Репост из: University of Gondar (UoG)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዩኒቨርሰቲያችን የ2015 ዓ.ም የ ኸልት ፕራይዝ ውድድርን አካሔደ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ኸልት ፕራይዝ/ሽልማት (Hult Prize) - የዩኒቨርሲቲ ቅደመ-ምረቃ (Under Graduate) ተማሪዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በአዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እና ቴክኖሎጂዎች እንዲወዳደሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ብሎም በፋይናንስ በማገዝ ወደ ተግባር/ ምርት እንዲገቡ ማድረግን ዓለማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ፕሮጀክት እንደሆነ ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
የዘንድሮው የ2015 ዓ.ም የኸልት ሽልማት ‘ፋሽን ኢንዱስትሪ/Redesigning Fashion Industry’ ላይ በዋናነት ትኩረት ያደረገ ሲሆን ዩኒቨርሰቲያችንን ጨምሮ የሀገራችን 10 ዩኒቨርሲቲወች በዚሁ የኸልት ሽልማት ውድድር ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
የየዩኒቨርሲቲዎች አሸናፊዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተወዳደሩ በኋላ አሸናፊዎች በአህጉር አቀፍ - በአፍሪካ ደረጃ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
በመጨረሻም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድረው አሸናፊ የሚሆኑ የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች የ አንድ ሚሊዮን የአሚሪካ ዶላር ተሸላሚ የሚሆኑ ይሆናል፡፡
ስለሆነም ይህንን እድል ለመጠቀም በዩኒቨርሲቲያችን በተለያዩ ዙሮች ሲወዳደሩ የቆዩ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ዛሬ የካቲት 25/2015 ዓ.ም የኸልት ሽልማት የፍጻሜ ውድድራቸውን በዩኒቨርሰቲው አሉምንየም አዳረሽ አካሂደዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ደሊቨረሎጂ/ውጤታማ ስራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር አራጋው እሸቴ (መርሀ-ግብሩን በንግግር የከፈቱ)፣ የዩኒቨርሰቲው ነርቸር ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ታደሰ (መርሀ-ግብሩ ላይ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉ) እንዲሁም ከተለያዩ ት/ት ክፍሎች የመጡ የቴክኖሎጅና የፈጠራ መምህራን (በዳኝነት የተሳተፉ) የዕለቱን መርሀ ግብር ታድመዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩ መሰረትም ሁሉም ተወዳዳሪ ተማሪዎች ስለ ፈጠራና ስለ ቴክኖሎጂ ስራዎቻቸው ለዳኞች በገለጻ ካስረዱ በኋላ ያረጁ ልብሶችን ወደ አዲስነት የሚቀይር የፈጠራ ቴክኖሎጅን ይዞ የመጣው ‘አድስ ፋሽን’ የፈጠራ ቡድን በአንደኝነት ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ለአዲስ ፋሽን የፈጠራ ቡድንና ለሌሎች ተሳታፊዎች እንደየ ቅደም ተከተላቸው የማበረታቻ ሽልማትና የዕውቅና ሰርቲፊኬት ተሸልመዋል፡፡ ለውድድሩ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አጋር አካላትም የምስጋና ሰርቲፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው በዚህ ውድድር ከ1ኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ የዩቨርሲቲያችን ተማሪዎች በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሔደው የዩኒቨርሲቲ ተማርዎች ዓለም ዓቀፍ የኸልት ሽልማት ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
እኛም ለዩኒቨርሰቲያችን ተማሪዎች ከወዲሁ መልካም ምኞትን እየተመኘን በዚህ ዓመት በተለያየ ምክንያት እድሉን ያልተጠቀማችሁ የዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች፣ ከዚህ በኋላ ባሉት ውድድሮች በመሳተፍ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጥኖቻችሁን/ሀሳቦቻችሁን እውን ታደርጉ ዘንድ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ለልህቅት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
የካቲት 25/2015 ዓ.ም