አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ።
ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ
እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ዩሱፍ አልዐይደሩስ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: ዐብዱረሒም
👌እንዲህ ነበር የሰለምኩት.pdf
4.8Мб
2ኛ ከለርድ እትም

ከተወሰነ ጭማሪጋ

የተዳሰሱ ርዕሶች

👉 ሕይወቴ በጴንጤ ዓለም ሳለሁ

👉 ሐይማኖት አልባነት

👉 እንዲህ ነበር የሰለምኩት

👉 ከሰለምኩ ኋላ

👉 ያቺ ጉደኛ ምሽት

👉 መንግስተ ሰማይና ገሀነም ደርሰን መጣን ያሉ ትናንሽ ደጃሎችና
ወዘተ

https://t.me/Abuenqurarit


ኡስታዝ  ኢብኑ  ሙነወር

ሁሉም ነብስ ሞትን ቀማሽ ናት!
ለሞት መዘጋጀት

   t.me/NABAWITUBE


Репост из: DARU-TAUHEED(ዳሩ-ተውሒድ)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጣፋጭ ቲላዋ ከኡለማዎች አንደበት

   🎙 በሸይኽ ሱለይማን አል-ሩሓይሊ  ሓፊዘሁላህ

           ~ t.me/Darutewhide


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሶላት የረሳ ሰው ሲያስታውስ ይሰግዳል። የመጀመሪያውን በማስቀደም ቅደም ተከተሉን ይጠብቃል። ለምሳሌ ዙህርን ረስቶ የዐስር ወቅት ከገባ በኋላ ቢያስታውስ መጀመሪያ ዙህርን ይሰግዳል። ከዚያ ዐስርን ያስከትላል።
ዐስርን መስገድ ከጀመረ በኋላ ካስታወሰ ግን የጀመረውን ያጠናቅና ከዚያ ዙህርን ይሰግዳል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: [] مركز أبي موسى الأشعري []
አስቸኳይ ማስታወቂያ


መረከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዓሪ ለአዳሪ የቁርአን ሒፍዝ ፕሮግራም ኡስታዞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል  ።

ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1, ቁርአንን መርከዝ ዉስጥ በጥሩ ተጅዊድ እና ሙራጅዓ የሀፈዘ ::
2, የቁርአን ሽሀዳ ያለውና መርከዝ ዉስጥ አስተምሮ የሚያዉቅ ::
3, መሰረታዊ የተጅዊድ ህግጋቶች ላይ ግንዛቤ ኖሮት ማስተማር የሚችል ።
4, የስለፊያን ዳዕዋ የተረዳ, ኪታቦችን የቀራና የ ማስተማር ልምድ ያለው ።
5,  ለተማሪዎች በሁለንተናው ጥሩ አርአያ መሆን የሚችል እና የማስተማር ልምድ ያለው
6,  እድሜው ከ 23 ዓመት በላይ የሆነ ::

7, ብዛት : 2

እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ከታች ባለው ዩዘር ኔም ያናግረን ።⤵️⤵️⤵️

📞 0930547776

@AbulAbasNasirMuhammed




Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሸይኽ ዐብዱልከሪም አልኹዶይር እንዲህ ይላሉ፦
"ልብ ሳይገነዘብ እንዲሁ በምላስ ጫፍ የሚፈፀሙ ዚክሮች ይጠቅማሉ። ነገር ግን ምላስ ከልብ ጋር የተዋሀዱባቸው ዚክሮች የሚኖራቸውን ያክል ውጤትና ምንዳ አይኖራቸውም።" [አተዕሊቃቱ ሰኒያህ፡ 116]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ርብርብ ነው! ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የሚችለውን እያደረገ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱን ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለኣኺራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል ፉርቃን በወረባቦ ወረዳ ዋና ከተማ ቢስቲማ ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለከተማው ድምቀት ነው። ከዚያ በላይ ግን ለከተማውም በዙሪያው ላሉ ቀበሌዎችም ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።

መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ወረባቦ ፉርቃን መስጂድ
ንግድ ባንክ - 1000401221957
አቢሲኒያ - 64828638
ዳሽን - 2935824167011

መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor






Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Репост из: Ibnu Hashim(امير هاشم)
ሁድሁድ የተሰኘው የአዕዋፍ ዝርያ ዜና ሲያስተላልፍ ዲሲፕሊን በተሞላበት መልኩ ነበር። «ሰማሁኝ ወይም ይላሉ» የሚሉ ገለጻዎችን በጭራሽ አይጠቀምም። ለነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) (وَجِئْتُكَ مِن سَبَإٍۭ بِنَبَإٍۢ يَقِينٍ) «ከሰበእም እርግጠኛ የሆነን መረጃ አመጣሁልህ» አላቸው።

ግና ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ሁድሁድ በእርሳቸው ላይ ለመዋሸት ቅንጣት እንደማይደፍር እርግጠኛ ቢሆኑም እንኳ እንደኛ መረጃን በንፋስ ፍጥነት ኮፒ ፔስት ለማድረግ አልቸኮሉም። ይልቅ ምላሽ የሰጡት

(سَنَنظُرُ أَصَدَقْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْكَٰذِبِينَ)
« ያልከው እውነት መሆኑን ወይም ከዋሾዎች መሆንህን በቅርቡ እናያለን» በማለት ነበር።

መረጃን ግራ ቀኝ ተመልክቶ ማረጋገጥ ሸሪዓዊ መስፈርት እና ነብያዊ ስልት ነው። እርግጠኛ ያልሆንክበትን ነገር ከማሰራጨት መቆጠብ ትርፍ ባታገኝበት እንኳ አትከስርም።

t.me/IbnuHashm








Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ተጠንቀቅ! ደካማ አያልቅስብህ
~
በጉልበትህ፣ በስልጣንህ፣ በወገንህ፣ በሃብትህ፣ ... ተማምነህ ሰዎችን አትግፋ። "ጌታዬ! እኔ አቅም የለኝም፣ አንተ ፍረደኝ!" ብሎ ሰው ካለቀሰብህ ወላሂ ወዮልህ! ያኔ እርቃንህን ብቻህን ከአላህ ፊት ለምርመራ ስትቀርብ ምን ይውጥሀል?! ያኔ ዛሬ የተመካህበት ጉልበት ይከዳሀል። ያኔ ዛሬ የጠገብክበት ስልጣን ያዋርድሃል። "ምነው በቀረብኝ?!" ትላለህ። ያኔ ዛሬ የተመካህበት ዘመድና ወገን ጥሎህ ይሸሻል።
{ فَإِذَا جَاۤءَتِ ٱلصَّاۤخَّةُ (33) یَوۡمَ یَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِیهِ (34) وَأُمِّهِۦ وَأَبِیهِ (35) وَصَـٰحِبَتِهِۦ وَبَنِیهِ (36) لِكُلِّ ٱمۡرِئࣲ مِّنۡهُمۡ یَوۡمَىِٕذࣲ شَأۡنࣱ یُغۡنِیهِ (37) }
"አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ ከእናቱም ከአባቱም፤ ከሚስቱም ከልጁም እንዲሁ። ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ሁነታ አልለው።" [0በሰ፡ 33-37]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor



Показано 20 последних публикаций.