🍁የኔና የሀቢብ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ 🍁
ምዕራፍ ሁለት
#ክፍል_7✨
ፀሀፊ✍ #yuti
ድጋሚ ስህተት መስራት አልፈልግም ግን ደሞ እንጃ ግራ ተጋብቻለው መወሰን አልቻልኩም ላምነውም አልቻልኩም እስኪ የሚሆነውን እናያለን
🧕 ፦ አሁን ለኔ መንገሩ ለምን አስፈለገ ሲጀመር አይመለከተኝም
👨🦱 ፦ ሀዩ በአላህ ፊት አትንሺኝ በቃ እኔ ከምር ራሴን በፀፀት መቅጣት አስጠልቶኛል
🧕 ፦ ለዛ አረፈድክ አሁን ያንተ መፀፀት ለኔ የሚያመጣው ለውጥ የለም ከቻልክ ተወኝ ብታየኝም ወደኔ አትቅረብ ልታወራኝም አትሞክር ያለበለዚያ ደስ አይልም መጨረሻው
👨🦱 ፦ ይቅርታን ያስተማርሽኝ አንቺ ነበርሽ ይቅር ማለትን የተማርኩት ካንቺ ነው እኮ ሀዬ
🧕 ፦ ታድያ ያማለትኮ አንተ አስሬ ሰብረከኝ መተህ ይቅርታ ስትለኝ እኔም ችግር የለውም እልሃለው ማለት አይደለም ሰህተት ሳናውቅ የምንሰራው ነው እንጂ እንዳንተ አስበን ለመጎዳት ያረግነው ነገር ስህተት አይደለም ደሞ ዛሬ ይቅር ብልህ ነገ እሷ መታ ይቅርታ ብላ ብታለቅስብህ እንደለመድከው ይቅር ትላትና መልሰህ እኔኑ መጉዳት ትጀምራለህ ያንን ደሞ እኔ አልቀበልም ምን ያህል እንደሰበርከኝ ብታውቅ አላህ ምስክሬ ነው ፊትህን እንኳ ለኔ ለማሳየት ባልደፈርክ ነበር አሁን እንደትከተለኝ በቃ መልካም ቀን
እኔን ለመከተል ድፍረት እንኳ አላገኘም አቀርቅሮ ከመቆም ውጪ ንግግሬ ሊጎዳው ይችል ይሆናል ግን እኔ ደሞ ያንን ለመረዳት እንኳ አቅሙ አልነበረኝም በጣም ተጎድቻለው አሁንም አንድ አይነት ስህተት መስራት አልፈልግም ከዛ በዋላ ሁሌም ሲያገኘኝ ይቅርታ እንዳለኝ ነው ሁሌም በእህቴ ደብዳቤ ይልካል አስሬ ይደውላል ሲጨንቀኝ አነሳሁለት
🧕 ፦ ቆይ ግን በአላህ ለምን አተወኝም ምን አርጊ ነው የምትለኝ አይሰለችህም እንዴ በቃ ተወኝ
👨🦱 ፦ ሰላምታ አይቀድምም ሀዩ
🧕 ፦ አሰላሙ ዋአለይኩም
👨🦱 ፦ ዋአለይኩም አሰላም😊
🧕 ፦ ጨረስክ አይደል ሰላምታውን አሁን ወደ ጉዳይህ ምን ፈለክ
👨🦱 ፦ እንዴት ነሽ ሀዩቲ ወላሂ ናፍቀሽኝ ነው አሁን ነው የገባኝ ላንቺ ያለኝን ስሜት ከረፈደ ቢሆንም ደስ ብሎኛል
🧕 ፦ ድሮ ቢሆን ይሄ ቃልህ ለኔ ከምግብ ከውሃ በላይ ነበር አሁን ግን ከስድብ አይተናነስም ለኔ
👨🦱 ፦ ይገርማል አንድም ቀን እኔም በተራዬ እዲህ እለምንሻለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ወላሂ
🧕 ፦ የራስህ ጉዳይ ተወኝ በቃ ቻው
👨🦱 ፦ ወላሂ ሀዩ ብዘጊው ቤት ድረስ መጥቼ ነው ገብቼ በሁሚ ፊት የማናግርሽ
🧕 ፦ ምን😳
◆◆✨✨ይቀጥላል ✨✨◆◆
የኔና የሀቢብ ታሪክ እያለቀ ስለሆነ ነው ቶሎቶሎ የማልቅላችሁ 🙏 እንዲውልጊዜው አንብባችሁ ስትጨርሱ #like_እንዳይረሳ
@all_love_world @yuti_Hijab_girl