሎ ይተረጎማል ከዚህ በኋላ በስምንተኛው ቀን ማለትም ደግሞ ሌላ መንገድ አሳየ እንግዲህ ሉቃስ በመናገር ከወንድሞቹ (ከማቴዎስና ከማርቆስ) እንዴት ተለየ? ትርጓሜውን እንናገር፡፡ ማቴዎስ እና ማርቆስ በዕብራውያን በሮማውያን በወር መባቻ ተናገሩ ነሐሴ ስምንት ቀን በዕብራውያን ወሮች የአብ መግቢያ በሮሜም ወሮች የአውግስጦስ መግቢያ ነውና፡፡ ሰባቱን የነሐሴን ቀኖች ከተውኸው በዕብራውያን ወሮች ወደ ሐምሌ በሮሜም ወሮች ወደ መስከረም ይሆናል በአሥራ ሦስቱ ስድስት ከዕብራይስጥና ከሮማይስጥ ከመባቻ ስድስት ቀን ይቀርልሃል በሰርቅ አንድ ናቸው በወሮቻቸው ስም ግን በየአጠራራቸው ነው፡፡ ስለዚህም ሁለቱ ወንጌላውያን ጌታ ወደ ታቦር ተራራ ከመውጣቱ አስቀድሞ እውነት እውነት እላችኋለሁ ከዚህ ከቆሙት የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩት ድረስ ሞትን የማይቀምሱት አሉ ማለትን እንዳስቀደመ ተናገሩ፡፡ 

ማቴዎስና ማርቆስ በዕብራውያን አምስተኛ ወር መባቻ ወደ ታቦር ተራራ እስከወጡበት ድረስ ያሉት ቀኖች ቆጠሩ ስድስት ቀንም ሆነላቸው ስለዚህም በስድስተኛው ቀን ወሰዳቸው አሉ፡፡ ሉቃስም ጌታ ኢየሱስ በፊሊጶስ ዘቂሳሪያ አውራጃ እውነት እውነት እላችኋለው በዚህ ከቆሙት መካከል የእግዚአብሔርን መንግሥት ሳያዩ ሞትን የማይቀምሱ አሉ ካለበት ቀን ጀምሮ የፊቱ መልክ በታቦር ተራራ በጴጥሮስና በያዕቆብ በዮሐንስም ፊት ብርሃን እስከሆነበት ቀን ድረስ ያሉትን ቀኖች ቆጠረ፡፡ ስምንት ቀን ሆነለት፡፡ ስለዚህም ከዚህ ነገር በስምንተኛው ቀን ጴጥሮስንና ያዕቆብን ይዟቸው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ ሲጸልይም መልኩ ተለወጠ አለ፡፡

...ዳግመኛም ጌታችን በታቦር ተራራ ለምን ከነቢያት አንድ ድንግል ከሐዋርያትም ሁለት ደናግልን ከነቢያት ከነቢያት አንድ ያገባ ከሐዋርያትም አንድ ያገባ አመጣ አለቅነት ግን ባገቡት ዘንድ ጸና፡፡ ሙሴ የነቢያት አለቃ ጴጥሮስም የሐዋርያት አለቃ ነው ይህ ስለምን ሆነ? (ቢሉ) ደናግል ባገቡት ላይ እንዳይመኩ እግዚአብሔር በጥበቡ ያደረገው ሥርዓት ነውና፡፡ ምእመናንም ያገባ ኤጲስ ቆጶስ መሆን አይቻለውም እንዳይሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይህን ያደረገው የድንግልና ክብር አቃልሎ አይደለም የመመካትን ሸለፈት ከደናግል ልብ ያስወግድ ዘንድ ነው እንጂ እግዚአብሔር በድንግልናው ከሚመካ ድንግል ይልቅ ስለኃጢአቱ የሚያለቅሰውን አመንዝራ ይወዳልና፡፡ የመብራት ፈትል ያለ ዘይት በጾምና በጸሎት መትጋትስ ያለ የዋህነት  ቤተክርስቲያንንም መከተል ለድሆች ያለመራራት ድንግልናም ያለትህትና ምን ይጠቅማል፡፡ ስለ መመካትም ከአለቅነት ያራቃቸው በያዕቆብና በዮሐንስ ዓመፃ ተገኝቶ አይደለም፡፡ ዓመፃስ ቢኖርባቸው በእቅፍ ባላስቀመጣቸው ነበር ዘወትር ራስን ከፍ ያለማድረግ ትኖር ዘንድ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት ሠራላት እንጂ ድንግል የሆነውም ድንግል ባልሆነው ላይ እንዳይመካ፡፡ ድንግል ያልሆነው ጴጥሮስ በቀኖናው ትእዛዝ ዮሐንስን እንዳከበረው ድንግሉን በመላእክት ሥርዓት እንዲያየው ሥርዓት ሠራ፡፡”

👉 መጽሐፈ ምስጢር  30፡19-27


If anyone has put his trust in Him as a Man without a human mind, he is really bereft of mind, and quite unworthy of salvation. For that which He has not assumed He has not healed; but that which is united to His Godhead is also saved. If only half Adam fell, then that which Christ assumes and saves may be half also; but if the whole of his nature fell, it must be united to the whole nature of Him that was begotten, and so be saved as a whole. Let them not, then, begrudge us our complete salvation, or clothe the Savior only with bones and nerves and the portraiture of humanity. For if His Manhood is without soul, even the Arians admit this, that they may attribute His Passion to the Godhead, as that which gives motion to the body is also that which suffers. But if He has a soul, and yet is without a mind, how is He man, for man is not a mindless animal? And this would necessarily involve that while His form and tabernacle was human, His soul should be that of a horse or an ox, or some other of the brute creation. This, then, would be what He saves; and I have been deceived by the Truth, and led to boast of an honor which had been bestowed upon another. But if His Manhood is intellectual and nor without mind, let them cease to be thus really mindless. But, says such a one, the Godhead took the place of the human intellect. How does this touch me? For Godhead joined to flesh alone is not man, nor to soul alone, nor to both apart from intellect, which is the most essential part of man. Keep then the whole man, and mingle Godhead therewith, that you may benefit me in my completeness. But, he asserts, He could not contain two perfect natures. Not if you only look at Him in a bodily fashion. For a bushel measure will not hold two bushels, nor will the space of one body hold two or more bodies. But if you will look at what is mental and incorporeal, remember that I in my one personality can contain soul and reason and mind and the Holy Spirit; and before me this world, by which I mean the system of things visible and invisible, contained Father, Son, and Holy Ghost. For such is the nature of intellectual existences, that they can mingle with one another and with bodies, incorporeally and invisibly.

Gregory of Nazianzus, Epistle 101, 4th c. A.D.


ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሲባል ምን ማለት ነው?

በዚህ ርዕስ ዙሪያ የሚያስቁ የተለያዩ ሀሳቦችን አይቻለሁ።

1ኛ. ባሕርይን እንጅ አካልን አልተካፈለም የሚልና
2ኛው .የመለኮቱ አካል (ሎጎስ) ሰው ለመሆን የጎደለው የሰው አካል ሳይሆን የሰው ባህሪ ነበር። የሚሉ አሰቂኝ ቀልዶች😁

ሲጀመር በየትኛውም መንገድ አካል ሳይኖር
ባሕርይው ሊኖር አይችልም እስትንፋስ ያለውም ይሁን የሌለውም።
‹አካል ሲባል ግዙፍም ሆነ ረቂቅ የባሕርይ መገለጫ ነው፤ ባሕርይ ሲባል ግዙፍም ሆነ ረቂቅ የአካል መገኛ መሠረት ነው፡፡

ስለሰው ባሕርይ ስናወራ ስለ ሥጋ ብቻ አይደለም ስለ ነፍስ ብቻ አይደለም የሰው ባሐርይ የነፍስና ሥጋ አንድ በመሆን የተገኘ ነው ከሁለቱ አንዱ ከጎደለ የሰው ባሕርይ አይደለም ሰው የሚባለው የሥጋና ነፍስ ተዋሕደው አንድ በመሆን ያስገኙት እንጅ ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሥጋና ነፍስን እደነሣ ነው የምናምነው ወይ ነፍስ ከእናትና አባት አትከፈልም ብለው ከሚያመኑት ወይም ደግሞ ለክርስቶስ በነፍስ ፈንታ መለኮት ሆነው ከሚሉት ወገን ካልሆን በስተቀር። የሰው ባሕርይ ከእንስሳት የሚለየው ሕያው የሆነች የማትሞት ነፍስ ስላለችው ነው ። ክርስቶስ ባሕሪያችን ነሣ ስንል ሥጋችንም ነፍሳችንም ነሣ ማለታችን ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም እኔ የምትል ነፍስን ከድንግል ማርያም ተካፍሏል  ከባሕርይ ባሕርይን ሲካፈል ከድንግል እኔነት እኔነትን ተካፍሏል ።
እኛ ሰዎች ባሕርይን ከእናትና አባታችን ስንካፈል አካልን ተካፈልን ማለት ነው ። እኔነትን ከእናትና አባታችን በተከፍሎ የምናገኘው እንጅ ከየትም የመጣ አይደለም ። ስለዚህ ክርስቶስ ስንል ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው ። ስለዚህ ቃል ሰው ከመሆኑ በፊት ሰዋዊ ባሕርይ እንዳልነበረው ሁሉ ሰዋዊ አካል(እኔነት የለውም) ሰው ሲሆን ግን የእርሱ ያልነበረውን የሰውን ባሕርይ ገንዘቡ ሲያደርግ የእርሱ ያልነበረውን እኔነትም ገንዘቡ አድርጓል ። ስለዚህ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ ነው እንደማንለው ሁሉ ሁለት እኔነትም አንለውም የሰውነት እኔነት ከመለኮት እኔነት በተዋሕዶ አንድ ሆኑ እንል አለን እንጅ ። ስለዚህ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ስንል ከድንግል ማርያም የተካፈለውን ባሕርይና የመለኮትን ባሕርይ ማለታችን እንደሆነ ሁሉ ከሁለት አካልም ስንል እንደሁ ነው የሰውነት እኔነት በተከፍሎ  የሚገኝ ነው።

@felgehaggnew


እናታችንም ቤተ ክርስቲያን በረድኤተ እግዚአብሔር ጥላ ሥር ጸንታ ትኖራለች፡፡ አቤቱ በረድኤት ጥላ ሥር ጸንቶ የሚኖር ማን ነው? መቅደስህም በተሠራበት ቦታ አድሮ የሚኖር ማነው? ተብሎ እንደተጻፈ በሙሽራዋ ክርስቶስ ደስ እያላት የወልድን ኀይል አምና በምእመናን ፀንታ ትኖራለች፡፡ ቀኝ ክንዱ ታቅፈዋለች ግራ ክንዱም ከራሴ በታች ናት ተብሎ እንደተጻፈ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃንነት ወደ ገነት ዓፀዶች ትመራለች፡፡ መንፈሰ ረድኤትህ መርቶ ወደ ምድረ ጽድቅ ያድርሰኝ ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ /መዝ.14፥1/
ከዚህም በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅን ስትፈልግ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ትመለሳለች፤ በዮርዳኖስ ወንዝ ለልጁ በመሰከረ በእግዚአብሔር አብ ስም አንድ ጊዜ ትጠመቅ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ትወርዳለች፡፡ ዳግመኛም በዘካርያስ ልጅ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ በእግዚአብሔር ወልድ ስም ትጠመቅ ዘንድ ሁለተኛ ትወርዳለች፡፡ ዳግመኛም በዘካርያስ ልጅ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ በእግዚአብሔር ወልድ ስም ትጠመቅ ዘንድ ሁለተኛ ትወርዳለች የርግብ መልክ ባለው አካል አምሳል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በተቀመጠ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ሦስተኛ ትጠመቃለች፡፡
ከዚህም በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ ወጥታ አመተ ክርስቶስ ትባል ዘንድ ቅብዓ ሜሮንን ተቀብታ ማዕተበ ክርስትናን ገንዘብ ታደርጋለች፡፡ ቅብዓ ሜሮን የሃይማኖት ኀይል ነውና ሐዋርያት በዲዲስቅልያ መጽሐፋቸው እንደገለጹት በጥምቀት የተወለደ ሰው አምላክ ከድንግል የተወለደውን ልደት ይመስላል፤ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም እንደተወለደ ከርሷም ከተወለደ በኋላ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ተገኘ፡፡
በጥምቀት የተወለደ ሰውም እንደዚሁ ነው ከውኃውም ከወጣ በኋላ ወደ ጥምቀተ ባሕር የገባበትና የወጣበት ምልክቱ አይገኝም፤ መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው ተብሎ በመዝሙረ ዳዊት እንደተነገረ ዱካህም ከጥልቅ ውኃ ውስጥ ነው ፍለጋህም አይታወቅም፡፡
ወደ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አርእስተ ነገር እንመለስ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰላም የተሰበከላችሁን የወንጌል ኀይል ተጫምታችሁ ያለውን ቃል ሰምታ የወንጌልን ቃል ጫማ በመጫማት አካሔዷን አሳምራ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገባለች ኤፌ.6፥15 በራሷም ላይ የዕንቊን ዘውድ ትቀዳጃለች ይኸውም የሃይማኖት አክሊል ነው ዳግመኛም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በራሳችሁ ላይ የሚያድነውን የራኀስ ቊር ድፉ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ በእጃችሁ ያዙ ይሄውም የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ እንደተናገረ፡፡ ኤፌ.6፥17 በጣቶቿ ላይም የክብር ቀለበትን ታደርጋለች ይሔውም የድኅነት ምልክት የሆነ የክብር ማዕተብ ነው፡፡
ከዚህም በኋላ አብርሃም ወዳለባት ይስሐቅም በበግ መሥዋዕትነት ወደ ዳነባት ከምድር እስከ ሰማይ ድረስ የእግዚአብሔር መላእክትም ሲወጡባትና ሲወርዱባት ያዕቆብ ባያት የወርቅ መሰላል ወደ ሙሸራው አዳራሽ ትገባለች፤ በእስራኤል ልጆች በደል ምክንያት ምስክር የሚሆኑ ሕግና ትእዛዝ የተጻፈባት ሙሴ የተሸከማት ጽላት ናት መልከጼዴቅም የቤተ ክርስቲያንን ምሥጢረ ቊርባን ሥርዐት የሚገልጽ የኅብስትና የወይን ግብር ያቀረበባት ናት ዘፍ.14፥18
ዳዊትም አቤቱ አንተ ታቦትህን ይዘህ ወደምታርፍባት ቦታ ተነሥ፡፡ እያለ የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈባት ታቦት ተነሥ፤ እያለ የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈባት ታቦት ፊት ምስጋና ያቀረበባት ናት አሳፍ የተቀኘላት፣ የቆሬ ልጆችም በምስጋና መሰንቆዎች የሚዘመሩላት የቆሬ ልጆችም በምስጋና መሰንቆዎች የሚዘምሩላት ናት፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ዐለቱን ሰንጥቆ የደብተራ ኦሪቱን ንዋየ ቅድሳት ያስቀመጠባት፣ የተሠነጠቀችውን ዐለት መልሶ እንደነበረችው ያደረጋት፣ እንደ ብረት መዝጊያም የሆነችለት፣ ቁልፎቿንም ለፀሐይ አደራ የሰጠባት ናት፡፡ መዝ.131፥8፣ ተረፈ ኤር.83፥18
ኤልያስ መልአኩ ያቀረበለትን የተዘጋጀ ኅብስት የበላባት፣ በተመገበው ምግብ ኀይልም ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት የተጓዘባት ናት፡፡ ዕዝራ ሱቱኤል መጻሕፍተ ብሉያትን የምታሳውቀውን ከመልአኩ ዑራኤል እጅ ተቀብሎ የምስጋና ጽዋን የጠጣባት፣ አእምሮውም በዕውቀት ተሞልቶ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት ብሉያትን አፉ ከመናገር ሳያቋርጥ የቆየባት ናት፡፡ /1ነገ.19፥5-8 ዕ.ሱ.3 40/ ዘካርያስ ነጫጭና ጥርኝ ፈረሶችን ያየባት ናት፡፡ ዘካ.1፥8
ዳንኤልም የእሳት ሠረገላን ያየባት ናት፤ ዘመናት የማይወስኑት አምላክ ከሰው ልጅ ጋር ከበላያቸው ላይ የተቀመጠባቸውን ዙፋኖች ዳንኤል ያየባት ናት፤ ዕንባቆም በሁለቱ እንስሳት መካከል እግዚአብሔርን ያየባት ነቢያትም ሁሉ ደስ የሚያሰኝ ድምጽ የትንቢት ምስጋናን የሚያሰሙባት ናት፡፡ የገሊላ ሕፃናትም ኅሊናን የሚመስጥ፣ ልቡናን የሚማርክ፣ አጥንትን የሚያለመልመውን ማኅሌታዊ ምስጋናን የሚያመሰግኑባት ናት፡፡ ዳን.7፥9፣ ዕን.3፥2
ጴጥሮስ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ የተቀበለባት፤ ጳውሎስም የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ይሆን ዘንድ የተጠራባት፤ ዮሐንስም እንደነጋሪት ድምጽ እያሰማ ምሥጢረ መለኮትን የሰበከላት፤ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን በአምሳለ እሳት የተቀበሉባት ናት፡፡ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት የሚያቀርቡበትን መንበረ ታቦት ለመጐብኘት ማኅበረ መላእክት የሚፈሯት ማኅበረ ሰማዕታትም የመከራቸውን ዋጋ ተቀብለው የክብር አክሊልን የሚቀዳጁባት ናት፡፡
ከዚህም በኋላ በሙሽራይቱ መጋረጃ ውስጥ ለምእመናን ምሳ ይሆን ዘንድ ሙሽራው ይሠዋባታል፤ መሥዋዕቱንም ከማየቷ የተነሣ ጉልበቶቿ ይብረከረካሉ፤ በደሙ ጽዋ ውስጥ ደሙ ሲንጠፈጠፍ ባየችም ጊዜ አንጀቷ ይላወሳል፤ ሥጋውን በፍርሃት፤ ትበላለች ደሙንም በመንቀጥቀጥ ትጠጣለች፤ ከዚህም በኋላ የሃይማኖት ነበልባል በልቡናዋ ውስጥ ይቀጣጠላል፤ ከሆዷም ውስጥ የፍቅር ሞገድ ይናወጣል፡፡ (መጽሐፈ ምሥጢር ከሚባለው ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ድርሰት የተወሰደ)


ወንድሞችና እህቶች እየሞላችሁ አይደለም

Показано 20 последних публикаций.