…ልዩነቱ ምንድነው ???
بسم الله الرحمن الرحيم
الفرق بين قيام الليل وصلاة التراويح والتهجد
📩 #السؤال :
ما الفرق بين صلاة التراويح والقيام والتهجد؟ أفتونا مأجورين.
ጥያቄ ፦
በ“ሰላተ ተራዊሕ” በ“ቂያመ ለይል” እና በ“ተሀጁድ” መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው ?
አላህ ይመንዳዎና ምላሹን ይስጡን።
📋 #الجواب :
الصلاة في الليل تُسمَّى تهجدًا ، وتُسمَّى قيام الليل ؛ كما قال الله تعالى : { وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَكَ [الإسراء: 79] ، وقال سبحانه : {يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا }. [المزمل: 1-2] ، وقال سبحانه عن عباده المتقين : { آخِذِينَ مَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَلِكَ مُحْسِنِينَ كَانُوا قَلِيلًا مِنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ } . [الذاريات: 16-17].
#أما_التراويح : فهي تُطلق عند العلماء على قيام الليل في رمضان أول الليل مع مراعاة التَّخفيف وعدم الإطالة ، ويجوز أن تُسمَّى تهجدًا ، وأن تُسمَّى قيامًا لليل ، ولا مشاحة في ذلك. والله الموفق.
📚 مجموع الفتاوى لسماحة الشيخ عبد العزيز بـن بـاز رحمه الله
መልስ ፦
❤ በለሊት ውስጥ (የሚሰገድ) ሰላት “ተሀጁድ” ወይም “ቂያመ ለይል” ተብሎ ይሰየማል።
ከፍ ያለው አላህ እንዳለው ፦
👉 « ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡ »
[አል–ኢስራ (78)]
ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ይላል ፦
👉 « አንተ ተከናናቢው ሆይ፡፡
ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤
(ስገደ)፡፡ግማሹን (ቁም) ፤ ወይም ከርሱ ጥቂትን ቀንስ፡፡ ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፡፡ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡ »
[አል–ሙዘሚል 1፥4]
ጥራት የተገባው አላህ ፈሪ የሆኑትን ባሪያዎቹ አስመልክቶ እንዲህ ይላል ፦
👉 « አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው ፤ (በገነት ውስጥ ይኾናሉ)፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና፡፡
ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡
በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ »
[አል–ዛሪያት 15፥18]
👉 “ሰላተ ተራዊሕ” ከሆነ ዑለማዎች ዘንድ በረመዳን ወር የመጀመሪያው ሌሊት ላይ ቀለል ማድረግን ከመጠባበቅ ጋርና ካለማርዘም ጋር የምትሰገድ (ስትሆን) “ቂያመ ለይል” በሚል ስያሜ ልቅ ትደረጋለች።
(ትገለፃለች።)
👉 "ተሀጁድ" ተብላ ልትሰየምም ትችላለች። “ቂያመ ለይል”
(የሌሊት ሰላት) በሚል
ልትሰየምም ትችላለች።
👉 በዚህ ነገር ላይ ጭቅጭቅ የለውም !!!
ትክክለኛውን መገጠም በአላህ ብቻ ነው !!!
(መጅሙዓ ፈታዋ ኢማም ኢብን ባዝ)
.
https://t.me/alfelah0925