❤ የፍቅር ስሜት 💕((በግጥም))


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


💞💕 የፍቅር ስሜት 💕💞
🌱ሰዎችን በልቤ ማስቀመጥ ከተውኩ ቆየሁ በመዳፌ ነው የማስቀምጣቸው
በእምነት የተደገፍኳቸው ሰዎች ጥለውኝ በሄዱ ቁጥር ስወድቅ የሚሰበረው ያመነው ልቤ ነው። ከዚህ ሁሉ ይልቅ በመዳፌ ይዤ መሄድ ሲፈልጉ መውደቅ አያስፈልግም መልቀቅ ብቻ ነው ። ያኔ መሄድ ለነሱ ቀላል እንደሆነ ሁሉ ለእኔም መልቀቅ ይቀለኛል🌱
👉 @Mak_bale @joftdav @Mak_bale

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ይቅርታ ባይገባኝም ግን ምን ላድርግ እናቴ ልል የምችለው ነገር ይቅርታ ብቻ ነው ይቅርታ


።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
                       ሀ~ሴት

ሀ -- ብሎ ጅማሬ
                   የሁሉ መጀመሪያ
       የነገር የፍቅር
                   የፊደል መቁጠሪያ....
ሴ -- ትነት የታየ
                   ከዚያች ከጥንቲቱ
                   ከአምላካችን እናት....
        ከምስኪኗ ማህፀን
                   ፍቅር ከታየበት......
      
ት --  ትላንቴን ረስቼ 
                    ቃል ኪዳኔን ትቼ
                    አመጣጤን ስቼ
                    ሁላዬን ዘንግቼ
                    አንቺን ብበድልም.......

              ነብሴ ረግታ አታውቅም
                 ምንም ቃል የለኝም
 
        ------   ይ - ቅ - ር  - ታ ------

      ✍  በኔ ጥፋት አንቺን በደለኛ ላደረኩሽ
             የሆነ ቀን ማታ ላይ ስትናፍቂኝ ፃፍኩት
                      ብቻ ግን በዚህ አመት




፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
    #ይቅርታ_እራሱ_ይቀራል

   በ jo

አንቺን መልሶ .............ካላመጣሽ
ርቀሽ ከሄድሽበት .........ካልመለሰሽ
ፍቅሬን መውደዴን ........ካልነገረሽ
ለንቺ መታመኔን ...........ካላሳየሽ
        ቃሉ ብቻ ምን ያደርጋል
   ይቅር ለእግዜር ምን ይሰራል
     አንቺን መልሶ ካላመጥሽ
       ይቅርታ እራሱ ይቀራል
  
       #ላንቺ
       #ከእኔ  #ታውቂዋለሽ   #ባለሽበት
            ✍ተፃፈ በ @Mak_bale
                      22,5,2010
                         Night
                          3:25
@joftdav
@joftdav
@joftdav


Репост из: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ደስ የሚል በአል!

@ilovvl
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ


Репост из: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
"የምሰራች"
ዮም:ፍስሀ:ኮነ:በእንተ:ልደቱ:ለክርስቶስ!! ትህትናን፣ፍቅርን የሰውን ዋጋ በበረት በመወለድ:አስተማረን!!
ወልድ:ሲወለድ:የሰው:ልጅ የሚፈልገውን: አምላክነት:በእሱ:አገኘ::
ውድ የግጥም ቃና ቤተሰቦች እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰለም አደረሰህን 🙏 መልካም በአል

@ilovvll
@ilovvll
@ilovvll 👈 ቤተሰብ ይሁኑ
አብሮነትዎም አይለየን


Plss start the bot




Репост из: Fera Movie Gallery ™📽️
🎬 FERA MOVIES GALLERY



ቻናላችን ላይ ሚያገኞቸው ፊልሞች፡
🎞 ኢንግሊዘኛ ፊልሞች በትርጉም፡
🎞 የህንድ ፊልሞች በትርጉም፡
🎞 ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም፡
🎞 የቱርክ ተከታታይ ፊልሞች:
🎞 ANIMATION MOVIES በትርጉም :
🎞 የታዋቂ አክተር ፊልሞች በትርጉም :
🎞  አክሽን ፊልሞች በትርጉም:
🎞 ADVENTURE FILM በትርጉም:
🎞 HD ትርጉም የሌላቸው ፊልሞች፡
🎞 HD KORIA DRAMA :
🎞 አማርኛ ፊልሞችን እንደወጡ ያገኛሉ፡፡

ሁሉንም አይነት ፊልሞች በቅርብ ቀን በቻናላችን ይጠብቁን።

t.me/fera_Movie_Gallery
t.me/fera_Movie_Gallery
t.me/fera_Movie_Gallery


Репост из: የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
እንኳን አደረሰን

@ilovvll
@ilovvll




Репост из: ኩታ መፅሔት🗞
kuta kes 3.pdf
1.6Мб
ሰላም ሰላም👐

ጅርቱ?

ቅዳሜን ከኩታ ጋር.....
በጉጉት ስትጠበቅ የነበረው ኩታ መጽሄት አንድ ሳምንት ዘግየት በማለቷ ይቅርታዬን እንኩ እያለች በዚ ሳምንት እነሆ ጥዕሙ እና ደማም ፅሁፎችን አካታ ለአንባቢያን ደርሳለች።

ኩታን አንብቡ ለኩታ ይፃፉ!

አሻም❤️

#share

@more_more_more
@more_more_more
@more_more_more


/// ቀናሽ አሉ ///

በቆምሽበት ሌላ ሳቆም
ማዶ ሆነሽ አየሽ አሉ...
ስሜን ጠርተሽ ተንበርክከሽ
በናፍቆት ድምፅ ጮ'ሽም አሉ

አንቺን በለመንኩበት አንደበቴ
ሌላዋን እንስት ሳማክራት
ስላንቺ ህመም በሙሉ....
ከንቺን መርሳቴን ስትሰሚ
አውለበለብሽ በእጅሽ ሁሉ
በእንባ ጠፋ አይንሽ ኩሉ....

...ግና ውዴ.......

ስህተቱ አንቺው ጋር ነው
አጉል ቅናት መለየት ነው
ያጠፋሽው ያን ጊዜ ነው

እንደማልወድሽ ስታስቢ
ያልወደድኩሽ ያኔ ነው
ጠልቶኛል ብለሽ ስታወሪ
ያስከፋሽኝ ወቅት ይሔ ነው

...እናም ፍቅር.........

ሺ ቢመጣ የሚወደድ
ዙሪያዬን ቢከብኝ እንስቶች
አእላፍ አድናቆት ቢጎርፍልኝ
የፍቅር የአብሮነት ጥያቄዎች

...ይህንን እወቂ.....

ንግስቴ እንቺ ነሽ
ልቤ አንቺው ጋር ነው
ቅናት ነው ጠላትሽ
ፍቅሬ'ኮ ላንቺ ነው

✍ተፃፈ በ'' @Mak_bale'

መስከረም 3,2013

@joftdav
@joftdav
@joftdav


Репост из: ግጥም ብቻ 📘
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

>

ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
አባትነትህ ልዩ ነው
ከነውጠኞች የሚበልጥ
ለኔ ለልጅህማ
አለምን ሁሉ ሚገለብጥ

.. ዛሬ ግን..........
አባ ፈራሁ ተጨነኩኝ
ስሷ ልቤ ተቀየመች....
ካልጠበኩህ ቦታ ተገኝተህ
ምስኪን ልቤ አለቀሰች...
አዎን አባ ተቀየምኩህ
አምርሬ አነባሁኝ...
እጅህ ቀሚሴን ሲገልብ
ከባትነትህ ጠፍቶ
የአውሬ ፊትህን አየሁኝ.....

.......ግን ያልገባኝ የኔ አባት......
ምን የማታውቀው ውበት
የቱ የተደበቀ ደም ግባት
ከእኔ አልጅህ ዘንድ አየህ...
ልብህ ለሴሰኝነት ተገዝቶ
ከአባትነትህ አስበልጦ
እርካታህን ያስመረጠህ
እስኪ ተናገር ካለ
ያላየኸው የደበኩህ ልጅነቴን
ስታቅፈኝ እኮ ታውቀዋለህ
ስትኮረኩር
ስትደባብስ ሰውነቴን

አባዬ.....
አሁንም አባቴ ነህ
ስምህን የምጠራበት
ያሳደገኝ ነውና
አንገቴን ሳልደፋ በፊት
ምጠራ' የኮራሁበት

* * * * * *
ስምህ ገናና ነበር
የኔ የስም መጠሪያዬ
ከስሜ ስምህ ተከትሎ
የሙሉነት መታያዬ
* * * * * *

አዎን አባዬ...
ትዝ ይልሀል...አፌን ስፈታ ገና
አባዬ ነበር ያልኩኝ
የማነሽ ሲሉኝ እንኳን
ያባቴ ልጅ ነበር ያልኩትኝ

ዛሬ ግን....
ሴሰኝነትህ በለጠ~ ከትውስታችን አለፈና
ከእናቴ ያጣኸውን ከኔ ከልጅህ ፈለክና
እናቴ ስታልፍ እንኳን
አንተ ነበርክ እናቴ
ሰው በራበኝ ግዜ እራሱ
ሆነሀልም ጓደኛዬ....
ከዛ ሚበልጠው ግን
አባቴ ብዬህ ነበር
እኔነቴን የሚገልፅ
ክብር መከታዬ እንደ ነበር

አሁንማ....
አንተው በፈጠርከው ገላ ላይ
ተረማምደህ አረከስከው
የወደፊት እኔነቴን
በአውሬነት ደመሰስከው

አዎን የኔ....... ጀግና አባት
እውትትም ወንድ ወጥቶሀል
ሴት የሆንክ መስሎኝ ነበር
እኔን ለማሳደግ፣
ስመለከት ከሴት መሀል
ብዬ ነበር የኔ አባት
እውነትም እናት ሆኗል

ስሷ ልቤን አስከፋሀት
አዎን አባ ተቀየምኩህ
እንድተኛ
ተረት በነገርከኝ ቦታ ላይ
ዛሬ ግን
ከጭኖቼ መሀል አገኘሁህ.....

📩ይድረስ📩
>

✍ተፃፈ በ @Mak_bale
ሰኔ,2,2012

@getem
@getem
@getem


Репост из: ግጥም ብቻ 📘
​​፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨

(((እኔም #ገጣሚ_ነኝ)))

ስሙኝ.......
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
በሶሻል ሚዲያ
ስሜ ያልተጠራ
ብዙም ያልታወኩኝ....
በደሳሳ ጎጆ
ህልሜን ያጠበብኩኝ
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
*
*
*
ከምሁራን ተርታ
ፈፅሞ ያልተሰለፍኩ
ከእውቅ ፀሀፊያን
መሀል ያልተካተትኩ
እኔም #ደራሲ_ነኝ!
በሰላች ብእሬ
ስሜቴን የገለፅኩ
*
*
ነገር ግን......
እንደነ እንትና
እስካርፕ አልጠመጠምኩ
እንደ ሀያሲያን
ሸሚዝ በከረባት
ታጥቄ አለበስኩ
በአምስቱ ጣቶቼ
የእከሌን መፅሀፍ
ይዤ አልተሽከረከርኩ....
በሄድኩበት ሁሉ
#ደራሲ_ነኝ እኔ
እውቅ ነው ሀሳቤ
ብዬም አልተናዘዝኩ.....
*
*
.........ግናም እፅፋለሁ........
ብእር ከወረቀት
እያዋደድኳቸው
ለሰው የማይገባ
ዝብርቅርቅ ሀሳባት
እኔም አፈሳለሁ ...
በሀሳቤ አርግዤው
ለአእላፉ ቀናት
እያብሰለሰልኩት
ይዤው እከርማለሁ...
የቁርጥ ቀን መቶ
እስክገላገለው
ወረቀት ከብእር
እስከማጋጥመው
ብዙ አምጣለሁ...
ያማጥኩት ተባርኮ
በመድብል ሲወለድ
ማየትን እሻለሁ..
*
*
እና እንደሌሎቹ.....
#እኔም_ገጣሚ ነኝ!
ብዬ አልዘባርቅም...
የገጠምኩት #ግጥም
የደረስኩት ድርሰት
የከሌ ነው ታሪክ ነው
ብዬ አልናገርም...
*
*
እውነቱ ገብቷቸው
አንተ #ደራሲ_ነክ
የሰዎችን እውነት
በብእር የገለፅክ
ብለው እስኪረዱኝ
በቤቴ የምኖር
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!

✍ተፃፈ በ @Mak_bale
ግንቦት 1,2012

@getem
@getem
@getem


Репост из: ግጥም ብቻ 📘
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

👉👉 #ኪያዬ_አይደለሽም 👈👈

ትዝ ይልሻል #ውዴ
ያኔ... ከ 3 ወራት በፊት

እኔና አንቺ ሆነን
በፍቅርም ከንፈን፤
ህይወትን እረስተን፤
ሀዘንን አባረን፤
እየተደሰትን....
ከሰፊው ሰማይ ላይ
በፍቅር ስንበር፤
ከፊት ማለፍ ስንችል፤
ከዃላ አየቀረን፤
እየተጎተትን፤
ደስተኞች ነበርን....
አዎ ውዷ #ህይወቴ
አውቃለሁ ታውቂያለሽ፤
ይህን አትረሽውም፤
ልብ ለልብ ገጥመን፤
የየቅል ህይወት ትተን፣
እኔ ባንቺ ልብ፣
አንቺ በኔ ልብ ስንኖር
ብዙ አስበን ነበር.....
°°°°°°°°°°°
#ህይወቴ.....
አሁን ግን ከፍቶኛል....
ልቤም ሀዘን ሞልቶት
የምር ደብሮኛል....
ከሳቅም ከደስታም
ሀዘን ይቀናኛል....
ውብ ናቸው ባልሻቸው
ሁለቱም አይኖቼ፣
እንባ ተንንቆኛል...
መኖርም ስጀምር...
ከባዶ አስነስቸሽ፤
ከ ዜሮ አስጀምረሽ፤
ያዳንሽኝን ያህል፣
ደግመሽ ገለሽኛል...
አናም ውዴ....
እሱም ሲል #ኪያዬ፤
እኔም #ህይወቴ አልኩኝ...
ባነባበት መጠን፤
እኔም አነባሁኝ....
በእሱ ተስፍ መቁረጥ፤
እራሴን ከተትኩኝ.....
ሀዘኑ ሲጎዳው፤
እኔም ተጎዳሁኝ....
ተመለሺ ሲላት
እኔ አልተመኘሁም...
ደስታሽ ደስታዬ ነው
የኔ ባትሆኝም.....
°°°°°°°°°
#ኪያዬ ሲላት ግን
.....እኔ አላልኩሽም....
.....ምክንያቹም.....

አንቺ ለኔ...
#ህይወቴ ነሽ እንጂ፤
#ኪያዬ አጀለሽም።

✍ተፃፈ በ @Mak_bale
#ካነብብሽው_ላንቺ _እንደሆነ_ታቂዋለሽ።
13.6.2012
@getem
@getem
@getem


Репост из: ግጥም ብቻ 📘
✤✣ይታይሽ የኔ አለም✣✤

ይታይሽ የኔ አለም
አዎን ተመልከቺ
አስተውይ እናቴ....
የእህቶቼን ሳቅ
የልጆችሽን ድምፅ
ሳጣው ከሰፈሬ።
፨፨፨፨፨፨
አዎን ኢትዮጵያዬ
በወንዞች በሳርሽ
በእርሻ ባፈርሽ
ቦርቀው ያደጉት
እነዛ ልጆችሽ......
ዛሬ ምነው ጠፉ
ደብዛ ተሠወረ
ማን ቀማሽ ከእጆችሽ።
፨፨፨፨፨፨፨
አዎን የኔ ልእልት
የሉም ከቤታቸው
ቀዬ መንደራቸው
ብቻውን ይጮሃል..
እናትም ተጨንቃ
አይኗ አንባን ያነባል።
ህፃናት አጥተዋል
ጡትን ከአፋቸው....
የእናታቸው መጥፋት
እንባ እያስነባቸው።
ያልተዘጋው ማጀት
ዛሬም አፉን ከፍቷል ....
እምዬ ከሌለች
እታአለም ካልመጣች
አሻፈረኝ ብሏል።
፨፨፨፨
እናም እታለሜ
አዎን አስተውዪ
የህዝቦችሽን ግፍ
የአጥፊዎችሽን ደባ ...
የእህቴን በደል
የቀሚሷን እንባ።
አዎን ተመልከቺ
መፍትሔ የሌለው
ጩኸቴን አድምጪ
✣✣✣✣✣
እናም ኢትዮጵያዬ
እስኪ ጠይቂያቸው
ወንዘና ተራራ
አእዋፍ ዛፎቹን ..
ጋራ ሸንተረሩን
መስካመስክ ዋሻውን ..
አይቻለሁ ያለ
ካለ..
የሲቃን ድምፅ
ያደመጠ ...
የሀዘንን እንባ
የጠረገ...
የእምዬን ፍርሀት ተመልክቶ
ለእህቶቹ ተቆርቁሮ
አንደራሱ የታገለ
እስኪ ጠይቂ ካለ !!!!!!


✍ተፃፈ @Mak_bale
23.5.2012
@getem
@getem
@getem


አንድ ቀን ትመለሻለሽ እሱንም ቀን እጠብቀዋለሁ አውቃለሁ ምናልባት የራስሽ ሂወት ይኖርሻል...
የምታፈቅሪው የምትሞችለት ሰው...
ሁሌም ምነው እሱን ሰው ባረገኝ እላለሁ ግን እሱ ህልም ነው ተስፋ ብቻ.......


Репост из: ኩታ መፅሔት🗞
front kuta.pdf
4.5Мб
ሰላም ሰላም👐

በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው የመጀመሪያዋ ኩታ - መጽሄት ቅፅ አንድ ዛሬ ለንባብ በቅታለች።
ቤተሰብ እንፍጠር - ለወዳጅ ዘመድ ማጋራቶዎን አይርሱ።

መርሀባ
!

@more_more_more
@more_more_more
@more_more_more


Репост из: የፍፄ ግጥሞች
https://www.tiktok.com/@fitsaetv/video/7066380245036715269?_r=1&u_code=deb97268bgma2j&preview_pb=0&language=en&_d=deb972hb8kam1i&share_item_id=7066380245036715269&source=h5_m×tamp=1645317624&user_id=6870143979539727366&sec_user_id=MS4wLjABAAAAI4eMxAXv6s7AvMLRutJw8rsdJjVGrlept4HL_I3ioPXBoxo76HpLMpzdhr0VW5dU&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_app_name=musically&share_iid=6870144276551452422&share_link_id=2c63d97f-e7ee-4775-aa7b-608959a35d2b
👆👆👆👆👆on tiktok👆👆👆
የእውቀት ጅማሬ
ሲያደርሰን ለዛሬ
ያለፍነው ፈተና ይቅር አይወራ።
======================
የያሬድ አዲ መራ ዘፈን በዚህ መልኩ ተዜመ!!
======================
ተማሪዎች ፈታ በሉበት!!
=======================
Follow us
Youtube.com/fitsaetv
Facebook.com/fitsaeman
t.me/poimfitsae
t.me/ft2194
Fitsaemagna@gmail.com
Fitsae Tv on TikTok
ያለፍነው ፈተና... ወይ ተማሪነት!!! #habeshatiktok #parody #habesha

Показано 20 последних публикаций.

738

подписчиков
Статистика канала