አላህ በቁርኣኑ ከጠቀሣቸው ነፍሣትና እንሠሣት ምን ምን ትምህርት እንወስዳለን?
https://t.me/iqraknow/1794
ነሕል (ንብ) ፡ (አን-ነሕል ቁ - 68)
ዕረፍት የሌለው ትንሹ ነፍሣት ሁሌም ሲደክም ይታያል፡፡ ንፁህ እና ፅዱ አካባቢ ይውላል፡፡ ሐላል ይሠራል፤ ሌሎችንም ሐላል ነገር ይመግባል፡፡ አላህ ወደ መልካም ሥራ መራው፡፡ ከሆዱም ለሰው ልጅ ለመድሃኒትነትና ለምግብነት የሚያገለግል ጣፋጭ ማርን አወጣ። በቅዱስ ቁርኣኑም ምሣሌ አደረገው፡፡ በስሙም እስከ ዕለተ ቂያማ የሚነበብ አንድ ምዕራፍ ‹ሱረቱ ነሕል› በማለት አወረደ ።
ከንብ እነኚህን ትምህርቶች ተማር -
~ካገኙት ነገር ሁሉ የላብ ውጤት ይጣፍጣል፣
~ጥሩ ሥራ ጥሩ ብላ፣
~በሥራና በፀባይህ ልስላላሴ ይኑርህ፡፡
~ ለራስህ ብቻ አስበህ ሌሎችን እንዳትጎዳ፣
~ በጥቅምህ ለሌሎችም ትረፍ፡፡
ስለ ንብ አስገራሚ ነገር ለማወቅ ይህን ተጭነው ያንብቡ ይገረማሉ☞ https://t.me/iqraknow/1794
በምድራችን ላይ ከ20,000 በላይ የታወቁ የንብ ዝርያዎች ሲኖሩ እነዚህም በዘጠኝ ታዋቂ ቤተሰቦች ተከፋፍለዋል፤ ምን አለፋን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ዝርያዎች ሊኖሯቸውም ይችላል።
ንብ የራሷን ቤቶች የምትሰራው ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ነው፤ ይህንን ሥርአት በደመነፍስ (አረብኛ ዋሂ) ያሳወቃት ንድፍ አውጪው አምላካችን አላህ መሆኑ በቁራን ይጠቀሳል፦ 16፥68 *ጌታህም ወደ ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ *"ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ"*፡፡
وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ
ንብ አበባዎች ባሉበት ሁሉ ትገኛለች፤ የንብ አካላቷ በሦስት ክፍል ይከፈላል፤
አንደኛው ክፍል የምታሸትበት፣ የምትዳስስበት፤ የምትሰግበት፣ በግንባሯ በስተቀኝና በስተግራ ሁለት ቀጫጭን ነገሮች እንደ ቀንድ የሆኑ አሏት፤ ደግሞ በዚህ በገጿ ላይ ሁለት ትልልቅ ጠፍጣፋ ዓይኖች በግራና በቀኝ ሆነው ለማየት የሚያስችሏት በሌሎች ትንንሽ ዓይኖች የተሞሉ አሏት።
ሁለተኛው ክፍል የአካሏ ክፍል ፀጉራሞች የሆኑ በአበባ ውስጥ ያለውን ኔክታር ማለትም ፈሳሽ ነገር ስትመጥ የአበባ ዱቄት የምታመጣባቸው ስድስት እግሮች፣ ሁለት ወፈር ያሉ ክንፎችና ሌሎች ሁለት ሳሳ ያሉ ክንፎች በጠንካሮች ሥር የሆኑ አሏት።
በሦስተኛው የአካላት ክፍሏ እንደ አንጓ ክርክር ያላቸው መተንፈሻዎች የምትነድፍበትና የተበላሸውን የምታስወጣበት አሏት።[1] ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ምግቧን ትብላለች፤ ይህንን የተፈጥሮ ሥርአት የነደፈላት አምላካችን አላህ ነው፦ 16፥69 «ከዚያም *ከ*ፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡
ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ الثَّمَرَات
"ፍሬዎች" በሚለው ቃል ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መግባቱ ከፍሬዎች ሁሉ መካከል መብላቷን ያሳያል እንጂ ፍሬዎችን ሁሉ አያሳይም።
ንብ ወለላን ቱቦ በመሰለው ምላሷ ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ቅሥም አውላ እየቀሰመች በሆዷ ውስጥ ባለ የማር ቋት ውስጥ ታጠራቅማለች፤ አምላካችን አላህ፦ "ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል" የሚለው ይህንኑ ነው፤ ከዚያም ተሸክማ ወደ ወደ ቀፎዋ ትወስደዋለች፤ ቀጥሎም ፈሳሽ የአበባ ወለላውን ወደ ሌሎች ንቦች ታዘዋውረዋለች፤ ወለላውን በአፏ ውስጥ ካሉት እጢዎች ከሚመነጭ ኢንዛይም ጋር እያዋሐደች ለአንድ ሰዓት ከግማሽ ያህል ታላምጠዋለች፤ ከዚያም ከሰም በተሠሩ ባለ ስድስት ማዕዘን ክፍሎች ውስጥ ታስቀምጥና እርጥበቱ እንዲተን በክንፎቿ ታራግባለች፤ የውኃው መጠን ከ18 በመቶ በታች ሲሆን ክፍሎቹን በሰም በስሱ ትሸፍነዋለች፤ በዚህ መልኩ የተሸፈነ ማር ሳይበላሽ ለዘመናት ሊቆይ ይችላል።
ይህ ማር ምግብ ከመሆኑም ባሻገር በቫይታሚን ቢ፣ በተለያዩ ማዕድናት እና አንቲኦክሲደንትስ በተባሉ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ መድኃኒት ነው፤ ማር ቁስልን፣ የተቃጠለ የአካል ክፍልን፣ የዓይን ቆዳ መሸብሸብን እና በቆዳ ላይ የሚወጣ ቁስልን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የጤና ችግሮችን ለማከም ዛሬ አገልግሎት ላይ ይውላል፤ ንብ በአበባ ፈሳሹ ላይ ኢንዛይም ስለምትረጭ ማር ለስለስ ያለ የፀረ ባክቴሪያነትና አንቲባዮቲክነት ባሕርይ እንዳለው ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህንን ያገራላት አምላካችን አላህ ነው፤ በማር ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት እና ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት፦ 16፥69
*የጌታሽንም መንገዶች ላንቺ የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት*፡፡ فَاسْلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا ۚ يَخْرُجُ مِن بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ فِيهِ شِفَاءٌ لِّلنَّاسِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ